Get Mystery Box with random crypto!

ተስፋየ ገብረአብ እኮ ...... ተስፋዬ ገብረአብ ደርግ ሊወድቅ አካባቢ ፕሬስ መምሪያ ውስጥ ሲሰ | Yihune Ephrem Kassahun

ተስፋየ ገብረአብ እኮ ......

ተስፋዬ ገብረአብ ደርግ ሊወድቅ አካባቢ ፕሬስ መምሪያ ውስጥ ሲሰራ ቅልጥ ያለ የኢሠፓ ደጋፊ ነበረ፤ ጦርነት ለመዘገብ በረሃ ወርዶ በወያኔ ሲማረክ ቀንደኛ የህወሃት አባል ሆነ፤ ሕወሃት ስልጣን ሲይዝ የህወሃት አመራሮችን ለማስደሰት ሲል በአማራውና በኦሮሞው መካከል ግጭት ለመፍጠር ልቦለድ ፅፎ ታሪክ ፃፍኩ አለን፤ ከህወሃት ጋር ያለው ፍቅር ጋብ ሲል በኬንያ አድርጎ ደቡብ አፍሪካ ከገባ በኋላ ወደኤርትራ በመሄድ የሻእቢያ አፈቀላጤ ሆነ፤ ሆላንድ ሲገባ ደግሞ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ መፅሀፉ ላይ አስተያየት እንዲጽፉ በመለመን የግንቦት ሰባት ደጋፊዎች ልብ ውስጥ ለመግባት ሞከረ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ስለመፅሃፉ አስተያየት ቢፅፉለትም ያሰበው ነገር አልሳካለት ሲል ወደኦነግ በመቅረብ ኦሮሞ ነኝ ሲል ሆላንድ ላይ በተካሄደው የኦሮሞ ኮሚኒቲ ኮንፍረንስ ላይ ተናግሮ ኦሮሞ መስሎ ኦነጎች ማንበብ የሚፈልጉትን እየፃፈ መጠቀም ፈለገ።
ተስፋዬ ገብረአብ የተሻለ ጥቅም አገኝበታለሁ ብሎ በሚያስብበት ሁሉ የሚገኝ ግለሰብ ነው፤ ተስፋዬ ገብረአብ ከስነፅሁፍ ችሎታው ውጭ ምንም አይነት ሰውኛ ስብእና የሌለው ግለሰብ ነው።

ተስፋዬ ገብረአብን ከስነፅሁፍ ችሎታው ውጭ የማደንቅለት ነገር ቢኖር የኢትዮጵያ ፖለቲከኞችን ድክመት በደንብ ያውቃል በድክመታቸውም እንደፈለገው ይጫወትባቸዋል። ጎበዝ ፀሃፊ እንደነበረ ግን ሁሉም ያምናል!

ነፍስ ይማር!