Get Mystery Box with random crypto!

የተፈጠረው የነዳጅ እጥርት እስከ ነገ ጠዋት ድረስ ይቀረፋል የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት | ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

የተፈጠረው የነዳጅ እጥርት እስከ ነገ ጠዋት ድረስ ይቀረፋል

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት

ከሰሞኑ በአዲስ አበባ ከተማ ረጃጅም የነዳጅ ሰልፎች ማስተዋል የተለመደ ሆኗል።ይሄንንም ተከትሎ የረጃጅም የነዳጅ ሰልፎች ምክንያት ምን እንደሆነ ለማወቅ ኢቢሲ የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅትን አነጋግሯል፡፡የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ይስማ አለም ምህረቱ የነዳጅ እጥረት የተፈጠረው ጅቡቲ ላይ የዘነበውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ ድልድይ በመሰበሩ ነው ብለዋል።

በተጨማሪም ነዳጅ የጫነ አንድ የነዳጅ ቦቴ ተገልብጦ መንገድ መዘጋጋት በማስከተሉ የነዳጅ እጥረት መከሰቱን አስረድተዋል፡፡ችግሩን ለመቅረፍ ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች በድሬደዋ በኩል እንዲገቡ ተደርጓል ያሉት ስራ አስፈጻሚው ይሄንኑ ተከትሎ ትናንት ከሰአት ጀምሮ ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች መግባት መጀመራቸውን አረጋግጠዋል፡፡አክለውም ዛሬ እና ነገ ነዳጅ የጫኑ ተጨማሪ ቦቴዎች እንደሚገቡ እና ችግሩ እስከ ነገ ጠዋት ድረስ እንደሚቀረፍ ገልጸዋል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1