Get Mystery Box with random crypto!

ermi ye hawii.....✍

የቴሌግራም ቻናል አርማ ermiyee1 — ermi ye hawii.....✍ E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ermiyee1 — ermi ye hawii.....✍
የሰርጥ አድራሻ: @ermiyee1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.10K
የሰርጥ መግለጫ

የፍቅር✦ ታሪኮች ✦ ብቻ ጠቃሚና አስተማሪ የሆኑ ጽሁፎች የሚለቀቁበት የፍቅር ግጥሞች📖 :ዘፈኖች🎶🎵🎻 : እንዲሁም ለሚፈልጉት ሰው የፍቅር💘💘 :የ ይቅርታ :የልደት🍮 የተለያዩ መልእክቶችን የሚልኩበት ቻናል ከ እርሶ የሚጠበቀው join ብለው እዚህ @ermiyehawii ላይ ማናገር ብቻ ነው 💔💖💖💞

for any comment. @Hawiikbot

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-08-16 21:28:21 ለራስ ቃል መግባት

ነገሮች በፈለከው መንገድ ላይሄዱ ይችላሉ፣ ሰዎች ጀርባቸውን ሊያዞሩብህ ይችላሉ፣ በዚች አለም ለመኖር የሚያጓጉህን ነገሮች ሁሉ ልታጣ ትችላለህ፤ ግን ሁላችንም በዚህ ስሜት ውስጥ አልፈናል ወደፊትም እናልፍ ይሆናል።

ታላቅነት ግን በዚህ ከባድ ጊዜ መቼም ተሰፋ ቆርጠህ ጥረትህን እንደማታቆም ለራስህ ቃል መግባት ነው!

ተስፋ የሞላበት ምሽት ተመኘሁላችሁ

የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
419 viewsErmi ye Hawii, 18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 16:32:22 ከሚጎዳው በላይ ስለሚያጣቸው ይፈራል!

አንድን ሰው ከሆነ አላስፈላጊ ነገር እንዲወጣ ከፈለግህ ይጎዳሀል መጥፎ ነው እንዲ ያረግሀል አትበለው ደጋግመህ ስለዛ ነገር ጉዳት ብቻ አትንገረው ፤ አስበው ሲጋራ የሚያጨስ ሰው ከሲጋራው ካረቶን በላይ ጉዳቱን የሚያስረዳው ነገር አለ እንዴ? ግን ለእርሱ ምኑም አደለም ስለዚህ እንዲህ አድርግ ፣ በጣም የሚወዳቸውን ነገሮች ዋጋ የሚሰጣቸውን ነገሮች ፈትሽ ከዛ ቀስ በቀስ አሳውቀው እነዛን ነገሮች እያጣቸው ሊሄድ እንደሚችል ንገረው አብዝቶ የሚፈልጋቸውን ሊሆን የሚጓጓላቸውን ነገሮች እንደሚያጣ አስረዳው ያኔ መጠንቀቅ ይጀምራል!

መልካም ቀን ተመኘን

የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
405 viewsErmi ye Hawii, 13:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 15:05:28 የመኖር ተስፋ

ሰዎችን ማዳን ባትችል ቢያንስ ለሰዎች የህመም መንስኤ አትሁን!!

ሁለት ሰዎች በአንድ ሆስፒታል ክፍል ውስጥ አልጋ ይዘው ተኝተዋል። ሁለቱም በጠና ታመው በአምላክ እጅ ተይዘዋል። አንደኛው ሳንባው የቋጠረውን ውሀ ለማድረቅ ሲባል ለሰአታት ያህል አልጋው ላይ ቁጭ እንዲል ይደረጋል። አልጋው የሚገኙው በክፍሉ ብቸኛ ከሆነው መስኮት አጠገብ ነው።

ሌላኛው ህመምተኛ ደግሞ በተቃራኒው ለሰአታት በጀርባው እንዲተኛ ይደረጋል። እነዚህ ህሙማን በቆይታቸው ብዙ ተጨዋውተዋል። ስለ ቤተሰቦቻቸው ስለ ኑሯቸው በወታደር ቤት ስለሰጡት አገልግሎት የእረፍት ጊዜያቸውን የት
እንደሚያሳልፉ...ወዘተ አውርተዋል።

ከመስኮት አጠገብ ያለው ህመምተኛ ቁጭ በሚልበት ሰአት ወደ ውጭ እየተመለከተ ሁሉን ነገር በጀርባ ለተኛው ሰው ይገልጽለታል። በሚያማምሩ ዛፎች የተከበበ ሀይቅ ይታየኛል በሀይቁ ላይ
ዳኪዬዎች ይዋኛሉ ህጻናት ደግሞ ከወረቀት የሰሩትን መርከቦች በሀይቁ ዳርቻ በማስቀመጥ ይጫወታሉ...ፍቅረኛሞች በአንድ እጆቻቸው አበባ በሌላው ደግሞ ተቃቅፈው ሀይቁን ይዞራሉ ከሀይቁ ባሻገር ውብ የሆነ ከተማ ይታየኛል...በማለት ዘወትር የሚያየውን ሁሉ ይተርክለታል። በዚህ አይነት ሁኔታ ሳምንታት አለፉ።

አንድ ማለዳ ነርስዋ ገላቸውን ልታጥብ ውሀ ይዛ መጣች። ከመስኮት አጠገብ ያለው በሽተኛ ግን በህይወት አልነበረም። በጣም ደነገጠች። ጓደኛውም እንዲሁ አዘነ። ነርስዋ አስከሬኑን በቶሎ እንዲያነሱ ሰዎች ጠራች። ያ ብቻውን የቀረው በሽተኛ አልጋውን ከመስኮቱ አጠገብ ሊወስዱለት ይችሉ እንደሆነ ጠየቀ። ወሰዱለት። በመስኮት ለማየት በጣም ቸኩሏል። ቀና ብሎ ወደ ውጭ ተመለከተ። ከመስኮቱ ባሻገር ያለው ጥቁር ቀለም የተቀባ ግድግዳ ብቻ ነው።

ደነገጠ ምን ሆንክ? አለቸው ነርስዋ። ሰዉዬው ብዙ አስደሳች ነገሮችን በዚህ
መስኮት አሻግሮ ይመለከት ነበር ያዬውንም ሁልጊዜ ለኔ እየነገረ የመኖሬን ተስፋ ያለመልምልኝ ነበር አላት። ኧረ ሰዉዬው ማየት የማይችል አይነስውር ነበር አለችው። ልብ የሚነካ ነገር...ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ።

ለካስ እሱን ለማስደሰትና የመኖር ተስፋ ለመስጠት ነበር ያን ሁሉ ነገር ፈጥሮ የሚያወራው። አንዳንድ ሠዎች እንዲህ ናቸው እነሡ እየሞቱ የሠውን የህይወት ብርሀን ያለመልማሉ። ሰው የመሆን ሚስጥር ደግሞ ይህ ነው ለሰወች ደስታ መኖር። ሰው ማለት ለሰው መኖር፣ተስፋ መሆን ነው እንጂ ለሰው የችግሩ መንስኤ መሆን አይደለም።

አንተስ እስከመቼ የራስህ ብርሀን እያለህ የሠው ጭላንጭል ያስቀናሀል? እስከመቼ የሰወችን ደስታ ትገድላለህ? እስኪ ለአንድ ደቂቃ ዝም ብለህ አስብ መልካምነት እኮ አያስከፍልም።

የሠው ህይወት ማዳን ባትችል እንኳን ቢያንስ ለሠው ተስፋ ስጥ ይሄም የመልካምነት አንዱ ገፅ ነው። አስታውስ ለሰወች ደስታ መስጠት ባትችል እንኳን የስቃያቼው መንስኤ አትሁን!! መልካም አድርግ መልካምነት አያስከፍልም ዋጋህን ከአለም ፈጣሪ ከእመቤታችን ልጅ ከልዑል እግዚአብሔር ታገኘዋለህ!
መልካም ቀን

#ከወደዱት_ለወዳጅ_ዘመድዎ #share
196 viewsErmi ye Hawii, 12:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 20:56:37 ለማሸነፍ ራሳችንን መሆን ነው ያለብን!

ሴት እና ወንድ እኩል ናቸው የፈለጉትን የማድረግ ችሎታውም መብቱም አላቸው ፣ የመሳሰሉትን ነገሮች እናውቃለን ነገር ግን ይሄ ማለት ምንም የሚያለያያቸው ነገር የለም አንዳቸው የሚችሉትን በሙሉ ሌላኛቸውም ይችሉታል ወይ መቻል አለባቸው ማለት አይደለም ! እንደዛማ ቢሆን የተለያየ ፆታ መኖር አያስፈልገንም ነበር ሴት ልጅ የራሷ የሆነ የማሸነፍያ ጥበብ ተሰጥቷቷል ለማሸነፍ ለማሳካት ድል ለማድረግ ወንድን መሆን አይጠበቅባትም እህቴ ከበቂ በላይ ብልሀት እና ጥበብ በውስጥሽ አለ ስለዚህ ባለሽ ነገር ማሸነፍ ትችያለሽ ወንድሜ አንተም ሞገስ ተሰጥቶሀል አቅም አለህ ስለዚህ እንደራስህ ሆነህ አሸንፍ! የተሰጠንን ሆነን ስንኖር ትዳራችንም ቤታችንም ይሰምራል!

የተባረከ ቀን ተመኘን

የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
228 viewsErmi ye Hawii, 17:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 18:49:07 ‍ እሙዬ ተረጂኝ

ልቤ ላይ ያሰርኩት የዝምታ ማተብ
በሀቅ የታሰረ የእምነቴ ገደብ
ፈሪ ነህ ተብየ በሀሰት ስሰደብ
በቃላቶች ጅረት እውነቴ ሲታጠብ

አደዩ ልብሽን በቃላት ባልቀስመው
ጠላት ምቀኛሽን በነገር ባልነድፈው
ቃሌ ባያረካሽ ውስጥሽን ባይነካው
ዝምታዬ ጥልቅ ነው ማንም ያተረዳው

የቃላት ጥርቅም የሀገሬ ስብጥር
የዓንቀፅ ጋጋታ የድርሰቶች ክምር
ፍቅርን ላያፀና በቃል ለሚሰበር
ዝምታ ሀቅ ነው ምንም ማይበገር

ልብሽን ባገኘው በቃላት ደልየ
የሞተ አስነስቼ ያለውን ገድየ
ልብሽ ላይ ከምሰፍር ውስጤን አታልዬ
መኖር ይሻለኛል እራሴን በድዬ
መኖር ይሻለኛል እራሴን ገድዬ

ግን ልብሽ ጆሮ ሁኖ ውስጤን አድምጠሽው
የዝምታ ገዳሜን ቆርበሽ ጎብኝተሽው
የልቤ ኪዳኑን በልብሽ ከትበሽው
ፍቅሬ ላይ ኮብልይ ሀቄን ተረድተሽው።
443 viewsErmi ye Hawii, 15:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 18:45:17 ህይወት አዙሪት ናት

ረጅም ርቀት የተጓዝክ ቢመስልህ የምትጨርሰው ከጀመርክበት ነው።
ራቁትክን ትወለዳለህ እርቃንህን ወደ መቃብር ትወርዳለህ በጥርስ አልባው ድድህ እየጋጥክ ትጀምራለህ ጥርሱን በረገፈው ድድህ እያልጎጠጎጥክ ትጨርሳለህ።

ዘመንም ተምኔታዊ ነው መስከረም ጥቅምት ብሎ ያስጀምርህና መስከረም በሉ ይመጣብሀል ሰኞ ማክሰኞ ብለህ ተጉዘህ እንደገና ሰኞ ትላለህ።

ህይወት አዙሪት ናት፡ መጀመሪያህ መጨረሻህ ነው የጀመርክበትን አትናቀው ትጨርስበታለህና ተራ ሰው ሆነህ ትጀምራለህ ተምረህ ዕውቀት ብትጨምር ነገ ህዝብ ብትበታትን ተሹመህ በህዝብ ላይ ብትሰለጥን ክቡረ ክቡራን ሆነህ የወርቅ ካባ ብትለብስ የምትጨርሰው እንደ ተራ ሰው አፈር ለብሰህ ነው።

ባለማወቅ ትጀምራለህ በመዘንጋት ትጨርሳለህ ዕውቀት አላመጣህምና ዕውቀትም ይዘህ አትሔድም በለቅሶ ትጀምራለህ በጭንቅት ትጨርሳለህ በሰው እቅፍ ትጀምራለህ በሰው ሸክም ትጨርሳለህ
ህይወት መጀመሪያዋ እና መጨረሻዋ አንድ ነው ርቀህ የሔድክ ቢመስልህም ትልቅ ክብ ሰርተህ ትመለሳለህ።

አለማየሁ ዋሴ እሸቴ
#መርበብት
359 viewsErmi ye Hawii, 15:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 12:30:57 የመፍትሄ ሰው ሁን !

ማደግ ከፈለግህ የመፍትሄ ሰው ሁን "መፍትሄ ወዳለበት ገንዘብ ይፈሳል " ስለዚህ ምንም የምሰራው አጣው ካልክ ውጣ እና ዞር ዞር ብለህ አካባቢህን ቃኝ ምን ምን የጎደለ ነገር አለው? ሰዎች ምን አስፈልጎቸዎል? በዚህ ምድር ላይ ያለ ስራ ሁሉ የተፈጠረው መፍትሄ ለመስጠት ነው ህክምናው፣ ትምህርቱ ፣ ምግብ ቤቱ ፣ ልብስ ሰፊው ፣ ሊስትሮው ሁሉም የሰዎችን ችግር በመቅረፋቸው ሰው ወደ እነርሱ እየሄደ ገንዘቡን ያፈሳል ! እድለኛነታችን የእኛ ሀገር ብዙ መፍትሄ የሚፈልጉ ጥያቄዎች መኖራቸው ነው ስለዚህ የመፍትሄ ሰው እንሁን! ያኔ ከእኛም ተርፈን ለብዙው እንሆናለን!

የተቀደሰ ሀሙስ ተመኘን
358 viewsErmi ye Hawii, 09:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 10:58:22 ውሸት ሰውን ለዘላለም ይገድላል!
Lying kills a person forever!

ወዳጄ የዛሬን በማሰብ ሰውን ለማስደሰት አትዋሽ! ዛሬ ዋሽተህ ያስደሰትከው ሰው ነገ እውነቱ ሲገባው ከሰጠኸው ደስታ በላይ ውሸትህ ሞት ነው የሚሆንበት። ብዙ ጊዜ ሰዎች ነገን በመርሳት ሰውን ዛሬ ለማስደሰት ሲዋሹ ይታያሉ ይህ አግባብ ነገር አይደለም።

ካየሁት ነገር ጎራ ብዬ አንድ ታሪክ ላጫውታችሁ አንድ ልጅ አንዲትን ልጅ በጣም ያፈቅራት ነበር በምንም መልኩ ማጣት አይፈልግም ነበር ስሜቱን በደንብ ነግሯት በቃ ተረጂኝ አላት እሷም ያላሰበችው ጥያቄ ስለነበር ላስብበት ብላው ሄደች። ልጅቱ አይሆንም እንዳትለው ልጁ ሊጎዳ ሆነ እሽ እንዳትለው ለልጁ ስሜት የሌላት ሆነ ግራ ተጋባች ውሴኔ መወሰን አቃታት ምን ማለት እንዳለባት ሳታውቅ ልጁ ምን አደረግሽው የነገርኩሽን? አላት።

ምንም ውሳኔ ላይ ስላልደረሰች ደንገጥ ብላ እሽ ተቀብየሃለው አለችው ልጁም በጣም ደስ አለው የመኖሩ አንድ ተስፋ/ምክንያት ስላገኜ የሚሆነው የሚጨብጠው ነገር አጣ በቃ አለም ሙሉ ሆነችለት ይህን ነገር ያዩ ጓደኞቹ ግራ ተጋብተው ደስታህን በልኩ አድርገው አሉት ነገር ግን አልሰማቸውም ነበር። ልጅቱ በልጁ ደስታ በጣም ደስ ብሏታል ነገር ግን ነገን አላሰበችም ዛሬ መደሰቱን እንጂ ነገ እንደማላፈቅረው ሲያውቅስ ምን ይህናል ብላ በፍፁም አላሰበችም ነበር።

የዚህ ልጅ ነገር አልዋጥ ያላቸው ጓደኞቹ ደጋግመው ነገሩት ደስታህን በልኩ አድርገው ብለው ነገር ግን እምነቱ ከራሱ በላይ ስለነበረ የነሱን ሃሳብ የሚሰማበት ጊዜ አልነበረውም። ልጁም ልጅትም እንዲህ እየሆኑ ቀጠሉ ልጁ ከመጀመሪያው በላይ አፈቀራት ሁሉ ነገሩ አደረጋት እምነት ተስፋ ፍቅር በሷ ላይ ጣለ። እሷ ካለችኝ እኔ ምንም አልፈልግም አለ ወደ ፊት ከሷ ጋር ለመኖር ማለም ያዘ ልጅቱም በልጁ ደስታ በጣም ደስ ብሏታል። እንዲህ እየሆኑ ቀናቷች አልፈው ወራቶች ወራቶች አልፈው አመታት አስቆጠሩ።

አንድ ቀን ግን ይህ ደስታቸው ወደ ሃዘን መከራ ተቀየረ ለልጁ ደግሞ ሞት ሆነበት ሞት እንኳን እረፍት ነው አለም ጨለመችበት ከሚኖሩት በታች ከሞቱት በላይ ሆኖ የሚኖር የኖሪ አኗኗሪ ሆነ። ያ ቀን እሷን ለጋብቻ የጠየቀበት ቀን ነበረ ለጋብቻ ሲጠይቃት በጣም ደነገጠች ምን ሆነህ ነው አለችው አሁን እኮ ለጋብቻ አልደረስንም ብላ ምክንያት መደርደር ያዘች ልጁ ግን ምላሹ ስራ አለን ገንዘብ አለን ከዚህ በላይ ምን እንፈልጋለን አፈቅርሻለሁ ታፈቅሪኛለሽ ታድያ ከዚህ ውጭ ምን ያስፈልገናል ሲል አናዘዛት።

ልጅቱ በጣም ደንግጣለች ይህ ቀን ይመጣል ብላ በፍፁም አላሰበችም ነበር እሷ ያዬች በሷ መደሰቱን እንጂ ቀኖች እንዲህ ፈጥነው እዚህ እሚያደርሷት አልመሰላትም ነበር። ልጁ አሁንም ድጋሚ ጠየቃት ተንበርክኮ ታገቢኛለሽ ወይ አላት። ተነስ ብላ አባብላ ልታስነሳው ሞከረች ግን አልሆነም ምን ማለት እንዳለባት ሳታውቅ ዝም አለች ልጁም ያላሰበው ነገር ስለገጠመው ደንግጦ ምን ተፈጠረ ምን ሆነሻል አላት እሱ እሚያስብ እሷ ያለ እሱ እሱ ደግሞ ያለ እሷ መኖር እንደማይችሉ ነው።

እውነታው ግን እሱ ያለ እሷ መኖር አይችልም እንጂ እሷ ያለ እሱ መኖር ትችላለች ትወደዋለች እንጂ አታፈቅረውም። በጣም ሲያፋጥጣት እውነቱን ዛሬ ካልነገርኩት ከባድ ነው ብላ በማሰብ እኔ አንተን በጣም ነው እምወድህ ምንም እንድትሆንብኝ አልፈልግም እወድሃለሁ እንጂ እኔ ላንተ የፍቅር ስሜት የለኝም አለችው።

ልጁ ማመን አልቻለም በጣም ተጎዳ ለምን እውነቱን ከፊት አልነገርሽኝም አለ ግን አልመለሰችለትም ልቡ ተሰበረ ከሰው እራቀ በየ ጎዳናው ብቻውን እያወራ መሄድ ጀመረ ልጅቱ በልጁ ሃዘን ልቧ አዘነ ግን እሱን ለመጥቀም እንጂ ለመጉዳት ስላልነበረ ያደረገችው በሱ ተፅናናች። በዬ ቀኑ ግን ልጁ እያበደ ጤንነቱን እያጣ መጣ ከወራት በኋላ የአዕምሮ በሽተኛ ሆነና ሆስፒታል ገባ። ሆስፒታል ቢገባም መዳን ግን አልቻለም ነበር።

ልጅቱም በዚህ ነገር አዝና ስራዋን አቆመች እራሷን ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ አደረገችው ህሊናዋ አንቺ ነሽ ከስራ ከአለም ሁሉ ያስወጣሽው አላት እሷም ከጊዚያት በኋላ በፀፀት ብዛት እራሷን አጠፋች። አዬህ ወዳጄ መጀመሪያውኑ እውነቱን ብትናገር እሱም ባላበደ እሷም ባልሞተች ነበር። የውሸት መጨረሻው አይምርምና አትዋሽ!! You see, lying kills a person forever!

ወዳጄ ዛሬ የምታደርገው ነገር የነገ መንገድህ ነው። ዛሬ ጥሩ ካደረክ ለነገ ሰላም ተስፋ ይሰጥሃል መጥፎ ካደረክ ግን ፀፀት ያለብስሃል። ዛሬን አስደስታለው ብለህ የአንተንም የሰውም ህይወት አታበላሽ። እውነትን አትሸሽግ ዛሬ ይጎዳል ብለህ በውሸት የሸፈንከው እውነት ህይወት ሊነጥቅ ስለሚችል ለጊዚያዊ ደስታ ብለህ አትዋሽ። መፅሐፍ ቅዱስ ላይ ከተዘረዘሩት አስርቱ ቃላት ውስጥም አትዋሽ እሚለውን መዘንጋት የለብህም!!!

ወይኩን ቡሩከ ስሙ ለእግዚአብሔር እምስራቀ ፅሃይ እስከነዐረብ ይትአኮት
333 viewsErmi ye Hawii, 07:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 10:47:39 ልበ ሙሉነት !

በከባዱ ግዜህ ማን ነበር ያገዘህ? አይዞሽ ብለውሽ ነው ያመለጥሽው ወይስ ብዙ ለፍተሽበታል? ብዙውን ግዜ ብዙ ነገሮችን በራሳችን ጥንካሬ አሸንፈናል ከጥቃቅን እስከ ትላልቅ የሚባሉ ፈተናዎችን ምንም እንኳን እገዛ ቢሰጠንም ካለ እኛ ጥንካሬ ግን ማለፍ የማይችሉ የነበሩ ሁሉ አልፈዎል ፤ ስለዚህ እንችላለን መጠንከር ማሸነፍ ማሳካት እንችላለን ፣ አጋዥ የለኝም ሰው የለኝም ገንዘብ የለኝም ማድረግ አልችልም የሚል ሀሳብ ከዚህ በኋላ የለም ! ያለእገዛ ከፈጣሪ ጋር ብዙ አሳክተሻል እና!

ደስ የሚል ቀን ተመኘን
315 viewsErmi ye Hawii, 07:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ