Get Mystery Box with random crypto!

ይናፍቁን ይሆን ''''''''''''''''''''''' ለቤት ስራ ለአሳይመንቱ መ | እንደመሠለን🥴😂❤️

ይናፍቁን ይሆን
"""""""""""""""""""""""

ለቤት ስራ ለአሳይመንቱ መሮጥ ቀረ ፣
አይባልም ዛሬ እንትና ተባረረ ፣
የቅዳሜ ቲቶር ፈተና ኩረጃ ፣
ያ ፕረዘንቴሽን የሚባለው ፍርጃ ፣
በጠዋት ሰልፍ ወጥቶ ማለት የዜግነት ፣
x ን ማፈላለግ ማትስ የሚባል ትምህርት ።
ቀረ
አረፈድኩኝ ብሎ ቅያስ መሯሯጡ ፣
ከትምሮ ቤት መልስ በረዶ መምጠጡ ፣
የጀማው ጨዋታ ጎምቤ መጠባበስ ፣
በጠዋት ተነስቶ ዩኒፎርምን መልበስ ፣
አርብን ቀን መናፈቅ ሰኞን ደሞ መርገም ፣
የክፍለ ጊዜውን ደብተሮች መሸከም ።
ቀረ
የረባሹ ፊርማ የወላጅ ስብሰባ ፣
የብሎኩ ፎርፌ የሚዲያው ዘገባ ፣
ዳይሬክተሩ መጥቶ አትገባም ሂድ ግባ ፣
መባባሉ ቀረ
ደብተር መሰራረቅ ለማርክ መፎካከር ፣
የፈተና ሰሞን ካሮት በልቶ ማደር ፣
ለ ሰኔ ሰላሳ ሰነፉ ሲያለቅስ ጎበዙ ሲሸለም ፣
አርፋጅ ላይ ተይዞ መገረፉ የለም ፣
ፀጉርን ደምድሞ መምህር መጋተት ፣
ደሞ ካልተሳካ በጨዋ በር መግባት ፣
ይብስ አልሆን ካለ ክላሱንም መቅጣት ።
ቀረ
በጀማ ደይ ማክበር በጀማ መጣላት ፣
ክፍል ተቀምጦ ቡድን ስራ መስራት ፣
ትርፍ እስኪርቢቶ የያዘ ብሎ መጠየቁ ፣
የቡድን ጨዋታ የአብሮነት ሳቁ ።
ቀረ
ቧንቧ ጋ ደርሰን እንምጣ ብሎ መለማመጥ ፣
መምህር መጣ አልመጣ እያሉ መደንገጥ ፣
ያ ጉልቤው ተማሪ ክላስ ሚቀውጠው ፣
ያ ጅሉ ተማሪ ዝምብሎ ሚስቀው ፣
ያቺ ቆንጅዬ ልጅ ሁሉም የሚያፈቅሯት ፣
ያቺ ምላሳሟ ሁሉም የሚሰድባት ፣
ያ ቀዳዳው ጀለስ ወሬ ማያልቅበት ፣
ያ ጢባራሙ ልጅ ሴቶች ሚባሉበት ፣
እነዛ ዥልጦች ልፊያ የሚወዱት ፣
ዴክስ እየዘለሉ ክፍሉን የሚያቦኑት ፣
ያ አይናፋሩ ልጅ ሴቶች ሚስቁበት ፣
እንረሳው ይሆን ? ሁሉን እንደዘበት ።

ክላስ እየቀጡ
ሰው አየኝ አላየኝ እያሉ መሳቀቅ ፣
የሰው ምሳ ሰርቆ ለመብላት መደበቅ ፣
መምህር ሲገባ ብላክቦርድ አጥፍቶ ፣
በዛው መቀየሱ ላራግፍ ብሎ ወጥቶ ፣
የክፍል ሀላፊው እንዲያምነን ለማድረግ ፣
ለቀረንበት ቀን ምክንያት ማፈላለግ ፣
የውሸት ማልቀሱ ዘመድ ባዳ መግደል ፣
ፕላስተር ለጥፎ
ወይ ፋሻ ጠቅልሎ የተጎዳ መምሰል ።
ቀረ
ወላጅ አምጡ የለ ፣
ኢንኮምፕሌት የለ ፣
ያሁሉ አለፈ የማያልፍ ምን አለ ፣
አይ የዘመን ክፋት ፣
ይናፍቁን ይሆን እነዚህ አመታት ።

#በረከትዘውዱ