Get Mystery Box with random crypto!

#SpecialForce ' ሂደቱ ከትጥቅ ማስፈታት ጋር የሚገናኝ አይደለም ' - ወ/ሮ ሰለማዊት ካ | EBS TV NEWS

#SpecialForce
" ሂደቱ ከትጥቅ ማስፈታት ጋር የሚገናኝ አይደለም " - ወ/ሮ ሰለማዊት ካሳ
መንግሥት እያካሄደ ያለው የልዩ ኃይል አባላትን መልሶ የማደራጀት መርሃ ግብር ትጥቅ ከማያስፈታት ጋር እንደማይገናኝ አሳወቀ።
የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ ፤ " የሁሉንም ክልል ልዩ ኃይል አባላት መልሶ የማደራጀት ስራ ነው የሚሰራው እንጂ ሂደቱ ከትጥቅ ማስፈታት ጋር የሚገናኝ አይደለም " ብለዋል።
የተጀመረው መልሶ የማደራጀት ሂደት የሀገር ሉዓላዊነትን ከማስጠበቅ፣ ከሀገር ውስጥ ሆነ ከውጭ የሚሰነዘርን ማንኛውም አይነት ጥቃት ከመከላከል አንፃር ጠንካራ የመከላከያ ኃይል ለመገንባት የሚያስችል ዕድል ነው ሲሉ ገልጸዋል።
" ህወሓትን በተመለከተ ፤ በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት ትጥቅ የመፍታት ሂደቱ ያለማወላወል የሚፈፀም ነው " ያሉት ወ/ሮ ሰላማዊት " ሂደቱ ከሌሎች ሀገራዊ እቅዶች ጋር የሚገናኝ አይደለም / የሚጣረስም አይደለም እራሱን ችሎ በራሱ መርሀግብር የሚከናወን ነው " ሲሉ አስረድተዋል።
ይህንን ሂደት ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች እየተከታተሉት መሆኑ መታወቅ አለበት ሲሉ አክለዋል።
ወ/ሮ ሰላማዊት የክልል ልዩ ኃይል አባላትን መልሶ ማደራጀት " በሁሉም ክልሎች በተመሳሳይ ወቅት እየተተገበረ ያለ ነው " ያሉ ሲሆን ሂደቱ በጥንቃቄ እና በጋራ መግባባት እየተመራ ያለ ነው ሲሉ አሳውቀዋል።
በሂደቱ በሁሉም ክልሎች ሰላም እና ደህንነትን ለማረጋገጥ በተለይ የፀጥታ ስጋት / የማህበረሰብ ጥያቄ ያለባቸው ቦታዎች ላይ ሀገር መከለከያ ሰራዊት ሁሉም ቦታዎች ስምሪት ወስዶ እየተንቀሳቀሰ ነው በዚህ ረገድ ክፍተት አይፈጠርም ብለዋል።
እየተካሄደ ባለው የመልሶ ማደራጀት ስራ በልዩ ኃይል ውስጥ ያሉ አባላት እንደምርጫቸው / እንደ ፍላጎታቸው ፦- በሀገር መከላከያ ሰራዊት
- በፌዴራል ፖሊስ- በክልል ፖሊስ አባልነት መካተት ይችላሉ ተብሏል።
ወደነዚህ የፀጥታ መዋቅሮች የሚቀላቀሉት ትጥቃቸውን እንደያዙ መሆኑ ተመላክቷል።
በዚህ ውስጥ መካተት የማይፈልጉ የልዩ ኃይል አባላት መብታቸው እንደሚጠበቅ እና ወደ መደበኛ ሲቪል ህይወት እንደሚገቡ መንግሥት የማቋቋም ስራ እና ድጋፍም እንደሚያደርግ ገልጿል።
@Ebs_tv_news