Get Mystery Box with random crypto!

ሙሉቀን መለሰ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ ***************************** የቀድሞ ድም | EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

ሙሉቀን መለሰ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
*****************************
የቀድሞ ድምፃዊ ሙሉቀን መለሰ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን የድምፃዊው የቅርብ ምንጮች ለኢቢሲ ሳይበር አረጋግጠዋል።
ሙለቀን መለሰ በሚኖርበት ሀገረ አሜሪካ ነው ሕይወቱ ያለፈው::
ገና የ13 ታዳጊ ሳለ ሙዚቃን የጀመረው ድምፃዊው በ1958ዓ.ም በፈጣን ኦርኬስትራ ውስጥ ተቀላቅሎ በመግባት ለሁለት ዓመታት ያህል መስራት ችሏል።
ከእዚያ በማስከተል በ1960 ዓ.ም ወደ ፖሊስ ኦርኬስትራ ክፍል በመግባት ይበልጥ በሙዚቃ ስራው ዝናን ማትረፍ ችሎ ነበር።
በ1972 ዓ.ም ላይ ደግሞ ከዳህላክ ባንድ ጋር ተቀላቅሎ ሰርቷል፡፡ እስከ 1980ዎቹ ድረስ በነበሩት ዓመታት እጅግ ተወዳጅ የሙዚቃ ስራዎችንም መስራት ችሏል።
የአንጋፋዋ ሁለገብ ከያኒት የአለምፀሐይ ወዳጆ እና የተስፋዬ ለሜሳን ግጥምና ዜማዎች አቀንቅኗል።
ሙዚቃ በቃኝ ብሎ ራሱን ከሙዚቃው ዓለም እስካገለለበት ጊዜ ድረስ በርካታ የሙዚቃ ስራዎችን ለትውልድ አበርክቷል።
ከ1980ዎቹ በኃላ ፊቱን ወደ መንፈሳዊ ስራዎች በማዞር የመዝሙር ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል።
እስከ ህልፈተ ሕይወቱ ድረስ በሀገረ አሜሪካ ኑሮውን አድርጎ በእዚያው ቆይቷል።
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽንም በአንጋፋው ድምጻዊ ሙሉቀን መለሰ ህልፈት የተሰማውን ሀዘን እየገለጸ፤ ለቤተሰቦቹና ለአድናቂዎቹ መጽናናትን ይመኛል።