Get Mystery Box with random crypto!

#Amhara ልዩ ኃይሉን ምን አስቆጣው ? መንግሥት በአማራ ክልል የልዩ ኃይል መልሶ ማደራጀት | EBS TV NEWS

#Amhara

ልዩ ኃይሉን ምን አስቆጣው ?

መንግሥት በአማራ ክልል የልዩ ኃይል መልሶ ማደራጀት እንቅስቃሴ ውስጥ ምን ስህተቶችን ፈፀመ ?


የአማራ ክልል ብልፅግና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ ትላንት ምሽት በክልሉ ቴሌቪዥን ቃለምልልስ አድርገዋል።

በዚሁ ቃለምልልስ ወቅት በአማራ ክልል ከልዩ ኃይል መልሶ ማደራጀት እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ ተፈፀመዋል ስላሉት ስህተቶች አብራርተዋል።

በተጨማሪ በክልሉ ህዝብ ዘንድ ስለሚነሱት ስጋቶች፣ጥያቄዎች ቅሬታዎች ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተዋል።

አቶ ግርማ የሺጥላ አተገባበሩንና የተፈፀሙ ስህተቶችን፣ እና ያጋጠሙ ችግሮችን በተመለከተ ምን አሉ ?

" ...በተገባበር በኩል በአማራ ክልል ሁኔታ ለየት ያሉ ችግሮች ገጥመዋል። ውሳኔው ሀገራዊ ውሳኔ ነው፤የሁሉንም ይሁንታ ያገኘ ነው። ይልቁንም በውሳኔ ደረጃ ከተመለከት ነው ይህ ጉዳይ መፍጠን ነበረበት ተብሎ የሚወሰድ ነው።

አሁንም ቢሆን አልመሸም ነበርና ከተወሰነ በኃላ አፈፃፀሙ ዝርዝር እቅድ ወጥቶለት እንዲከናወን ሲደረግ በአማራ ክልል የገጠመ ችግር አለ።

የገጠመው ችግር አንደኛው እና ዋነኛው ስራውን እንዲካከናውን የተደጋጀው ኃይል የተከተለው መንገድ ብዙ እቅዱን የተመረኮዙ ስራዎች ቢሆንም የተፈፀሙ ስህተቶች አሉ።

የመጀመሪያው የተፈፀመው ስህተት የቅድመ እውነቶች፤ፖለቲካ ስራዎች ቀድመውናል። አንደኛው ልዩ ኃይሉን መልሰን እናደራጃለን የሚል እቅድ ይዘን ለመንቀሳቀስ ስራ ስንሰራ 'ልዩ ኃይሉን ለማፍረስ መንግሥት ወሰነ' የሚል የፖለቲካ ስራ በስፋት ተሰራጨ።

2ኛው ልዩ ኃይሉ እየተጠቀማቸው ያሉ የጦር መሳሪያዎች እና ተተኳሾች እንዲሁም ልዩ ልዩ ግብአቶችን በተመለከተ በእቅዱ ላይ የተመላከተው በዋነኛነት ክልሉን ለማጠናከር፣ ይሄን ኃይል ይዞ ለማጠናከር እንደሚውሉና ተነግሮት አውቆ አምኖበት በወታደራዊ ዲሲፕሊን ለየሚፈለግበት ስራ እንደሚያውል ተደርጎ የተቀመጠውን ትጥቅ ' ሊፈታ ነው ' እና የአማራን ክብር እና ሞገስ የሚያዛባ አይነት ስራ እንደሚሰራ ተደርጎ ተገለፀ።

3ኛው ይሄ ኃይል ሪፎርም ሲደረግ በዋነኛነት የክልሎችን የፀጥታ ተቋም እንደሚያጠናክር ሳይሆን ወደ መከላከያ ግባ እንደተባለና የመከላከያ ኃይል በጉልበት እንደሚያደርገው ተደርጎ ተቀነቀነ።

በዚህ ምክንያት የአማራ ክልል የስራው ባለቤቶች ስራው ወደ ክልል መጥቶ ሲጀመር ስርዓት ባለው መንገድ በአግባቡ ውይይት፣ ንግግር ሲደረግ በመሃል ከስራ አስፈፃሚዎች መካከል 'ትጥቅ እንዲያወርድ' የሚል ደብዳቤ የመንግስት መሪዎች፣ የፖለቲካ መሪዎች ባላወቅነው መንገድ ሾልኮ ይልቁንም ሰራዊቱ ሳያውቀው በማህበራዊ ሚዲያ ሲዘዋወር ተመለከትን።

በዚህ በእጅጉ አዝነናል፤ አንደኛ የሰራዊቱንም የህዝቡንም ክብር ይነካል። ሁለተኛ ለቆምንለት አላማና ለምንሰራው ስራ በፍፁም የሚመጥን ደብዳቤ አይደለም።

ያለው የፖለቲካ ሴራ እንዲህ አይነት ነዳጅ ሲያገኝ የበለጠ ተጋጋለ በመጋጋሉ ምክንያት ልዩ ኃይሉ ሊወያይ ካለበት ቀን በፊት ለምንድነው የተበደልኩት? ለምንድነው ላደረኩት አስተዋፅኦ እንዲህ አይነት ደብዳቤ ሳይነገረኝ ሳልወያይ የከፈልኩት መስእዋትነት ደሙ ሳይደርቅ እንዲህ አይነት በደል ለምን ይሰርስብኛል ብሎ ተቆጣ፤ መቆጣቱ ትክክል ነው።

የእሱ (የልዩ ኃይሉ) አመራሮች ግን ተወያይተዋል። እኔ እራሴ ባለሁበት፣ ክቡር ምክትል ፕሬዜዳንቱ ባሉበት፣ የሀገሪቱ ምክትል ኢታማዦር ሹም ባሉበትና ሌሎች አካላት ባሉበት የሁሉም የአማራ ክልል የ21ዱ ዞንና ከተማ አስተዳደሮች የመንግሥት እና ፖለቲካ አመራሮች፣ የፀጥታ ' ሚኒ ካቢኔ ' በተለምዶ ይሄ አካል በተሳተፈበት ውይይት ተካሂዷል። "

(ሙሉ ቃለምልልሱ ከላይ ተያይዟል)

Video:AMC (196 MB)

@EBS_TV_NEWS