Get Mystery Box with random crypto!

ስለድርድር አብዝቶ እየተወራ ነው፤ ግልፅ ሊሆንልኝና ማንም ሊያስረዳኝ ያልቻሉ ጉዳዮች አለ። 1, | Yihune Ephrem Kassahun

ስለድርድር አብዝቶ እየተወራ ነው፤ ግልፅ ሊሆንልኝና ማንም ሊያስረዳኝ ያልቻሉ ጉዳዮች አለ።

1, ብልፅግና ማንን ወክሎ ነው የሚደራደረው? የሞተው ድሃው ህዝብ ነው። ሚስቱና እህቱ የተደፈረችበት ሲቪሉ ሆኖ ሳለ ድርድርም ካስፈለገ ሀሳቡ በጦርነቱ ከተጎዱ ንፁሃን መምጣት እያለበት ብልፅግና ስለድርድር የሚያወራው ማንን ወክሎ ነው? እውነት ህዝቡ ላይ ስለደረሰው ግፍ ባለስልጣኖቻችን በትክክል ያውቃሉ?

2, ይሄ እኮ የብልፅግና ጉዳይ አይደለም፤ ጦርነቱ የኢትዮጵያና የትግሬ ወራሪ ቡድን እንጂ የብልፅግና እና የህወሃት አልነበረም። ህዝብ የሞተው ሀገር ለማዳን እንጂ የብልፅግና ባለስልጣናትን ስልጣን ለማራዘም አይደለም።

በመጨረሻም ድርድር ከተባለ በግሌ ልደግፈው የምችለው ድርድር ወልቃይትና ራያ ወደታሪካዊ ድንበራቸው ተጠቃለው የአማራ ንብረት ሲሆኑ፤ የህወሃት መሪዎች ለፈፀሙት ግፍ በህግ ለመጠየቅ ፍቃደኛ ሆነው እጃቸውን ሲሰጡና የትግሬ ወራሪ ቡድን ከአማራና ከአፋር ለዘረፋት ንብረት ተገቢውን ካሳ ሲከፍል ነው። ይህ ሳይፈፀም ቀርቶ ብልፅግና ወደድርድር ከገባ ምንም የሚያስፈራን ነገር ስለሌለ ዳግመኛ ትግላችንን እንጀምራለን። ድሮም ቢሆን ህወሃትን የታገልነው እኛ እንጂ ብልፅግና አይደለም።