Get Mystery Box with random crypto!

የመኖር ተስፋ ሰዎችን ማዳን ባትችል ቢያንስ ለሰዎች የህመም መንስኤ አትሁን!! ሁለት ሰዎች በ | ermi ye hawii.....✍

የመኖር ተስፋ

ሰዎችን ማዳን ባትችል ቢያንስ ለሰዎች የህመም መንስኤ አትሁን!!

ሁለት ሰዎች በአንድ ሆስፒታል ክፍል ውስጥ አልጋ ይዘው ተኝተዋል። ሁለቱም በጠና ታመው በአምላክ እጅ ተይዘዋል። አንደኛው ሳንባው የቋጠረውን ውሀ ለማድረቅ ሲባል ለሰአታት ያህል አልጋው ላይ ቁጭ እንዲል ይደረጋል። አልጋው የሚገኙው በክፍሉ ብቸኛ ከሆነው መስኮት አጠገብ ነው።

ሌላኛው ህመምተኛ ደግሞ በተቃራኒው ለሰአታት በጀርባው እንዲተኛ ይደረጋል። እነዚህ ህሙማን በቆይታቸው ብዙ ተጨዋውተዋል። ስለ ቤተሰቦቻቸው ስለ ኑሯቸው በወታደር ቤት ስለሰጡት አገልግሎት የእረፍት ጊዜያቸውን የት
እንደሚያሳልፉ...ወዘተ አውርተዋል።

ከመስኮት አጠገብ ያለው ህመምተኛ ቁጭ በሚልበት ሰአት ወደ ውጭ እየተመለከተ ሁሉን ነገር በጀርባ ለተኛው ሰው ይገልጽለታል። በሚያማምሩ ዛፎች የተከበበ ሀይቅ ይታየኛል በሀይቁ ላይ
ዳኪዬዎች ይዋኛሉ ህጻናት ደግሞ ከወረቀት የሰሩትን መርከቦች በሀይቁ ዳርቻ በማስቀመጥ ይጫወታሉ...ፍቅረኛሞች በአንድ እጆቻቸው አበባ በሌላው ደግሞ ተቃቅፈው ሀይቁን ይዞራሉ ከሀይቁ ባሻገር ውብ የሆነ ከተማ ይታየኛል...በማለት ዘወትር የሚያየውን ሁሉ ይተርክለታል። በዚህ አይነት ሁኔታ ሳምንታት አለፉ።

አንድ ማለዳ ነርስዋ ገላቸውን ልታጥብ ውሀ ይዛ መጣች። ከመስኮት አጠገብ ያለው በሽተኛ ግን በህይወት አልነበረም። በጣም ደነገጠች። ጓደኛውም እንዲሁ አዘነ። ነርስዋ አስከሬኑን በቶሎ እንዲያነሱ ሰዎች ጠራች። ያ ብቻውን የቀረው በሽተኛ አልጋውን ከመስኮቱ አጠገብ ሊወስዱለት ይችሉ እንደሆነ ጠየቀ። ወሰዱለት። በመስኮት ለማየት በጣም ቸኩሏል። ቀና ብሎ ወደ ውጭ ተመለከተ። ከመስኮቱ ባሻገር ያለው ጥቁር ቀለም የተቀባ ግድግዳ ብቻ ነው።

ደነገጠ ምን ሆንክ? አለቸው ነርስዋ። ሰዉዬው ብዙ አስደሳች ነገሮችን በዚህ
መስኮት አሻግሮ ይመለከት ነበር ያዬውንም ሁልጊዜ ለኔ እየነገረ የመኖሬን ተስፋ ያለመልምልኝ ነበር አላት። ኧረ ሰዉዬው ማየት የማይችል አይነስውር ነበር አለችው። ልብ የሚነካ ነገር...ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ።

ለካስ እሱን ለማስደሰትና የመኖር ተስፋ ለመስጠት ነበር ያን ሁሉ ነገር ፈጥሮ የሚያወራው። አንዳንድ ሠዎች እንዲህ ናቸው እነሡ እየሞቱ የሠውን የህይወት ብርሀን ያለመልማሉ። ሰው የመሆን ሚስጥር ደግሞ ይህ ነው ለሰወች ደስታ መኖር። ሰው ማለት ለሰው መኖር፣ተስፋ መሆን ነው እንጂ ለሰው የችግሩ መንስኤ መሆን አይደለም።

አንተስ እስከመቼ የራስህ ብርሀን እያለህ የሠው ጭላንጭል ያስቀናሀል? እስከመቼ የሰወችን ደስታ ትገድላለህ? እስኪ ለአንድ ደቂቃ ዝም ብለህ አስብ መልካምነት እኮ አያስከፍልም።

የሠው ህይወት ማዳን ባትችል እንኳን ቢያንስ ለሠው ተስፋ ስጥ ይሄም የመልካምነት አንዱ ገፅ ነው። አስታውስ ለሰወች ደስታ መስጠት ባትችል እንኳን የስቃያቼው መንስኤ አትሁን!! መልካም አድርግ መልካምነት አያስከፍልም ዋጋህን ከአለም ፈጣሪ ከእመቤታችን ልጅ ከልዑል እግዚአብሔር ታገኘዋለህ!
መልካም ቀን

#ከወደዱት_ለወዳጅ_ዘመድዎ #share