2022-08-29 10:49:21
የብርሃን እናት ትረካ ክፍል 4
➣
ጸሐፊ ፦ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ብዙ ሰዎች እግዚአብሔር ሰይጣንን ባይፈጥረው ኖሮ ይህ ሁሉ ነገር አይፈጠርም ብለው ይተክዛሉ
ሰይጣንን የፈጠረው እግዚአብሔር አይደለም!!
ታዲያ ማን ፈጠረው ልትሉ ትችላላችሁ ነገርግን ክፉውን ሰይጣን የፈጠረው ራሱ ሰይጣን ነው
እግዚአብሔር የፈጠረው ሰማልያል/ሳጥናኤል/ የተባለ እጅግ የተዋበ ሊጋርድ የተቀባ ኪሩብ ብሩህ የአጥቢያ ኮከብ የሆነ መልአክ ነበረ
እግዚአብሔር የፈጠረው በኤደን ገነት ነበረ የከበረ ዕንቁ ለብሶ በእግዚአብሔር ተራራ ይኖር ነበረ
➦
ከተፈጠርኽበት ቀን ጀምረህ በደል እስኪገኝብህ ድረስ በመንገድ ፍጹም ነበርክ ተብሎ እንደ ተጻፈው እግዚአብሔር የፈጠረው ንጹሕ መልአክ እንጂ ክፉውን ሰይጣንን አይደለም
ትንቢተ ሕዝቅኤል 28፥15አንዲት እናት ልጅ ወልዳ ልጇ ሲያድግ ልጁ ሌባ ቢሆን እናቲቱ ልጅ እንጂ ሌባ ወለደች ሊባል እንደማይገባው ሁሉ እግዚአብሔር ፍጹም የሆነውን መልአክ ፈጠረ እንጂ ለሰዎች ክስ የሚቆም የርሱን አምላክነት የሚሻ ክፉን ጠላት አልነበረም የፈጠረው
ከመጽሐፉ የተወሰደ
ትረካውን ለማግኘት
1.0K views07:49