Get Mystery Box with random crypto!

ሰዓትን ደቂቃ አርዝሞ የፈጠረው ካንቺ ሲያገናኘኝ ለምን አሳጠረው? ይሄን ምጠይቀው አንዱን ፈጣሪን | እንደመሠለን🥴😂❤️



ሰዓትን ደቂቃ አርዝሞ የፈጠረው
ካንቺ ሲያገናኘኝ ለምን አሳጠረው?
ይሄን ምጠይቀው አንዱን ፈጣሪን ነው?
አንቺን ያገናኘኝ ምክንያት ቢኖረው ነው


ከዛስ አትዪኝም...


ልክ አንቺን ሳገኝሽ ሰዓቱ ይሮጣል
ዝምተኛውን ልጅ ወረኛ አርገሽኛል
ብዬ አልዋሽሽም ግን...
በፊት ከነበርኩበት አሁን ብሶብኛል


ከዛስ አትዪኝም...


እድለኛ እኮነኝ እያልኩ አወራለው
ለምን ይሆን እንዲ የምታስብልኝ እያልኩ አስባለው


ከዛስ አትዪኝም...


ወደላይ አንጋጥጬ ፈጣሪን እያየሁ
የውስጧን ባላውቅም ከልቧ ከሆነ የምታስብልኝ
መቼም አትቀይራት እንዳንሰለቻች አንተው ጠብቅልኝ
እያልኩኝ ፀለይኩኝ


ከዛስ አትዪኝም...


ብትወጂኝ ባትወጂኝ እኔ እወድሻለሁ፦
አንቺን ስለሰጠኝ አመሰግናለሁ


ከዛስ እንዳትዪኝ