Get Mystery Box with random crypto!

ባለፉት 3 ወራት ዲኘሎማሲውን ወደ ከፍታ መመለስ ያስቻሉ ስራዎች መሰራታቸው ተገለፀ ********* | EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

ባለፉት 3 ወራት ዲኘሎማሲውን ወደ ከፍታ መመለስ ያስቻሉ ስራዎች መሰራታቸው ተገለፀ
**************

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የ2016 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፓርት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በዛሬው እለት ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።

በሪፖርቱ ግንኙነትን በማጠናከር፣ የኢትዮጵያን ተሰሚነት በማሳደግ እና ሚዛናዊ አቋም እንዲያዝ በማድረግ፣ የኢንቨስትመንት ፍሰትን በማሳደግና በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ዜጎችን ከውጭ በመመለስ ዲፕሎማሲው ውጤታማ እንደነበር ተነስቷል።

ባለፉት ሶስት ወራት በጎረቤት ሃገራት ከ11 በላይ ጉብኝቶችን በማድረግ ግንኙነትን የማጠናከር ስራዎች ተሰርተዋል ነው የተባለው።

https://ebc.et/newsdetails.aspx?newsid=4267