Get Mystery Box with random crypto!

የENG ታላቅ የጽሎት ጥሪ! ENG's great call of prayer! ድርጅታችን #ኢምፓ | Empowering Next Generation - ENG

የENG ታላቅ የጽሎት ጥሪ!
ENG's great call of prayer!

ድርጅታችን #ኢምፓወሪንግ_ኔክስት_ጀነሬሽን በታማኝነት ወጣቶችን በሁለንተናዊ(በዋናነት በጤና፣በሰላም፣በግል ልዕቀት እና በጎ ፍቃድ) መንገድ ሊያገለግል፣ #በቅድሚያ አንደ ወጣቱ ትውልድ #ቀጥሎም እንደ ሃገር #ለውጥን_መርህና_መሰረት_ባለው አግባብ ለማምጣት የሚተጋ ተቋም ነው፡፡

#ቴክኖሎጂው_የደረሰበት ልዕቀት በዓለም ላይ #አይሞከሩም_የሚባሉ_ለውጦችን እንኳን ሳይቀር በሰዎች #ሰውነት_ላይ ከሳምንታትና ወራት እምብዛም ባልዘለለ የህክምና ክትትልና ሌሎች መንገዶች ማምጣትን አስችሏል፡፡ ግዜው #ለመሆን እና #ለመቀየር አመታት የሚፈጁ ጉዳዮችን በቀናትና ሳምንታት እድሜ ዕውን እንዲሆኑ አስችሏል፡፡

#ከውስጥ_የሚነሳ_የትውልድ_ለውጥ_ግን_አካሄዱ_ለብቻ_ነው።

የትውልድን ሁኔታ #በጥልቀት_መመርመር፣ጠንካራውን እና ደካማውን ጎን #በትኩረት_ማጤን፣ከዚያም ሁኔታ ጋር ተቀራራቢ በሆነ መንገድ የተቃኘና ተነጣጥለን የማንተገብረው አንድ ሰፋ ያለ የመፍትሄ ሃሳብና መንገድ መቅረጽ፣ #ግልጽና_ፕሮፋውንድ የሆነ #ቲዎሪ_ኦፍ_ቼንጅን በማስቀመጥ የትውልድን #ቫሊው_ሲስተምና #ኖርም ፖዘቲቭሊ #ቻሌንጅ ማድረግ፡፡ በመጨረሻም #ከአስተሳሰብ_የሚነሳ በብዙ መንገድ #የሚተገበር እና #ራሱን_ማኒፌስት የሚያደርግ አካሄድ #የለውጥ_ሌየሮቹን_ሳያዛንፉ እየደረደሩ ትውልድን መቀየር። #ቀላል_አይደለም_ግን_ይቻላል፡፡