Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያ 6ኛውን እና 7ኛውን  ወርቅ በ5 ሺህ ሜትር እና በ1 ሺህ 500ሜትር ሴቶች ሩጫ ውድድር | EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

ኢትዮጵያ 6ኛውን እና 7ኛውን  ወርቅ በ5 ሺህ ሜትር እና በ1 ሺህ 500ሜትር ሴቶች ሩጫ ውድድር አገኘች
*****
በጋና እየተካሄድ ባለው 13ኛው የመላ አፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ በ5 ሺህ ሜትር ወንዶች እና በ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች ሩጫ 6ኛውን እና 7ኛውን ወርቅ አግኝታለች፡፡
ለኢትዮጵያ በ5 ሺህ ሜትር ወንዶች ፍፃሜ በሚያስደምም የአጨራረስ ብቃት ወርቅ ያመጣው አትሌት ሀጎስ ገ/ሕይወት ነው።
አትሌት ሂሩት መሸሻ በ1 ሺህ 500ሜትር ሴቶች ሩጫ ውድድር የወርቅ ሜዳለያ ያስገኘች ሌላኛዋ ጀግና አትሌት ናት፡፡
አትሌት ሀዊ አበራም  የብር ሜዳሊያ በማስገኝት የአገሯን ክብር ከፍ አስደርጋለች፡፡
በ1500 ሜትር ወንዶች ፍፃሜም ሌላኛው ባለድል ኤርሚያስ ግርማ   የብር ሜዳልያ ለአገሩ አስገኝቷል፡፡https://www.facebook.com/share/p/L64tzNa5JTcbHNLn/?mibextid=qi2Omg