Get Mystery Box with random crypto!

አብሰራ ገብርኤል ለማርያም

የቴሌግራም ቻናል አርማ enatachn_mareyam — አብሰራ ገብርኤል ለማርያም
የቴሌግራም ቻናል አርማ enatachn_mareyam — አብሰራ ገብርኤል ለማርያም
የሰርጥ አድራሻ: @enatachn_mareyam
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.78K
የሰርጥ መግለጫ

እኔ #በእግዚአብሔር_ፊት የምቆመው #ገብርኤል_ነኝ
በቻናላናችን የሚሰጡ ነገሮች
መንፈሳዊ ትምህርቶች
መንፈሳዊ ምክሮች
መንፈሳዊ መዝሙር
መንፈሳዊ ጥያቄዎች
መንፈሳዊ ስዕልዎች
በየለቱ ስንክሳር
አስተያየት ካላቹ 👇👇👇
https://t.me/Enatemareyam21
https://t.me/Enatemareyam21

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-24 21:32:51 #ወዳጄ!! ታሪክህን የሚቀይረው ከፈጣሪ ቀጥሎ ያንተ ቆራጥነት ነው! ከሰዎች ብዙ አጠብቅ! ሰዎችን እንዳስቀመጥክ አታገኛቸውም ጊዜና ሁኔታ ይቀይራቸዋል ። ለራሴ ያለሁት እኔ ነኝ ማለት ስትጀምር በአመለካከት ከፍ ማለት ትጀምራለህ ።
674 viewsብላቴና ዳዊት, edited  18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 07:59:52
#ወዳጄ__ሆይ…. ሠው ለምን ከዳኝ፣ ለምን እኔ እንደወደድኩት እሱም አልወደደኝም ብለህ አትብሠልሠል! እንዴት እኔ ለክፉ ቀኑ የደረስኩለት ሠው በጨለማው የህይወት ጊዜዬ ሸሸኝ ብለህ አትጨናነቅ፡፡ ለምንድነው እኔ ሳከብረው ያላከበረኝ ብለህም በሃሳብ አትናወዝ! ሲያከብሩት የሚያከብር፣ ሲወዱት የሚወድ፣ ክፉ ቀንን አብሮ የሚያሳልፍ ወዳጅ፣ ዘመድ፣ የቅርብ ሠው ማግኘት ብርቅ ሆኗልና ያን ያህል አይድነቅህ! አንተ ግን ከደግነትህ፣ ከመልካምነትህ፣ ከቅንንነትህ ወለምዘለም አትበል፡፡ ሠዎችን በነፃ ከመውደድ ውልፍት አትበል፡፡ ባይወዱህም ውደዳቸው፣ ቢጠሉህም ቅን አስብላቸው፡፡ መቼም ቢሆን ክፉን በክፉ አታሸንፍ! ክፋት ማሠብ ቀላል ነው፤ ከባዱ ነገር የከፉብህን ሠዎች #በፍቅር ማቀፍ መቻል ነው፡፡

#መልካም__ቀን

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ ለማግኘት //

@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
1.3K viewsብላቴና ዳዊት, 04:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 08:34:25
#መልካም_አድርግና_እርሳው...

ስላደርግኸው ስለዚህ ነገር ማንኛውንም ዓይነት
#ውዳሴም ሆነ ሙገሳ አትሻ። መልካም ያደረግህለት ሰው አንተ እንዳደረግህለት ለአንተ መልካም የሆነውን አጸፋ እንዲመልስልህ ወይም አንተ አንደተንከባከብከው እርሱም #እንዲንከባከብህ አትጠብቅ።

#መልካም ስታደርግ በምላሹ #መልካም ዋጋ አገኛለሁ ብለህ በመጠበቅ ላለመሆኑ እርግጠኛ ሁን! መልካም የምታደርገው መልካም ማድርግን ስለምትወድ ወይም መልካም ከማድረግ መከልከል ስለማትችል ለመሆኑ እርግጠኛ ሁን። መልካም መሆን በውስጥህ ያለ ጠባይ ይሁን። መልካም ጠባይ እንደ መተንፈስ ምንም ዓይነት ጥረት የማይጠይቅ ግብታዊ ነገር ይሁን።

እንዲህ ያለውን ነገር የምትረሳው ከሆነ እግዚአብሔር በዚህ ምድርም ሆነ በሚመጣው ዓለም ያስታውስሃል። መልካም ማድረግህን የምታስታውሰውና በውስጥህ ይዘኸው የምትቆይ ከሆነ ግን ታጣዋለህ።

#መልካም__ቀን

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ ለማግኘት //

@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
1.2K viewsብላቴና ዳዊት, 05:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 21:38:45
#ትንሳኤሽ_ሳይሆን_ሞትሽ_ይደንቀናል!

"የህይወት እናት
#ድንግል_ማርያም ሆይ ትንሳኤሽ ሳይሆን ሞትሽ ይደንቀኛል፤ እርገትሽ ሳይሆን ወደ መቃብር መውረድሽ ይገርመኛል። የብርሃን እናት ድንግል ማርያም ሆይ #ትወጂኛለሽን? ብዬ አልጠይቅሽም! ፍቅርን የወለድሽ አንቺ ለዓለሙ ሁሉ ፍቅርሽ የበዛ ነውና፤ #አትናፍቂኝምን? ብዬም አልጠይቅሽም! ዘወትር እኔን ለመጠበቅ ከጎኔ እንደማትለይ አውቃለሁኝና።

#እመቤቴ_ሆይ፦ እንደ ቶማስ አይሽ ዘንድ በእጅጉ እጓጓለሁ የቶማስ ንፅህናና ቅድስና ግን የለኝም፤ እንደ ዮሐንስ ከጎንሽ ልሆን እጓጓለሁ፤ የዮሐንስ ፀጋ ግን የለኝምና !

#እናቴ_ሆይ፦ እንደ ኤልሳዕ የልቦናዬ ዓይን በርቶ ሰማያዊ ክብርሽን ላይ አልተቻለኝምና ፤ አዝናለሁ! ኤልሳዕ በፀሎት ኃይል የግያዝን ዓይን እንዳበራ፤ አንቺም ዓይኔን ታበሪልኝ ዘንድ ኃይልሽን በእኔ ላይ አበርቺ፡፡

#ድንግል_ሆይ፦ ይህን የምል የእምነት ማረጋገጫ ፈልጌ አይደለም፤ በልጅሽ መሠረትነት የታነፅኩኝ፤ በልጅሽ ስምም የተጠመቅኩኝ ነኝና፤ ነገር ግን ዘወትር #ስለምትናፍቂኝ ይህን አልኩኝ። ስለዚህም ነይ ነይ #እመይ_ማርያም እያልኩኝ እንደ #እናቶቼም እለምንሻለሁ፡፡ የብርሃን ልብስሽን ለብሰሽ ነይ!! የክብር አክሊልሽን ደፍተሽ ነይ አንቺ ሱላማጢስ ሆይ ነይ እናይሽ ዘንድ ነይ፡፡"

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
•➢ ሼር // SHARE

#ለመቀላቀል
@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
1.2K viewsብላቴና ዳዊት, 18:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 07:50:42
#ነሐሴ_፲፮

#እንኳን_እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም የዕርገት በዓል አደረሳችሁ ።

#ዕርገተ_ድንግል_ማርያም °

#ሞት_ለመዋቲ_ይደሉ_ሞታ_ለማርያም የዐጽብ ለኲሉ>>
#ሞትማ_ማናቸውም_ሰው ሁሉ የተገባ ነውነ #የማርያም_ሞት ግን ሁሉን #ያስደንቃል፡፡» ቅዱስ ያሬድ፡፡

‹‹አቤቱ ወደ እረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦት፡፡›› ቅዱስ ዳዊት፡፡
‹‹ወዳጄ ሆይ ተነሺ፣ ውበቴ ሆይ ነይ!››
ጠቢቡ ሰሎሞን፡፡

#እንኳን_ለዚህች_እለት_አደረሳችሁ

ይህች ዕለት እጅጉን ታላቅና ክብርት ናት፤ ምክንያቱም
#የድንግል_ማርያም #ሥጋዋ_ተነስቶ አርጎባታልና ።ድንግል ማርያም ዐረገች ስንል እንደ እንግዳ ደርሶ እንደ ውሃ ፈሶ ወይም በአጋጣሚ የተደረገ አይደለም ። ጥንቱን በአምላክ ልቡናዊ ይታስባል ኃላም ትንቢት ተነግሮለት ነው ። ከነገር ሁሉ በፊት እግዚአብሔር እናቱን ያውቃት ነበር እና ነው ።
ከአዳም አንስቶ ለአምስት ሺህ አምስት መቶ ዓመታት አበው :_ነቢያትና:_ካህናት ስለ
#ድንግል_ማርያም ብዙ ሐረገ ትንቢቶችን ተናገሩ ።

መዳኛቸውን ሱባኤ ቆጠሩላት ምሳሌም መሠሉላት ከሩቅ ዘመን ሆነውም ሊያገኟት እየተመኙ እጅ ነሷት

እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ እርገቷ በሰላም አደረሳችሁ

#መልካም__በዓል

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
•➢ ሼር // SHARE

#ለመቀላቀል
@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
1.3K viewsብላቴና ዳዊት, 04:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 22:03:08
#በረከት_ይድረሰን

ፍቅርሽን ተርበን
#ፍልሰትሽን አስበን
ውዳሴሽን ደግመን
ቅዳሴሽን ሰምተን
ጸበልሽን ጠጥተን
እምነት ተቀብተን
#በረከትን ሽተን
ከልጅ እስከ አዋቂ ፥ ከሊቅ እስከ ደቂቅ
በፊትሽ
#ለምንሰግድ ፥ በፊትሽ #ለምንወድቅ...
#ለእኛ_ለልጆሽ
ከጉስቁልና አኗኗር ፥ ፍልሰትሽ ያፍልሰን
የትንሣኤሽ በረከት ፥ ከኃጢአት ሞት ያንሣን ከምድራዊ ሃሳብ ፥ ፍፁም ተለይተን
#በዕርገትሽ_እናርግ#በረከት ይድረሰን።

በዓለን የሰላም የፍቅር የፅድቅና የበረከት ያድርግልን።
#በትንሣኤዋ#በዕርገቷ#ትንሣኤ ልቡና ዕርገተ ህሊናን ያድለን። አሜን።

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
•➢ ሼር // SHARE

#ለመቀላቀል
@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
1.2K viewsብላቴና ዳዊት, 19:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 07:38:24
"ምንተ ንነግረኪ ውስተ ልብነ ዘሀሎ
እስመ አንቲ ተአምሪ ኀዘንነ ኩሎ"

#በልባችን_ካለው_ምኑን_እንነግርሻለን
አንቺው ኀዘናችንን ሁሉ ታውቂዋለሽ"

#ጾመ_ፍልሰታ ሐዋርያት የእመቤታችንን ሥጋዋን ሽተው የጾሙት ጾም በኁዋላም ትንሣኤዋን ያዩበት ጾም ነው::
ዘንድሮ የምንጾመው ከብዙ ብሶትና ኀዘን ጋር ነው::
#እመቤታችንን_ሐዋርያት ሥጋዋን ይዘው ሊቀብሩ ባሉ ጊዜ አይሁድ የላኩት አንድ ታውፋንያን ነበር:: ዘንድሮ የሰማዕታት አስከሬን ላይ የሚሆነው ታውፋንያ ምን አደረገ የሚያስብል ሆነብን:: ወላዲተ አምላክ የልባችንን ኀዘን ለማን እንነግራለን? ከአንቺ በቀር ማን ያጽናናል?
ዘንድሮ ፍልሰታን ከሞቀ ቤታቸው ፈልሰው በደጅ ፈስሰው
በዚህ አጥንት የሚሰብር ብርድ ከደጅ የሚያድሩ ሱባኤያተኞችሽን ተመልከቺ:: በልጅሽ ያመኑ ባለማተቦችሽን
#እመብርሃን_ሆይ ተመልከቺ::
ከአንቺ በቀር የልባችን ኀዘን ለማን እንነግራለን?
ሱባኤያችንን የኢትዮጵያ ሰላም የቤተ ክርስቲያን ዕረፍት የኃጢአታችን ሥርየት ሱባኤ አድርጊልን::
#በጾመ_ፍልሰታ_ንስሓ እንግባ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን እንቀበል::

#መልካም_ዕለተ_ሰንበት

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
•➢ ሼር // SHARE

#ለመቀላቀል
@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
1.5K viewsብላቴና ዳዊት, 04:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 21:05:51
@Bini photographer

Join share

https://t.me/bini_image
https://t.me/bini_image
501 viewsብላቴና ዳዊት, 18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 08:26:56
​​#መነኮሳት_በእንተ_ጾም

"
#ትጾማለህ? ጾምህ ፍጹም እንዲሆንልህ የተራቡትን #አብላክ፥ ለተጠሙት #አጠጣክ፥ የታመሙ ወገኖችን #ጎበኘክ፥ የታሠሩ ወገኖችን #ጠየክ፥ የሚያለቅሱትንና የተበደሉ ወገኖችን #አጽናናክ፥ ምህረትን #አድርግ፥ ትሁት #ሁን፥ የተረጋጋህ #ሁን፥ ይቅር #በል፥ እውነትን #ተናገር፥ ሃይማኖተኛ #ሁን። እንዲህ ከሆነ #እግዚአብሔር ጾምህን ይቀበል ይሆናል። #የንስሐን ፍሬም ገንዘብ ማድረግ ይቻልሃል። #ጾም_የነፍስ መድኃኒት ነውና።"

#ታላቁ_ቅዱስ_ባስልዮስ_ዘቂሳሪያ

#ሰናይ____ቅዳሜ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
•➢ ሼር // SHARE

#ለመቀላቀል
@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
1.4K viewsብላቴና ዳዊት, 05:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 21:07:06
....“ሆያ ሆዬ ሆ
....“እዛ ማዶ ጭስ ይጨሳል ……ሆ
.....አጋፋሪ ይደግሳል ……..ሆ
.....ያችን ድግስ ውጬ ውጬ …….ሆ
.....ከድንክ አልጋ ተገልብጬ ……..ሆ
.....ያቺ ድንክ አልጋ አመለኛ …….ሆ
.....አላንድ ሰው አታስተኛ” …….ሆ
ተብሎ ይጨፈራል፡፡ ይኸውም የእስራኤልን ታሪክ ያዘለ ሲኾን “ሆያ ሆዬ ሆ” ማለት ጌታው ሆዬ እሜቴ ሆዬ ብሎ አክብሮትን መግለጽ ነው፡፡

“እዛ ማዶ ጭስ ይጨሳል ……ሆ አጋፋሪ ይደግሳል ……..ሆ ማለት እስራኤል ከግብጽ ባርነት በወጡ ጊዜ በጭስ የተመሰለ ጉምና ደመና እየመራቸው ቅዱስ ሚካኤል መና እያወረደላቸው ስለወጡ ጭስ የተባለው የደመናው ምሳሌ፤ አጋፋሪ የተባለው ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡

ያችን ድግስ ውጬ ውጬ …….ሆ ከድንክ አልጋ ተገልብጬ ……..ሆ ማለት በድግስ የተመሰለውን መና እስራኤል 40 ዘመን በአጋፋሪ በተመሰለው በቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነት እየተመገቡ በድንክ አልጋ የተመሰለችውን ኢየሩሳሌምን መውረሳቸውን የሚያመለክት ነው፡፡

“ያቺ ድንክ አልጋ አመለኛ …….ሆ አላንድ ሰው አታስተኛ” …….ሆ” መባሉ እስራኤል ከግብጽ ሲወጡ 600,000 ሆነው ሲሆን ነገር ግን ሁሉም በምድረ በዳ አልቀው ኢየሩሳሌምን የወረሳት አንድ ኢያሱና አንድ ካሌብ ነው ለማለት ነው፡፡
[በደብረ ታቦር ላይ ብርሃኑን የገለጠው አምላካችን ክርስቶስ ምስጋና ይግባው]፡፡
[መልካም በዓል]
መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
•➢ ሼር // SHARE

#ለመቀላቀል
@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam
1.3K viewsብላቴና ዳዊት, 18:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ