Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በታንዛንያ ቆይታው የመጨረሻ ልምምዱን ዛሬ በኡሁሩ ስታዲየም አከናውኗል። | Ethiopian Football Federation

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በታንዛንያ ቆይታው የመጨረሻ ልምምዱን ዛሬ በኡሁሩ ስታዲየም አከናውኗል።

ከነሐሴ 18 ጀምሮ በታንዛንያ ቆይታ ያደረገው ብሔራዊ ቡድናችን ነሐሴ 20 ከሩዋንዳ ጋር የቻን ማጣርያ የመጀመርያ ጨዋታውን ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን ከጨዋታው በኋላ ያለፉትን ቀናት በዛው በመቆየት ለመልሱ ጨዋታ ዝግጅቱን ሲያከናውን ቆይቷል።

ቡድናችን በዛሬው ዕለት የመጨረሻ የታንዛንያ ልምምዱን ያከናወነ ሲሆን ቆይታ ያደረገበት የአውራ ሲውት ሆቴል ማኔጅመንት እና ሰራተኞች በእራት ሰዓት ላይ ኬክ በማዘጋጀት ቡድኑ በመልሱ ጨዋታ ድል አድርጎ ወደ አልጄርያው ውድድር እንዲያልፍ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

የቡድናችን አባላት ዛሬ ለሊት ወደ ሩዋንዳ የሚደርገውን ጉዞ የሚጀምሩ ሲሆን በአዲስ አበባ በኩል አድርገው በነገው ዕለት ሩዋንዳ የሚደርሱ ይሆናል ።