Get Mystery Box with random crypto!

በፒያሳና አካባቢው እየተከናወነ ባለው ግንባታ ምክንያት መንገዱ ስለተዘጋ አሽከርካሪዎች አማራጮችን | ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

በፒያሳና አካባቢው እየተከናወነ ባለው ግንባታ ምክንያት መንገዱ ስለተዘጋ አሽከርካሪዎች አማራጮችን እንዲጠቀሙ ፖሊስ አሳሰበ

ቀደም ሲል የመንገዱን መዘጋት በተመለከተ መረጃ ቢሰጥም አሁንም አሽከርካሪ ዎች ወደ ግንባታ ቦታው እየመጡ በግንባታ ስራው ላይ ጫና እየፈጠሩ መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በመሆኑም በፒያሳና አካባቢው የመንገድ ግንባታ እየተከናወነ በመሆኑ ላልተወሰነ ጊዜ መንገዱ ስለተዘጋ አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጮችን እንዲጠቀሙ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

በዚህም መሰረት፡-

• ከጊዮርጊስ አደባባይ በእሳት አደጋ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ

• ከአፍንጮ በር ወደ ራስ መኮንን ድልድይ

• ከቅድስተ ማርያም ወደ አራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር

• ከአራት ኪሎ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ

• ከባሻ ወልዴ ችሎት ወደ ቱሪስት እና ወደ ቅድስተ ማርያም

• ከእሪ በከንቱ (ቀይ ባህር ኮንዶሚኒየም) ወደ ደጎል አደባባይ እንዲሁም

• ከደጎል አደባባይ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ በሚወስዱት መንገዶች መግባት እና መንገዶቹን ለጊዜው መጠቀምም ሆነ በመንገዶቹ ላይ መኪና ማቆም እንደማይቻል ተገልጿል፡፡

ይህን በመገንዘብ አሽከርካሪዎች ከእነዚህ ውጪ ያሉ ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ እና ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትዕዛዝ ተባባሪ እንዲሆኑ ፖሊስ አሳስቧል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1