Get Mystery Box with random crypto!

ብሔራዊ ቡድናችን ሩዋንዳ ደርሷል በቻን ማጣርያ የመልስ ጨዋታ ሩዋንዳን የሚገጥመው ብሔራዊ ቡድናች | Ethiopian Football Federation

ብሔራዊ ቡድናችን ሩዋንዳ ደርሷል

በቻን ማጣርያ የመልስ ጨዋታ ሩዋንዳን የሚገጥመው ብሔራዊ ቡድናችን ያለፉትን ቀናት ቆይታ ያደረገበት ታንዛንያን በመልቀቅ ሌሊት 10:00 ላይ ወደ አዲስ አበባ ጉዞ ያደረገ ሲሆን ጠዋት ከደረሰ በኋላ በዛው ወደ ሩዋንዳ ጉዞውን ቀጥሎ ከቀኑ 8:00 ላይ ኩጋሊ ዓለም አቀፍ አየር ማረፍያ ደርሷል።

በስፍራው በሩዋንዳ የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ ተወካዮች በመገኘት ለቡድናችን አቀባበል ያደረጉ ሲሆን በአስፈላጊው ነገር ሁሉ ከጎናቸው መሆናቸውን ገልፀዋል።

ቡድናችን ኪጋሊ ከደረሰ በኋላ ጨዋታውን ወደሚያደርግበት ሁዬ ከተማ የ130 ኪሜ የመኪና ጉዞ በማድረግ 12:00 ገደማ ከተማው ደርሶ ማረፊያውን ክሬዶ ሆቴል አድርጓል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ነገ የመጨረሻ ልምምዱን በሁዬ ስታዲየም አከናውኖ ቅዳሜ ሩዋንዳን የሚገጥም ይሆናል።