Get Mystery Box with random crypto!

በተጫዋቾች ምዝገባ እና ዝውውር ዙርያ ስልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽ | Ethiopian Football Federation

በተጫዋቾች ምዝገባ እና ዝውውር ዙርያ ስልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢንፎርሜሽን ኮምዩንኬሽን ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀው በተጫዋቾች ምዝገባ (FIFA CONNECCT) እና የተጫዋቾች ዝውውር (FIFA TMS/DTMS) ላይ ያተኮረው ስልጠና ዛሬ በጁፒተር ሆቴል መሰጠት ጀምሯል።

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ የሆኑ ክለቦች የወንድና ሴት ተጫዋቾች ምዝገባ እና ዝውውር ላይ ያተኮረው ይህ ስልጠና ነገም ቀጥሎ የሚደረግ ይሆናል።

ይህንን ስልጠና እየሰጡ የሚገኙት ወ/ሮ ዘውድነሽ ይርዳው የፕሪምየር ሊግ ክለቦች የተጫዋቾች ዝውውር እና ምዝገባ ከዚህ ሲስተም ውጭ ማድረግ እንደማይችሉና የተጫዋቾች ህጋዊነት የሚረጋገጠው በዚህ ሲስተም ሲያልፍ በመሆኑ ክለቦች እዚህ ላይ ትኩረት በመስጠት ሊሰሩበት ይገባል ብለዋል።