Get Mystery Box with random crypto!

#EHRC ' ... ጉዳዩ ከዚህ የበለጠ ሳይባባስ ፓርላማው የመንግስት አስፈፃሚ አካሉን በአስቸኳይ | EBS TV NEWS

#EHRC
" ... ጉዳዩ ከዚህ የበለጠ ሳይባባስ ፓርላማው የመንግስት አስፈፃሚ አካሉን በአስቸኳይ ሊያሳስብ ይገባል " - ዶ/ር ዳንኤል በቀለ
ዛሬ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የ9 ወራት የእቅድ አፈፃፀሙን ሪፖርት ለህ/ተ/ም/ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አቅርቧል።
በዚህም ወቅት የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ፥ በአማራ ክልል የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች አሳሳቢ እንደሆኑ ቀጥለዋል ብለዋል።
ከቅርብ ጊዜ አንስቶ መንግሥት በአማራ ክልል እያካሄደ ያለው ወታደራዊ እንቅስቃሴ ከሰብዓዊ መብቶች አንፃር በጣም የሚያሰጋነው ሲሉ ገልጸዋል።
ዋና ኮሚሽነሩ ፤ በአሁን ወቅት በአማራ ክልል እየተካሄደ ባለው ወታደራዊ እንቅስቃሴ #በሲቪል ሰዎች ላይ ፦- የሞት፣
- የንብረት መውደም፣ - የመፈናቀል ጉዳት መድረሱን በዚህም የሰብዓዊ መብት ስጋቱም መቀጠሉን አንስተዋል።
" መንግሥት የፀጥታ እርምጃ በአማራ ክልል በማካሄድ ላይ የሚገኝ መሆኑን አሳውቋል ፤ " ያሉት ዶ/ር ዳንኤል " ነገር ግን ይህ ወታደራዊ እርምጃ የሰብዓዊ መብት እንድምታ ስላለው ፣ የሰብዐዊ መብት ተፅእኖ ስለሚፈጥር ይሄን በቅርበት እየተከታተልን ነው " ብለዋል።
" እስካሁን ባለው መረጃ በመነሳት ከሰብዓዊ መብቶች አንፃር በጣም የሚያሰጋ ስለሆነ ኢሰመኮ #ውይይት እና #ሰላማዊ መፍትሄ አስፈላጊነትን አበክሮ በማሳሰብ ጉዳዩ ከዚህ የበለጠ ሳይባባስ ፓርላማው የመንግስት አስፈፃሚ አካሉን በአስቸኳይ ሊያሳስብ ይገባል። " ሲሉ አክለዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ዶ/ር ዳንኤል ባቀረቡት ሪፖርት የዘፈቀደ እስር ፣ ሰዎች ሲታሰሩ የሚያዙበት መንገድ፣ ለሰብዓዊ ጉዳዮች አሳሳቢ ሆኖ ቀጥሏል ብለዋል።
ዶ/ር ዳንኤል ፤ " በተለያዩ አካባቢዎች የሚፈፀመው የዘፈቀደ እስር እና በእስር ወቅት የሚፈፀሙ ተገቢ ያልሆኑ አያያዞች / አንዳንድ ቦታዎች ድብደባን ጨምሮ ተገቢ ያልሆነ አያያዝና እስራት እንዲሁም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አለመከበርም ቀጥሏል " ብለዋል።
ዋና ኮሚሽነሩ ፤ አንዳንድ ቦታዎች ላይ የሚፈፀሙት የዘፈቀደ እስሮች #የቤተሰብ አባላትን ጭምር ለማጥቃት የሚውሉ ናቸው ሲሉ ለፓርላማው በሪፖርታቸው አሳውቀዋል።
@EBS_TV_NEWS