Get Mystery Box with random crypto!

#AddisAbaba ዛሬ በአዲስ አበባ ፤ ' አንዋር መስጂድ ' ከጁመአ ስግደት መጠናቀቅ በኃላ የፀ | EBS TV NEWS

#AddisAbaba
ዛሬ በአዲስ አበባ ፤ " አንዋር መስጂድ " ከጁመአ ስግደት መጠናቀቅ በኃላ የፀጥታ ኃይሎች በተከፈቱት ተኩስ ጉዳት ስለመድረሱ በአካባቢው የሚገኙ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል።
በአሁን ሰዓት የተጎዱ ሰዎች እርዳታ እንዲያገኙ ጥሪ አቅርበዋል።
በመስጂዱ በነበረው ሁኔታ የአደጋ ጊዜ አዛን መሰማቱ ተነግሯል።
ከዚሁ ጋር በተያየ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ፤ " በታላቁ አንዋር መስጂድ የጁምዓ ሰላቱን ለመስገድ ከቤቱ የወጣን እና በመስጂድ ያለን ንፁሃን ህዝበ ሙስሊም ላይ ያለምንም ርህራሄ በጥይት የሀይል እርምጃ መውሰድ ኢ ሰብዓዊ ተግባር ነው " ብለዋል።
" ባዶ እጁን ለሰላት በወጡ ንፁሀን ላይ እየተወሰደ ያለውን የኃይል እርምጃ የፀጥታ ኃይሎች ያቆሙ ዘንድ አሳስባለሁ " ያሉቱ ኡስታዝ አቡበከር " በመስጂዱ ተጠልለው የሚገኙ እና ያለህራሄ በጥይት ተመትተው በመስጂዱ ውስጥ እና ዙሪያውን ወድቀው የሚገኙት ወንድሞቻችን በአስቸኳይ ወደ ህክምና ቦታ ይወሰዱ ዘንድ አምቡላንስ ወደ ቦታው እንዲገባ መንገዱን ክፍት ልታደርጉ ይገባል " ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ስለ ዛሬው የአንዋር መስጂድ ሁኔታ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እንዲሁም የአ/አ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሚሰጡት መረጃ / መግለጫ ካለ ተከታትለን እናሳውቃለን።
በተመሳሳይ በመንግስት / በከተማው አስተዳደር በኩል የሚሰጥ ማብራሪያ ካለ ተከታትለን የምናቀርብ ይሆናል።
ባለፈው ሳምንት ጁመአ በአንዋር መስጂድ በሸገር ከተማ እየተከናወነ ያለው የመስጂዶች ፈረሳ ተግባር በአፋጣኝ እንዲቆም ጥሪ በቀረበበት ወቅት በተወሰደ እርምጃ የሰዎች ህይወት ማለፉ የሚዘነጋ አይደለም።
@Ebs_tv_news