Get Mystery Box with random crypto!

የአሜሪካ የረድኤት ድርጅት ኃላፊ ሳማንታ ፓወር የአፍሪቃ ቀንድ ጉብኝታቸውን ጀመሩ። የአሜሪካ የረ | ዶይቸ ቬለን | DW AMHARIC NEWS🇪🇹

የአሜሪካ የረድኤት ድርጅት ኃላፊ ሳማንታ ፓወር የአፍሪቃ ቀንድ ጉብኝታቸውን ጀመሩ።
የአሜሪካ የረድኤት ድርጅት በእንግሊዥኛው ምህፃሩ USAID ኃላፊ ሳማንታ ፓወር በአፍሪካ ቀንድ በጎርጎሮሳዊው ከዛሬ ሀምሌ 22 ቀን 2022 ጀምሮ ለሶስት ቀናት ለሚያደርጉት ጉብኝት ትናንት ኬንያ ገብተዋል።
ሀላፊዋ ድርቅ ያስከተለውን ጉዳት ለመገምገም ሶማሊያን እንዲሁም ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። ጉብኝቱ ድርጅቱ በሶማሊያ፣ በኬንያ እና በኢትዮጵያ በሚሊዮን በሚቆጠሩ ሰዎች ላይ የደረሰውን የድርቅ አደጋ ለመከላከል ተጨማሪ 1.2 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ እንደሚሰጥ ከገለፀ ከቀናት በኋላ ነው።
ከፍተኛ የረሃብ ስጋት ባለባቸው ሀገራት የሚደርሰውን ረሃብ እና ሞት ለመታደግ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሀብት እንዲያሰባስብ ፓወር በጉብኝቱ ወቅት ያሳስባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ሳማንታ ፓወር በጉብኝታቸው ከሰብአዊ አጋሮች፣ ከሲቪል ማህበረሰብ እና ከከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር ስለ ድርጅቱ ድጋፍ እና ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምታደርገው ጦርነት በምግብ ዋስትና ላይ ስላስከተለው ተጽእኖ ይወያያሉ ተብሏል።