Get Mystery Box with random crypto!

ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት

የቴሌግራም ቻናል አርማ eotcbook — ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት
የቴሌግራም ቻናል አርማ eotcbook — ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት
የሰርጥ አድራሻ: @eotcbook
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.40K
የሰርጥ መግለጫ

Coming Soon

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 32

2022-08-13 15:12:00 ለጀማሪ የግእዝ ቋንቋ ወዳጆች ሁሉ
ሰላም ጤና ይስጥልን ክቡራት እና ክቡራን የልሳነ ግእዝ ስልጠና በ @lesangeez128 እየሰጠን እንደሆነ ይታወቃል ሆኖም የጀማሪዎች ስልጠና በቅርቡ በonline ስለሚጀመር በዚህ #ዙር ላይ 20 ተማሪዎች ብቻ ስለሚካተቱ ከወዲሁ እራሳችሁን እንድታዘጋጁና በፍጥነት እንድትመዘገቡ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።
#ለሁለት ወር የመማሪያ ክፍያ 200ብር ብቻ ለበለጠ መረጃ በ @asrategabriel ያነጋግሩን አልያም በ +251914946589 ይደውሉልን።

ሰብሕዎ የልሳነ ግእዝ ማሰልጠኛ ተቋም
2.3K views12:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 21:01:55 በዚህ ክረምት የአብነት(የቆሎ) ትምህርቶችን ለመማር ፈልገው በአቅራቢያዎ መማርያ አጥተው ተቸግረዋል ?

ምንም አያስቡ በtelegram ብቻ ያለ ምንም ክፍያ በነጻ መጽሐፍትን በመጽሐፍ እና በድምፅ እያግኙ በግሩፕ እየተወያዩ ይማሩ
የአብነት ትምህርት ቤት
ውዳሴ ማርያም
የግእዝ ትምህርት
ወንጌለ ዮሐንስ
መዝሙረ ዳዊት
የዜማ ትምህርቶችን ጨምሮ
➦ ቅኔ ዘተዋነይ
➦ መጽሐፈ ሰዓታት
➦ ቅዳሴ ግዕዝ እና ዕዝል በዜማ
➦ውዳሴ ማርያም ዜማ
➦መልእክተ ዮሐንስ እና ሌሎችን ለመማር ይቀላቀሉን
45 views18:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 21:00:00 ልጄ ሆይ ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን

ሰው ከመሆንህ በፊት ዶክተር (ሐኪም) አትሁን፡፡
ሰው ከመሆንህ በፊት መሐንዲስ አትሁን፡፡
ሰው ከመሆንህ በፊት መምህር አትሁን፡፡
ሰው ከመሆንህ በፊት ሰባኪ አትሁን፡፡
ሰው ከመሆንህ በፊት አባ-ወራ አትሁን፡፡
ሰው ከመሆንህ በፊት መሪ፣ መካሪ፣ አውሪ፣ ዘማሪ፣ ጸሐፊ፣ ለጣፊ፣ ሰባኪ፣ ሹመኛ፣ ወገኛ.... ሌላም አትሁን በመጀመሪያ ግን ሰው ሁን፡፡

➥ ዓለም
➥ ኢትዮጵያ
➥ ቤተ ክርስቲያንም ያጣችው ይህንን ሁሉ አይደለም፡፡
ሰው የሚሆንላትን እንጂ፡፡ ይልቁንስ ከሁሉ በፊት ሰው ሁን፡፡ ሰው መሆን ከእነዚህ ሁሉ የተሻለ ማንነት ነውና፡፡

መጽሐፍስ ምን አለ "ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊትም ልጁ ሰለሞንን ሰው ሁን አለው፡፡" (1ነገ. 2፡3)

ሰው ወደ መሆን የሚመሩን ምክሮች የምናገኝበት ልዩ ቻናል

t.me/sew_hun_ke_sewm_sew_hun
t.me/sew_hun_ke_sewm_sew_hun
t.me/sew_hun_ke_sewm_sew_hun
67 views18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 17:06:44 በዚህ ክረምት የአብነት(የቆሎ) ትምህርቶችን ለመማር ፈልገው በአቅራቢያዎ መማርያ አጥተው ተቸግረዋል ?

ምንም አያስቡ በtelegram ብቻ ያለ ምንም ክፍያ በነጻ መጽሐፍትን በመጽሐፍ እና በድምፅ እያግኙ በግሩፕ እየተወያዩ ይማሩ
የአብነት ትምህርት ቤት
ውዳሴ ማርያም
የግእዝ ትምህርት
ወንጌለ ዮሐንስ
መዝሙረ ዳዊት
የዜማ ትምህርቶችን ጨምሮ
➦ ቅኔ ዘተዋነይ
➦ መጽሐፈ ሰዓታት
➦ ቅዳሴ ግዕዝ እና ዕዝል በዜማ
➦ውዳሴ ማርያም ዜማ
➦መልእክተ ዮሐንስ እና ሌሎችን ለመማር ይቀላቀሉን
335 views14:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 12:14:16 ሐምሌ 7

ቅድስት ሥላሴ በአብርሃም ቤት

ሐምሌ ሰባት በዚች ቀን ሥሉስ ቅዱስ በአብርሃም ቤት የተገለጠበት ነው፡፡ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስም በአካል በግብር ሦስትነት በባሕርይ በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ተገኙ፣ በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና፡፡ ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት ‹‹ቅድስት ሥላሴ›› እንላቸዋለን፡፡
የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም፡፡ የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል፣ በቤቱም መጥተው ያድራሉ፡፡ ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም፡፡ አባታችን ቅዱስ አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል፡፡


አባታችን አብርሃም በ99 ዓመቱ እናታችን ሣራ በ89 ዓመቷ ሥላሴን በድንኳናቸው አስተናገዱ፡፡ አብርሃም እግራቸውን አጠበ፡፡ በጀርባውም አዘላቸው፡፡ ምሳቸውንም አቀረበላቸው፡፡ እነርሱም እንደሚበሉ ሆኑለት፡፡ በዚያው ዕለትም የይስሃቅን መወለድ አበሠሩት፡፡ አብርሃም ከደግነቱና እንግዳ ከመውደዱ የተነሣ በተመሳቀለ ጎዳና ላይ ድንኳን ሠርቶ የወጣ የመረደውን፣ የመጣ የሄደውን ሁሉ እየተቀበለ እግዚአብሔርን እያገለገለ የሚኖር ጻድቅ ነበር፡፡
ለዚህም ነው አብርሃም በወይራ ግራር (በመምሬ) ዛፍ ሥር ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር አንድነቱን ሦስትነቱን የገለጠለት፡፡ ዘፍ 18፡1-25፣ ሮሜ 4፡-3፡፡ ቀትር ሰዓት ላይ በድንኳኑ ደጅ ተቀምጦ እንግዳ ሲጠብቅ እግዚአብሔር ታየው ተነጋገረው፡፡ አንገቱን ቀና አድርጎ ዐይኑን አራምዶ በተመለከተ ጊዜ እነሆ ሦስት ሰዎች ከበላዩ ባለ ተራራ ላይ ቆመው አያቸው፣ ወደ እርሱም ሲወርዱ አይቶ ፈጥኖ ሄዶ ከሰግደላቸው በኋላ ‹‹አቤቱ በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ ባሪያህን አትለፈኝ ብዬ እለምናለሁ፤ ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ…›› እያለ በትሕትና በመጋበዝ ወደ ድንኳኑ አስገብቶ በሚገባ ጋበዛቸው፡፡ ‹‹በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ›› ብሎ አንድነታቸውን፣ ‹‹ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ›› ብሎ የሦስትነታቸውን ምስጢር ገልጾአል፡፡

ያች ሥላሴ የገባባት የአብርሃም ድንኳን የእመቤታችን ምሳሌ ናት፡፡ ሥላሴ ወደ አብርሃም ድንኳን እንደገቡ ሁሉ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያምም አብ ለአጽንዖ፣ መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ፣ ወልድ በተለየ አካሉ ሥጋዋን ለመዋሐድ የማደራቸው ምሳሌ በመሆኑ አማናዊቷ የሥላሴ ማደሪያ የአብርሃም ድንኳን እመቤታችን ናት፡፡ ሉቃ 1፡35፡፡

እግዚአብሔርም አብርሃምን የዛሬ ዓመት ልጅ እንደሚወልድ ነግሮት በዓመቱ ይስሐቅን ወልዷል፡፡ ሁለቱ ሰዎች ከአብርሃም ድንኳን ወጥተው ወደ ሰዶም ወደ ገሞራ ሄዱ፣ አብርሃምም ይሸኛቸው ዘንድ አብሯቸው ሄደ፡፡ የሄዱትም ሁለቱ ሰዎች አብና መንፈስ ቅዱስ ናቸው፡፡ ነገር ግን አንዱ ወልድ በአብርሃም ቤት ቀርቷል ይኸውም ከቤተ አብርሃም ሰው እንደሚሆን ለማጠየቅ ነው፡፡ አብርሃምም ተመልሶ በእግዚአብሔር ፊት ቆመ፡፡
እግዚአብሔርም የሚሠራውን ሁሉ ከአብርሃም አይሠውርም ነበርና የሰዶምን የገሞራን ጥፋት ነገረው፡፡ አብርሃምም ይቅር እንዲላቸው አብዝቶ ለመነላቸው፡፡ ሥሉስ ቅዱስን የአብርሃሙ ሥላሴን በምግባር በሃይማኖት ሆነን እናገለግል ዘንድ የቅዱሳኑ ጸሎት ይርዳን!

የእኛንም ጓዳ ጎድጓዳ አጋዕዝት ዓለም ቅድስት ሥላሴ በምህረቱ የጎብኝልን አሜን

ምንጭመጽሐፈ ስንክሳር ዘተዋሕዶ


አቅራቢ ፦ ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት

የግእዝ ትምህርት በyoutube
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆  
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆
1.2K views09:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 12:14:05 ቅድስት ሥላሴ በአብርሃም ቤት

በቀትርም ጊዜ እርሱ በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር(ሥላሴ) በመምሬ የአድባር ዛፍ ተገለጠለት
እሱም ሮጦ እነሆ በፊትህ ሞገስን አግኝቼ እንደሆን ባሪያኽን አትለፈኝ ብሎ በቤቱ አስተናገደው የአንዱ እግር በታጠበ ጊዜ የሦስቱም እግር ታጥቦ ተገኘ።
ኦሪት ዘፍጥረት 18፥1-ፍጻሜ
የአብርሃም ደስታ የሆነው ይስሐቅም በዚህ ዕለት ተጸነሰ!!

አቅራቢ ፦ ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት

የግእዝ ትምህርት በyoutube
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆  
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆
925 views09:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 12:13:57 ሰይፈ ሥላሴ የአጋንንት ማሰሪያ ጸሎት

ይህ የጸሎት መጽሐፍ በጣም ብዙ ነፍሳትን በእሳት ከመብላት የታደገ ነው ምክንያቱም ኅቡዕ ምስጢራዊ በሆነው በሥላሴ ስም የሚጸለይ ስለሆነ
አሌፍ፣ቤት፣ጋሜል፣ዳሌጥ....እያለ የሚወርደው ስመ ኅቡዐት በዚህ ውስጥ ይገኛል ይህን መጽሐፍ ሁልጊዜ የሚጸልዩ ሰው ሥጋው ብትራብ ነፍሱ ሁሌም እንደጠገበች ትኖራለች።


አቅራቢ ፦ ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት

የግእዝ ትምህርት በyoutube
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆  
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆
816 views09:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 12:13:45 ዘለዓለማዊ የሥላሴ አናኗር

እግዚአብሔር በገናንነቱ ገናና ነው በቅድስናው የተቀደሰ ነው በምስጋናው የተመሰገነ ነው በክብሩም የከበረ ነው።
ቅዳሴ ኤጲፋንዮስ ቁጥር 3


አቅራቢ ፦ ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት

የግእዝ ትምህርት በyoutube
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆  
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆
909 views09:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 09:53:27 ክፍል አንድ - የግእዝ ፊደላት

1. የግእዝ ፊደላት እነማን ናቸው?
2. የፊደላቱ ታሪክ ምን ይመስላል?
3. ለአንድ "ድምጽ" ሁለት፣ ሦስት ፊደላት ለምን?
4. የግእዝ እና የአማርኛ ፊደላት አንድ ናቸው?


በዚህ ክፍል፣ እነዚህን እና መሰል ጥያቄዎችን ለመዳሰስ ተሞክሯል። ቪዲዮውን አዳምጡ፣ "Share" በማድረግ ለሌሎች አድርሱ፣ "Subscribe" በማድረግም በየሳምንቱ የሚለቀቁትን ክፍሎች ተከታተሉ።

መልካም ጊዜ









1.4K views06:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 14:00:25 የግእዝ ትምህርት ስልጠና በክፍያ መማር ለማንችለው በyoutube ትምህርት ይጀመር ብላችሁ ብዙዎቻቹ ሃሳብ ሰጣችዃል ይህን ሃሳብ በመቀበል ትምህርቱን ሀምሌ 6/11/2014 ዕሮብ ለመጀመር ወስነናል የምትማሩበት ቻናል










SUBSCRIBE በማድረግ ይጠብቁን
1.7K views11:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ