Get Mystery Box with random crypto!

Empowering Next Generation - ENG

የቴሌግራም ቻናል አርማ engethiopia — Empowering Next Generation - ENG E
የቴሌግራም ቻናል አርማ engethiopia — Empowering Next Generation - ENG
የሰርጥ አድራሻ: @engethiopia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.38K
የሰርጥ መግለጫ

ENG is built by the youth for the youth.
#WeEmpowerGeneration
#WeRefusedToBeNormal
Cntct @EngEthiopia_Chat

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-05 08:05:20 ስለ ሰው ልቡና እና አዕምሮ ትተን ስለ አካሉ ብንመለከት እንኳን #ሪዛይለንስን በሚገርም ሁኔታ እናስተውላለን፡፡ እንግዲህ ቀና ለማለት ግን የተስፋን ጭላንጭል የሚያሳዩ በሮች፣ሃሳቦችና እገዛዎችን የሚያሳዩና የሚያደርጉ ሰዎች፡ሰው በአንድም በሌላም አጋጣሚ ሊያስፈልጉት ይችላል፡፡ ታዲያ የዚህ ፕሮጀክት የአተገባበር መንገድና የዚህ ስልተናችንም የመጀመሪያው መግቢያ ይኧው ነው፡፡

መልካም ቀን ዋሉ ያ’ገሬ ልጆች
#WeEmpowerGeneration
#WeRefuseToBeNormal
#PoweredByPlanInternational
225 viewsedited  05:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 08:01:52
#ጸጸትና_ምሬት
#ምስጋና_ተስፋና_አዲስ_ጅማሬ

በሚሉ ሃሳቦች ላይ የመጀመሪያውን ስልጠና በመስጠት የ #Women_Empowerment_Project ትግበራችን አካል የሆነውን #የDay1_Capacity_Building ስልጠናችንን ጀምረናል፡፡ በጣም ደስ የሚልና #ኳሊቲ_ታይም ነበር ያሳለፍነው በውይይታችን እና ስልጠናችን፡፡

ሰዎች በህይወት ጎዳና በሚያጋጥሟቸው አሰልቺ የመከራ ድግግሞሽ ሳቢያ ምናልባት በህይወት እያሉ ታሪካቸውን ግን እንደ ሞተ ሰው ታሪክ እያሰቡ ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ከንግዲ የማይለወጥ፣ተስፋ የሌለው፣ያበቃለት፣እንዲያ እንዲሆን ብቻ ተፈርዶ መዝገቡ የተመለሰና ከንግዲ ስለ መኖር አለመኖር እንጂ ስለ ለውጥ እንዳያስቡ ነገር ሁሉ ያከተመ፡፡

በለውጥ ውስጥ ካሉ ጥሩ ነገሮች አንዱና እጅግ አስደናቂው እውነት #ለውጥ_ከአስተሳሰብና_አተያይ ብቻ የሚጀምር መሆኑ ነው፡፡ ሰዎች ነገርን ካላዩበት አቅጣጫ አንድ ግዜ ዘወር ብለው ማየት ቢችሉ ብዙ ተስፋ፣እድል፣ምስጋና እና አዲስ ጅማሬ ሁሌም አለ፡፡

ብዙ የመከራን ዑደት፣ቀዝቃዛን ክረምት አሳልፎ ደግሞ እንደገና ካጎነበሱበት ቀና የማለት ህግ #Resilience ይባላል፡፡ ይህ በሁላችንም ውስጥ ያለ ድንቅ የተፈጥሮ ስጦታ ነው፡፡ በተደጋጋሚ ከባድ በሆነ ፈተና ውስጥ ሰው ሲያልፍ፣የፈተናው ቁመንትና ክብደት ደንደን/ረዘም ሲል #አቀርቅሮ_በመቆየት_ብዛት የጠፋ ሊመስል ይችላል እንጂ እንደምታውቁት #ህግ_አይጠፋም፡፡ ትንሽ ደግሞ ጸሃይ ብቅ ሲል ከንደገና መዘረጋጋት፣ማበብ፣ወደ ድሮው መልክ መመለስ ፍጥረት ውስጥ አለ #ይፈተናል_እንጂ በልዩ ልዩ ሁኔታዎች፡፡
233 views05:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 10:12:21 ለወረት ያህል ያልሆነ እና #በመክኒያትና_እውቀት_የደረጀ_የለውጥ_ርሃብ በወጣቱ ትውልድ ላይ ማምጣት፣ ለዚያም ርሃብ ምላሽ በሚሆን ሁለንተናዊ #3H(Head-knowledge, Heart-attitude and hand-practice) መንገድ #የወጣቶችን_ላይፍ_ስታይል_በቀስታ_ቻሌንጅ ማድረግና #በትክክለኛ_ሂደት_ያለፈ #በቀላሉ_የማይቀለበስ ለውጥን በወጣቱ ዘንድ ማዛመት። #ቀላል_አይደለም_ግን_ይቻላል፡፡

ታዲያ ምንም እንኳን የዚህን ስራ #ከመሬት_በላይ_ቪዢብሊ ሊኖረው የሚችለውን #የአካሄድ_እሳቤ_ሰመሪ እንዲህ ባለ ሰውኛ መንገድ ብናስቀምጥም፤ ነገር ግን ድርጅታችን ያለ ሃይማኖት ልዩነት

#የነገሮች_ሁሉ_አስጀማሪና_አስፈጻሚ ማንም ቢደክመው እርሱየማይደክመው #የትጋትና_የለውጥ_አድናቂ ለሰው ልጆች ሁሉ እኩል መልካም የሆነና የሚያስብ #የትኛውንም_ውስብስብ_ነገር_ለመፍታት_ሊሚቴሽን_የሌለበት ግለሰቦች ትውልድ ሰዎች ህዝቦችን ለበጎ ነገር ሲነሱ አይቶ መርዳት ደስ የሚለው #ኢማጂኔሽን_ያልሆነ_ነገር_ግን_ያለ_የማሚያይ_የሚሰማ ከመክኒያት ያለፈ በጎነት ያለውና ሁሉን ማደረግ የሚችል አንድ አምላክ/ፈጣሪ እንዳለ ያምናል፡፡

ስለሆነም አምላክ ከላይ ለጠቀሳችሁት ሃሳብ እንዲረዳችሁ/ዳን በራሴ ሃይማኖት ወደ ፈጣሪ በመለመን አብሬያችሁ መቆም እችላለሁ ለምትሉ ሁሉ እባካችሁ #ከዛሬ_ጀምሮ እስከ #መስከረም_1 ድረስ ለሚቆይ የጾሎት ጥሪ #ተቀላቀሉን እና እንደተቀላቀላችሁንም አሳውቁን፡፡
230 viewsedited  07:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 10:10:06
የENG ታላቅ የጽሎት ጥሪ!
ENG's great call of prayer!

ድርጅታችን #ኢምፓወሪንግ_ኔክስት_ጀነሬሽን በታማኝነት ወጣቶችን በሁለንተናዊ(በዋናነት በጤና፣በሰላም፣በግል ልዕቀት እና በጎ ፍቃድ) መንገድ ሊያገለግል፣ #በቅድሚያ አንደ ወጣቱ ትውልድ #ቀጥሎም እንደ ሃገር #ለውጥን_መርህና_መሰረት_ባለው አግባብ ለማምጣት የሚተጋ ተቋም ነው፡፡

#ቴክኖሎጂው_የደረሰበት ልዕቀት በዓለም ላይ #አይሞከሩም_የሚባሉ_ለውጦችን እንኳን ሳይቀር በሰዎች #ሰውነት_ላይ ከሳምንታትና ወራት እምብዛም ባልዘለለ የህክምና ክትትልና ሌሎች መንገዶች ማምጣትን አስችሏል፡፡ ግዜው #ለመሆን እና #ለመቀየር አመታት የሚፈጁ ጉዳዮችን በቀናትና ሳምንታት እድሜ ዕውን እንዲሆኑ አስችሏል፡፡

#ከውስጥ_የሚነሳ_የትውልድ_ለውጥ_ግን_አካሄዱ_ለብቻ_ነው።

የትውልድን ሁኔታ #በጥልቀት_መመርመር፣ጠንካራውን እና ደካማውን ጎን #በትኩረት_ማጤን፣ከዚያም ሁኔታ ጋር ተቀራራቢ በሆነ መንገድ የተቃኘና ተነጣጥለን የማንተገብረው አንድ ሰፋ ያለ የመፍትሄ ሃሳብና መንገድ መቅረጽ፣ #ግልጽና_ፕሮፋውንድ የሆነ #ቲዎሪ_ኦፍ_ቼንጅን በማስቀመጥ የትውልድን #ቫሊው_ሲስተምና #ኖርም ፖዘቲቭሊ #ቻሌንጅ ማድረግ፡፡ በመጨረሻም #ከአስተሳሰብ_የሚነሳ በብዙ መንገድ #የሚተገበር እና #ራሱን_ማኒፌስት የሚያደርግ አካሄድ #የለውጥ_ሌየሮቹን_ሳያዛንፉ እየደረደሩ ትውልድን መቀየር። #ቀላል_አይደለም_ግን_ይቻላል፡፡
227 views07:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 13:02:48 እንደምታስተውሉት አንዳንድ ትምህርቶችን በልጅነት እድሜ የተማርነው #የልጅ_ትምህርት ስለሆኑ ሳይሆን #መሰረታዊ ስለሆኑ ነው፡፡ እውነት እንነጋገር ከተባለም ሰው #ተሸናንፎ ሳይሆን #ተግባብቶ አብሮ መኖር ካለበት #የእውነት_መግባባት_የሚሆንለት_በመሰረታዊ_ነገሮች ላይ ብቻ ነው፡፡ #በሁሉም_ነገር_ለመግባባት ማሰብ ብዙ ግዜ እንዲያውም የተጨማሪ አለመግባባት ምንጭ ይሆናል፡፡ መልካሙ ዜና ግን እነዚያ ጥቂት መሰረታዊ ነገሮች ናቸው መሰረታዊ የውጤት ልዩነት የሚያመጡት፡፡
265 viewsedited  10:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 12:57:23
ትላንትና #ሰላም_በሚል_ርዕስ ላይ አንድ በአብዛኛው ወጣቶች በሚሳተፉበት የስልጠና መርሃግብር ላይ ተጋብዤ ስልጠና እየሰጠሁ ነበር፡፡ ታዲያ እያንዳንዱ ተሳታፊ የነበረው ንቃትና ተነሳሽነት እጅግ ደስ የሚል እና ተስፋን የሰጠኝም ነበር፡፡ ታዲያ #ሲምፕል በሆኑ መሰረታዊ ሃሳቦች ላይ የሚያጠነጥን #ትሬኒንግ ልሰጥ በተገኘሁበት #ፕሮፌሰር_ዲባባ የተሰኙ በሰላም ዙሪያ ብዙ ርቀት ሄደው ያጠኑ ድንቅ ሰው ጋር ተገናኘሁና፤ ከነጭራሹ “በቀጣይ ሃሳቦቹን በጥልቀት የምታስደግፍበት” ይሁንህ ሲሉ እጅግ ብዙ ዋጋ የሚያወጡና ተደክሞባቸው የተገኙ #ማቴሪያሎችን ለኔና ለድርጅቴ አበረከቱልን፡፡

መቼም ሰዎች ወደድንም ጠላንም በህይወት ስንኖር በአንድ ሲስተም ውስጥ ወይ #የመፍሄው_አካል ወይ #የችግሩ_አካል ካልሆነም #የችግሩ_ሰለባ ሆነን ልንኖር የግድ ነው፡፡ አንዳንዴ ደግሞ የማይጋጩ ሁለት ቤቶች ውስጥ እንደሁኔታው ልንኖር እንችላለን፡፡ በዚህ አጋጣሚ እንደ ግለሰብ ከየትኛው ወገን ነኝ ብለው ያስባሉ? ከሆነስ ለምን?

ከሚያመጣው ተቀራራቢ ወጤት አንጻር ሰዎች #በአመጽና_ትውድን_ሰላም_በመንሳት አካሄድ ውስጥ በዋናነው በሁለት መንገድ ይሳተፋሉ፡፡ #1ኛው በቀጥታ እጃቸውን ሰንዝረው በአመጽ ውስጥ በማስገባት፡፡ 2ኛው #በተለያየ_መልክ_ራሱን_በሚገልጥ_ኢግኖራንስ፡፡ በጉዳዩ ላይ #እንደማያገባው_ሰው_አክት ለማድረግ በመሞከር፡፡ አብዛኛው የኔ ቢጤ ሰው #በ2ኛው መንገድ ነው የሚሳተፈው ብዬ አስባለሁ፡፡

ታዲያ ግን ከሰላም ጋር በተያያዘም ብቻ ሳይሆን በብዙ #አስፔክት_ኦፍ_ላይፍ #ኢግኖራንስ በጣም አደገኛ ነው፡፡ #ሰዎች_ለማወቅና_ጥቂት_አክት_ለማድረግ ከሚከፍሉት ዋጋ አንጻር #ባለማወቅና_ጥቂት_አክት_ባለማድረግ የሚከፍሉት ዋጋ ብዙና አሳዛኝ ነው፡፡ምናልባት ግን እርሶስ በየትኛው መንገድ ተሳታፊ ኖት? ከሆነስ ለምን?
240 viewsedited  09:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 14:50:39
The second "Promoting Peace, Protecting the Environment" conference is hosted in Ethiopia by the FDRE Ministry of Women and Social Affairs, East African Standby Force, and the FDRE Ministry of Defense jointly.

Youth leaders from East Africa have met at their second home. overviews of the continental framework on youth, peace and security & gender in matters of peace and security have taken the explanatory part.

No one could possibly appreciate peace more than those of us struggling as African youths. What a fantastic opportunity to make a difference, to exchange visions, to debate ideas, and most importantly, to strengthen brothers and sisterhood throughout the course of those two days.

Indeed, we are the youth leaders who will be steering Africa's destiny by triangulating all the potential outcomes.

#Eng is honored to be one of the youth-led organizations to take a part.

#Africanyouthleaders
#EmpoweingNextGeneration
#FutureAfrica
#peacebuilding
#Environment
527 views11:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ