Get Mystery Box with random crypto!

የፀሐይ ግርዶሹ በርካታ የአሜሪካ ከተሞችን በእኩለ ቀን አጨልሟቸዋል ******************* | EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

የፀሐይ ግርዶሹ በርካታ የአሜሪካ ከተሞችን በእኩለ ቀን አጨልሟቸዋል
****************************

የፀሐይ ግርዶሹ በርካታ የአሜሪካ ከተሞችን በእኩለ ቀን ሙሉ በሙሉ እንዳጨለማቸው ተገልጿል፡፡

ሙሉ የጸሐይ ግርዶሹ ማዛትላን የተባለችውን የሜክሲኮ ከተማ ጨለማ አልብሷት ካለፈ በኃላ ወደ ዳላስ፣ ቴክሳስ እና ሌሎች የአሜሪካ ግዛቶች ተሸጋግሯል፡፡

በአንዳንድ የአሜሪካ ግዛቶች የጸሐይ ግርዶሹ እስከ 4 ደቂቃ መቆየቱም ተመላክቷል፡፡

የጸሐይ ግርዶሹ በሚቀጥሉት ሰዓታት ወደ ሰሜን አሜሪካ ሰሜናዊ እና ምስራቃዊ ክፍሎች እንደሚዞርም ተጠቁሟል፡፡

በሰሜን አሜሪካ ክስተቱን ለማየት በ10 ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች አደባባይ መውጣታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ክስተቱን በልዩ ሁኔታ እየተከታተለ የሚገኘው የአሜሪካ የጠፈር ምርምር ተቋም (ናሳ) ያለ ጸሐይ መነጽር ግርዶሹን ለማየት መሞከር የዓይን ብርሃንን እስከማሳጣት የሚያደርስ የጤና ችግር ሊያስከትል እንደሚችል በማስገንዘብ ላይ ነው፡፡