Get Mystery Box with random crypto!

ረድኤት አስረሳኸኝ በካፍ የኮከቦች ሽልማት በምርጥ ወጣት ተጫዋቾች ዘርፍ እጩዎች ውስጥ ተካተተች | Ethiopian Football Federation

ረድኤት አስረሳኸኝ በካፍ የኮከቦች ሽልማት በምርጥ ወጣት ተጫዋቾች ዘርፍ እጩዎች ውስጥ ተካተተች

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የሴካፋ ባለ ድል እንዲሆን እና በዓለም ዋንጫ ማጣርያ እስከ መጨረሻው ዙር በዘለቀ አስደናቂ ጉዞ ላይም 7 ጎል በማስቆጠር ትልቅ ድርሻ የተወጣችው ረድኤት አስረሳኸኝ በካፍ የዓመቱ ምርጦች ሽልማት ላይ በወጣቶች ዘርፍ 10 እጩዎች ላይ መካተት ችላለች።

በሀዋሳ ከተማ እየተጫወተች የምትገኘው ወጣቷ አጥቂ ረድኤት በሽልማቱ ላይ በእጩነት በመካተቷ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተሰማውን ደስታ እየገለፀ በምርጫው መልካም ዕድል እንዲገጥማት ይመኛል።