Get Mystery Box with random crypto!

ትክክለኛ ኢትዮጵያዊ ባህሪይ ያለው መንግስት አግኝተናል!!! መንግስታችን የኛን ባህሪይ ወርሶ እኛን | Yihune Ephrem Kassahun

ትክክለኛ ኢትዮጵያዊ ባህሪይ ያለው መንግስት አግኝተናል!!!
መንግስታችን የኛን ባህሪይ ወርሶ እኛን መስሎ እያስተዳደረን መሆኑን ተገንዝባችሁት ይሆን? መንግስትም ልክ እንደህዝቡ ድህነትን ሳይሆን ደሃ መባልን የሚጠየፍ፤ የሚበላው ሳይኖረው 20 ሺህ ብር ስልክ ይዞ እንደሚቧዝን ህዝብ ለእይታ ብቻ የሚጨነቅ መንግስት፤ ችግረኛ ቤተሰቦቹን ከመርዳት ይልቅ ባለፀጋ ለመመስል ያገኛትን ብር ለገፅታ ግንባታ እንደሚጠቀም ምስኪን ኢትዮጵያዊ ፍጡር ስንት ረሃብተኛ ህዝብ ባለበት ሐገር ፏፏቴ ስር አፍሪካ መሪዎችን እራት በመጋበዝ ሐብታም መንግስት መስሎ መታየት የሚፈልግ ምስኪን፤ ውስጡ በመጠጥ ተቃጥሎ ጉበቱ ተጎድቶ ፊቱ ወዛም መስሎ እንደሚታይ ሰካራም አፋር ላይ ጭስ እያለ ሸገር ላይ ፈንዲሻ መስሎ የሚቀርብ መንግስት ኢትዮጵያን እየገዛ ነው፡፡
ከሰሞኑ እንኳን የአፍሪካ መሪዎች በየጎዳናው ያሉ ድሃዎችን አይተው እንዳይታዘቡን ድሃ ሀብታም ፊት እንዳይታይ ደብቀናል፤ ድህነትን ሳይሆን ደሃን ተጠይፈናል፡፡ ልክ እንደህዝባችን በድህነት መኖርን ሳይሆን ደሃ መባልን አጥብቆ የሚጠየፍ መንግስት ሾመናል፡፡ ይህ ሀገርና ህዝብ ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም ላይ ለፈፀመው ክህደት ገና ስንት መስሎ መኖር የሚፈልግ፤ አእምሮውን ሳይሆን ውጫዊ ገፅታውን ማስተካከል የሚፈልግ መንግስት እንደሚመራት ፈጣሪ ይወቀው፡፡ እውነተኛው የኢትዮጵያ ድሃ ህዝብ መሪ ኮሎኔል መንግስቱ ይህ ሁሉ ሲሆን ቆሞ ያያል፤ አስመሳዩ እየተቀያየረ ኢትዮጵያን ይገዛል፤ ይበለን አዎ በደንብ ይበለን!!!! እዚህ ፅሁፍ ስር እየመጣህ መንጌ እንዲህ አደረገን እያልክ የምታላዝን በሙሉ አንተን የመሰለ መንግስት እየተፈራረቀ እየገዛህ ነውና እንኳን ደስ አለህ፡፡