Get Mystery Box with random crypto!

ermi ye hawii.....✍

የቴሌግራም ቻናል አርማ ermiyee1 — ermi ye hawii.....✍ E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ermiyee1 — ermi ye hawii.....✍
የሰርጥ አድራሻ: @ermiyee1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.10K
የሰርጥ መግለጫ

የፍቅር✦ ታሪኮች ✦ ብቻ ጠቃሚና አስተማሪ የሆኑ ጽሁፎች የሚለቀቁበት የፍቅር ግጥሞች📖 :ዘፈኖች🎶🎵🎻 : እንዲሁም ለሚፈልጉት ሰው የፍቅር💘💘 :የ ይቅርታ :የልደት🍮 የተለያዩ መልእክቶችን የሚልኩበት ቻናል ከ እርሶ የሚጠበቀው join ብለው እዚህ @ermiyehawii ላይ ማናገር ብቻ ነው 💔💖💖💞

for any comment. @Hawiikbot

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-26 19:31:04
#ምሬት

ምሬት ሲበዛ ሰዉ መኖር ይደክመዋል፡፡ ፍቅር ሲበዛ ደግሞ መኖር መኖር ያሰኘዋል...ነገን ይናፍቃል፡፡ በዚህ እልህ አስጨራሽ የምድር ኑሮ ይብዛም ይነስም ምሬቶቻችን አያሌ ናቸዉ፡፡

ከእንጀራና ወጥ ጀምሮ እስከ ሃገር ብዙ ነውጦች በልባችን ይከሰታሉ፡፡ ልባችን ብዙ ሲበጠበጥና ማረፍ ሲሳነዉ እዚህም እዚያም እያለ ያስቸግራል...ልብ ማስቸገር ከጀመረ ደግሞ እንደህፀን ልጅ በል ተዉ! ብለን በቀላሉ አንገታዉም፡፡

ልብ አሸባሪ ነዉ...በሚያየዉና በሚሰማዉ እያንዳንዱ ነገር ይሸበራል...ቀን እየገፋ ሲመጣ በህይወት የሚሰለችና ቶሎ የሚመረር ልብ በየቦታዉ እየበዛና፣ እየጨመረ፣ እየፈላ ይመጣል፡፡

የምሬት ዋናዉ መድሃኒት ብዙ ነገሮችን ማሳለፍ ይመስለኛል፡፡ ባየነዉና በሰማነዉ ነገር ሁሉ ልባችን እየተራገመና ደማችን ከፍ እያለ ከሄደ ብዙ የህይወት አቅጣጫችንን ማበላሸት እንጀምራለን፡፡

እራሳችን ያወላገድነዉን ኑሮ ደግሞ ማንም ሊያቃናልን አይችልም፡፡ አንድ ሰዉ እንደተናገረዉ “መንገድ ላይ በሚጮህብህ ዉሻ ላይ ሁሉ ድንጋይህን አትወርውር” እንዳለዉ በያንዳንዱ ቅፅበት ያለንን ማንነት አላፊ አግዳሚዉ ባወራዉ ላይ ሁሉ መሳተፍ እፈልጋለሁ ካልን ትልቅ ኪሳራ ዉስጥ እንገባለን፡፡

እንደኛ እንጀራ ለመብላት ደፋ ቀና በሚል ህዝብ መካከል ምሬቶቻችንን ብንዘረግፈዉ አዉርተን ዝንት አለም አንጨርሰዉም፣ ነገር ግን መልካሙን፣ ተስፋ የሚሰጥበትን፣ ብሩሁን ከዚህ ጨለማ ዉስጥ ሻማችንን አብርተን እንፈልግ!

#እኔው_ነኝ_ወንድማችሁ.!
218 viewsErmi ye Hawii, 16:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 18:30:32 ለመውደቅ አትሞክርም!

አዎ! ትሞክራለህ ትወድቃለህ ፣ ድጋሜ ትሞክራለህ ድጋሜ ትወድቃለህ ፣ አሁንም ትሞክራለህ አሁንም ትወድቃለህ ፣ የውድቀትህ ድግግሞሽ ሙካራህን አያቆምም በምትኩ እራስህን ወደማወቅ ፣ እራስህን ወደማግኘት ያቀርበሃል ። የጉዞህ አካል ውድቀት ፣ ስብራት ፣ ህመም ፣ ስቃይ ነው ። ሃሳብህ መሻገር እንጂ ወድቆ መቅረት አይደለም ፣ ውጥንህ ከፍ ማለት እንጂ ባሉበት መቅረት አይደለም ፣ ፍላጎትህ መሻሻል እንጂ ዘወትር ተመሳሳይ ህይወት መኖር አይደለም ። ስለዚህ የመረጥከውን ትጀምራለህ ፣ ትሞክራለህ ፣ ትወድቃለህ ደጋግመህም ትነሳለህ ።

አዎ! ጀግናዬ..! ለመውደቅ አትሞክርም ፤ ለማቆም አትጀምርም ፤ ተንኮታኩቶ ለመቅረት አትጥርም ። የጅማሬህ ውጥን መጨረሻ አለው ፣ የሙከራህ ጥንስስ ግብ አለው ። ውድቀትህ አንድ ቀን እንደሚያበቃ ታውቃለህ ፣ በእያንዳንዱ ሙከራህ የምታካብተው ክህሎት ፣ የምታሻሽለው ስጦታ አለ ። ህልምህን እንዳትኖር የሚያግድህ ውድቀትህ አይደለም ፣ ስብራትህ አይደለም ፣ የመንገዱ ስቃይም አይደለም ፤ የውድቀት ፍራቻህ ፣ የመገፋት ስጋትህና የህመሙ ሽብር ነው ። ሃሳብህ ትልቅ ከሆነ በትንሹም ቢሆን መውደቅህ ፣ መቃጋጥህና በእራስህ ማዘንህ አይቀርም ። ዋናው ግን እርሱ አይደለም ፤ የሃሳብህ ትልቅነት የሚታወቀው ለስኬቱ ብለህ በምትከፍለው ዋጋ ነው ፤ በምትጋፈጠው ተግዳሮት ልክ ነው ።

አዎ! ትልቅ ህልም ይኑርህ ፣ ግዙፍ ራዕይ አንግበህ ተነስ ፣ ሁሉን አቀፍ እቅድ ይኑርህ ፣ ነገር ግን እርሱን ለማሳካት እስከምን ድረስ ትጓዛለህ ? እስኬት ትፋለማለህ ? ለእርሱ ብለህ ስንቴ ለመሳሳት ፣ ስንቴ ለመታረም፣ ስንቴ ለመውደቅ ፣ ስንቴስ ለመነሳት ዝግጁ ነህ ? ብዙዎች ብቁ ያልሆኑበትን ህልምህን መኖር ጀምረሃል ፤ ጥቂቶች የሚሻገሩትንም ውድቀት ትሻገረዋለህ ፤ ብዙዎች የሚፈሩትንም ትቺት ፣ ዘለፋና ስህተትም በድፍረት ትጋፈጠዋለህ ። ስለወደክ አታቆምም ፤ ስተወቀስክ አትረታም ፤ ስለተሳሳትክ አትሸነፍም ። እስክታሸንፍ አታቆምም ፤ ግብህን እስክትመታ ፣ ህልምህን እስክታሳካ ሸብረክ አትልም ። ከምንም የላቀ ግብ ፣ ከምንም የሚበልጥ ራዕይ አለህ ። ካንተም በላይ ብዙዎችን ቀያሪው ሃሳብህ አብሮህ አያረጅም ፣ ይዘሀው አታልፍም ፤ ትተጠቀምበትና ትጠቅምበት ዘንድ ግዴታ ነው ።

አዎ! ሙከራህ ፣ ጅማሬህ ፣ ጥረትህ ለመውደቅ ብሎም ወድቆ ለመቅረት አይደለም ። ከውድቀትህ ለመማር ፣ ዳግም ለመነሳት ፣ ስህተቶችንም ለማረም ነው ። በምትፈራው ውድቀት አትሸበር ፣ በስህተት ስጋት አትታሰር ፤ ለእርማት ፣ ለመሻሻል ፣ ለማደግና ለመቀየር ሁሌም ዝግጁ ሁን ።
═════════❁✿❁ ═════════
አንብባችሁ #ሼር አላደርግ ስትሉ #ብሞት እንኳን #የማትቀብሩኝ አይነት ስሜት ነው የሚሰማኝ #ልሙትላችሁ ሆሆ ፣ ለማንኛውም አሁንም #ሼር አድርጉልን የቴሌግራም ቻናላችንንም ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/ermiyee1
211 viewsErmi ye Hawii, 15:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 08:10:29 "አለማወቅ ከተጠያቂነት አያድንም !"

ስላላወቅኩ ነው አልሰማውም ነበር ብለን ከፍርድ መዳን አንችልም በላይኛውም በዚህኛውም ምድር ጥፋት ሁልግዜም ጥፋት ነው ! በህይወትም ባለማወቅ ፣ ባለመረዳት ብዙ ነገሮችን አጥተናል ከዚህ በኋላ ግን እስቲ ይብቃን መንገዳችን የተበላሸ ሲመስለን ኑሮ ሲቆረቁረን እስቲ ራሳችንን እንፈትሸው ልክ ያልሆነውን ነገር ተምረን እንለውጠው ለማወቅ አንተኛ!

የተባረከ ቀን ተመኘን
227 viewsErmi ye Hawii, 05:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 20:57:57 በፈጣሪህ እመን...ከዛ በራስህ እመን!

"ማየት ማመን ነው" ሲባል እንሰማለን ግን አንድ ነገር ካየኸውማ ማረጋገጥ ነው የሚባለው። ማመን ያለብህ ገና ያላየኸውን ነው፤ ገና እጅህ ውስጥ እንዲገባ የምትፈልገውን ደስታ፣ ሀብትና መንፈሳዊ እርካታ ገና ከመሳካቱ በፊት እንደሚሳካ እርገጠኛ መሆን ነው ማመን ማለት።

እልም ባለ ጨለማ ውስጥ ብርሀን የሚያይ ሰው ከምንም ነገር ይወጣል፤ ወዳጄ እምነት እንዳለው ሰው ሀያል የለም፤ አስፈሪ የሚመስሉ ሁኔታዎችና ነገሮች ሁሉ በእምነትህ ፊት ቁጫጭ ናቸው!

ውብ ምሽት ተመኘንላችሁ

የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
237 viewsErmi ye Hawii, 17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 21:00:41 የማይፈልገውን ተወው!

አንዳንዴ እንዲጠቀም የምትፈልገው ፣ ለውጥን የምትመኝለት ፣ ችግሮቹን ለመቅረፍ የምትጥርለት ሰው እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይከትሃል ። እያሰብክለት ይወቅስሃል ፣ እየተንከባከብከው ምንም ነገር አይጥመውም ፤ መልካሙን ብትመኝለትም ፣ ብትጨነቅለትም ላንተ ሃሳብ ምንም ግድ የለውም ። በእራሱ ላይ ሙሉ ስልጣን እንዳለው ብትነግረውም አይሰማህም ፣ ሊረዳህ ፍቃደኛ አይሆንም ፣ ውስጡ የተሰገሰገው አሉታዊ ሃሳብ ያንተን መልካም ሃሳቦች ውጦ ያስቀራቸዋል ። በዚህ ሰዓት ትግሉን ማቆምና ሰውየውን መተው መቻል ትልቅነት ነው ።

አዎ! ጀግናዬ..! የማይፈልገውን ተወው ፤ ካልተረዳህ ብዙ አትድከም ፤ ሲገባው ይገባዋል ፤ ካልገባውም እንዳይገባው ፈልጎ እስከሆነ ድረስ እርሳው ። ምንም የማይፈልግን ፣ ውስጡ በተቃርኖ ሃሳቦች የተሞላን ፣ የለውጥ እይታዎች ፣ የእድገት እሳቤዎች የማይጥሙትን ፣ መልካም ሃሳቦች ህመሙ የሆኑተን ሰው ከመራቅ ውጪ ሌላ የሚበጅ ተግባር አይኖርም ። ተስፋ መቁረጥ ይጋባል ፤ ማማረር ይተላለፋል ፤ በትንሹም በትልቁም ማለቃቀስና ማሳበብ ክፉ አባዜ ነው ይወረሳል ። ሁሌም ሲያማርር ትሰማዋለህ ፣ ማማረሩን እንዲያቆምና የተሻለ ቦታ ላይ እንዲገኝ ልትረዳው ስትሞክር ግን በፍፁም ሊሳማህ አይፈቅድም ። ከጀምሩ ምሬት የሚባለው ነገር ከማንነቱ ጋር ተዋህዷልና ባይመቸውም አንሶ ላለመታየት እንደተመቸው አድርጎ እየኖረበት ነው ።

አዎ! እርሱ ፍላጎቱና ምርጫው ነውና ሊከበርለት ይገባል ። " መለወጥ ፣ ማደግ ፣ ከፍ ማለት አልፈልግም ፤ ያለውበት ተመችቶኛል አትነካኩኝ ፤ ሲነኩኝና ሲያግዙኝ ሲያበረቱኝ አልወድም " የሚልን ሰው ከመራቅ ውጪ ምንም የሚደረግ ነገር አይኖርም ። ሁላችንም የፈለግነውንና የመረጥነውን የህይወት ዘይቤ የመኖር መብት አለን ። በንቃት የተሞላ ፣ በመልካምነት የተቃኘ ፣ እለት እለት የተሻሉ ነገሮች የሚከወኑበት ፣ ባለራዕይና ህልመኛ ፣ በአዎንታዊ ሃሳቦች የታነፀ ፣ የፈለገውን በማሳካት የሚያምን የህይወት ዘይቤና መርህ ያለው ሰው መቼም ችግር ፈጣሪ ሆኖ አያውቅም ። በዚህ ተቃራኒ የቆመ ፣ ከማሳበብና ከማማረር የዘለለ የሆን ነገር ማድረግ የማይችል ፣ ዘወትር መንቀፍና መተቸት የሚቀለውን መደበኛ ሰውን ጥሎ የማለፍና የመተው አቅሙ አለህና እርግፍ አድርገህ ተወው ፣ በእርሱ ምክንያት እራስህን አታድክም ። በሃሳብህ የሚስማማውን ፣ ድጋፍህን የሚቀበለውን ፣ አዎንታዊና ንቁውን ሰው ይዘህ ወደፊት ተጓዝ ፣ ሃሳብህን ሙላ ፤ ምኞትህንም አድርስ ።
═════════❁✿❁ ═════════
አንብባችሁ #ሼር አላደርግ ስትሉ #ብሞት እንኳን #የማትቀብሩኝ አይነት ስሜት ነው የሚሰማኝ #ልሙትላችሁ ሆሆ ፣ ለማንኛውም አሁንም #ሼር አድርጉልን የቴሌግራም ቻናላችንንም ግቡና Join አድርጉ ።
https//t.me/ermiyee1
277 viewsErmi ye Hawii, 18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 20:53:57 "እልፍ ሲሉ እልፍ ይገኛል!"

አንዳንዴ የሆነ ቦታ ላይ የምንፈልገው ነገር ይኖራል ከእርሱ ውጪ ምንም ነገር የሌለ ይመስለናል ፤ አልተሳካም ማለት በቃ አለቀልን መንገድ ላይ መቅረታችን ነው ፣ የእኛ ነገር አበቃ ተበላሸ ይመስለናል ግን ደግሞ ከአጠገቡ ሌላ ትልቅ እድል ትልቅ ህይወት ተቀምጦ ይጠብቀናል የፈጣሪ አላማ እኮ ሁሌም ለእኛ የሚበጀውን መስጠት ነው እንጂ ፈፅሞ ሊጥለን አይፈቅድም የአንዱን በር ሲዘጋብን ሌላውን ወለል አድርጎ እየከፈተው ነው ስለዚህ አትቁም ዞር ዞር ብለህ ተመልከት ይሄ ተዘጋ እንግድያው ያ ተከፍቷል በል መቼም አትቁም!

የስኬት ምሽት ተመኘን
233 viewsErmi ye Hawii, 17:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 21:17:22 ውስጥህ ምን እያለህ ነው!

እኛ የሚሰማን ስሜት ሌሎች አይሰማቸውም ፣ ፈጣሪ በሁላችንም ልብ ውስጥ ምን ማድረግ እንዳለብን አስቀምጦልናል ፤ አንዳንዴ ልባችን እያወቀ ውስጣችን ልክ እንዳልሆነ እየነገረን የምንሰራቸው ስራዎች ምንም ያህል ብንሄድባቸው ትክክል አይመጡም ከእኛ ጋር አይገጥሙልንም ፤ ምን አልባት እኛ ያመንበት ከሌሎች ጋር ላይጣጣም ይችላል ግን ደግሞ ይባስ የሚከብደው ከራሳችን ጋር ሳይጣጣም የምናደርገው ነገር ነው! ለመደነቅ ወይ ከሁሉም ሰው ድጋፍ ለማግኘት ከምትሰራው ይልቅ በልብህ በመደገፍ የምትሰራው ያዋጣሀል !

ደስ የሚል ምሽት ተመኘን

የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
315 viewsErmi ye Hawii, 18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 12:07:12 ከጣልከው አይነሳም !

ወፍራምን ሰው ለመጣል ከባድ ነው ከበድ ያለ ትግል ይጠይቅ ይሆናል ነገር ግን ከወደቀ ፈፅሞ አይነሳም ፤ አንተም አንቺም ከባድ የሆነ ወቅት ላይ ትሆናላችው ችግሩን ለመጣል የማትችሉ ያህል ተሰምቷችው ይሆናል ነገር ግን ሙሉ አቅማችውን ተጠቅማችው ጣሉት ችግራችው ወፍራም መሆኑን ውደዱት ምክንያቱም አንዴ ከጣላችውት በኋላ ፈፅሞ ሊነሳ አይችልም! ቀላል የሆኑ ትግል የማይፈልጉ ነገሮች እኛንም አያጠነክሩንም ስለዚህ ደስ ይበልህ! ደግመህ የማትገባበት ልትጥለው የምትችለው ፈተና ነው እና የተሰጠህ!

የተባረከ ሰንበት ተመኘን

የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
309 viewsErmi ye Hawii, 09:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 11:56:41 በሁሉም ምርጥ መሆን!

ሙሉ ሰውነትህ ቢወፍር የተለመደ ነው፤ አንድ እጅህ ተነጥሎ ቢወፍር ግን እንግዳ ነገር ነው። አየህ መዝናናትና ፈታ ማለት ላይ ምርጥ ሆነህ ነገር ግን ስራህ ላይ፣ መንፈሳዊ ህይወት ላይ፣ የቤተሰብ ወይ የፍቅር ግንኙነት ላይ ከፈዘዝክ ይሄን ምሳሌ አስታውስ። ወዳጄ የሁሉንም ነገር ሚዛን ማስጠበቅ አለብህ።

የተባረከ ምሽት ተመኘንላችሁ

የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
289 viewsErmi ye Hawii, 08:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 14:58:42 ስኬት ለሚገባው የፈጣሪ ስጦታ ነው!

በጣም በሚገርም ሁኔታ በጣም ትልቅ ስኬት ላይ ያሉ የሚያስቡትን ትላልቅ ሀሳብ ያሳኩ የእውነት ደስተኛ የሆኑ ሰዎች የህይወታቸው ትልቁን ድርሻ የሚሰጡት ለፈጣሪ ነው ፤ እንዴት ተሳካልህ ሲሉት ፈጣሪ በመንገዴ ሁሉ ከእኔ ጋር ሆኖ ረዳኝ እኔ በብዙ ለፋው እርሱም እንደሚገባኝ አይቶ ካሰብኩት በላይ ሰጠኝ ብለው በልበ ሙሉነት ይናገራሉ ፤ የፈጣሪ ዋጋ የገባው ሁሌም አሸናፊ ነዉ!

ደስ የሚል ቀን ተመኘን

የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
402 viewsErmi ye Hawii, 11:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ