Get Mystery Box with random crypto!

በትግራይ #ኔትዎርክ ተቋርጧል። በትግራይ ክልል ከምሽት 12 ሰዓት አንስቶ የኔትዎርክ አገልግሎት መ | EBS TV NEWS

በትግራይ #ኔትዎርክ ተቋርጧል።
በትግራይ ክልል ከምሽት 12 ሰዓት አንስቶ የኔትዎርክ አገልግሎት መቋረጡን በዚህም ምክንያት " ምን ተፈጥሮ ነው ? " በሚል ጭንቀት እንደገባቸው የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የቤተሰቡን አባላት መልዕክት ይዞ ኢትዮ ቴሌኮምን አነጋግሯል።
ኢትዮ ቴሌኮም ፤ እውነት ነው ኔትዎርክ ተቋርጧል ሲል አረጋግጦልናል።
" ኔትዎርክ የተቋረጠው ፋይበር ተቆርጦ " ነው ያለው ኢትዮ ቴሌኮም " ሰራተኞቻችን በጥገና ላይ ናቸው " ብሏል።
" ከማዕከል የሚያገናኘው ፋይበር ሁለት ቦታ ተቆርጧል፤ ዋናው እና የመጠባበቂያውን ጨምሮ " ያለው ኢትዮ ቴሌኮም ፤ ከመቐለ ፣ ከደሴ እና ከሰመራ ሰራተኞች ተሰማርተው በርብርብ እየሰሩ ይገኛሉ ሲል አሳውቋል።
የጉዳቱን መጠን በተመለከተ ላቀረብነው ጥያቄ " ምሽት በመሆኑ የጉዳቱን መጠን ማረጋግጥ አልተቻለም " ተብለናል።
@EBS_TV_NEWS