Get Mystery Box with random crypto!

የሐምሌ 16 ቀን 1014 ዓ/ም የዓለም ዜና በድምጽ ርዕሶቹ አዲስ አበባ ውስጥ የሽብር ጥቃት ሊፈጽ | ዶይቸ ቬለን | DW AMHARIC NEWS🇪🇹

የሐምሌ 16 ቀን 1014 ዓ/ም የዓለም ዜና በድምጽ
ርዕሶቹ
አዲስ አበባ ውስጥ የሽብር ጥቃት ሊፈጽሙ ነበር ያላቸውን ከ450 በላይ ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የፌደራል የጸጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ። ግብረ ኃይሉ ዛሬ ባወጣው መግለጫ መሠረት ተጠርጣሪዎቹ አል ሸባብ እና አይ ኤስ እና በሀገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የአራት ታጣቂ ቡድኖች አባላት ናቸው።

በምስራቅ አፍሪቃ በዚህ ዓመት ከ50 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ለከፍተኛ የምግብ ዋስትና እጦት ሊጋለጡ እንደሚችሉ የምስራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግስታት ወይም በእንግሊዘኛ ምህጻሩ ኢጋድ አስጠነቀቀ። ኢጋድ ትናንት አርብ ባወጣው መግለጫው በሶማሊያ እና ሱዳን ከ300 ሺ በላይ ሰዎች በከፋ የረሃብ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ገልጿል።

በማሊ በዋነኛው የመንግስት ወታደራዊ የጦር ሰፈር ላይ ለደረሰው ጥቃት ከአልቃኢዳ ጋር ግንኙነት እንዳለው የሚነገርለት እስላማዊ ቡድን ኃላፊነት ወሰደ። ቡድኑ ጥቃቱን የማሊ የመንግስት ኃይሎች ከሩሲያ ቅጥረኞች ጋር በማበራቸው የተሰጠ ምላሽ ነው ብሏል።

ሩሲያ በጥቁር ባህር ዳርቻ የምትገኘውን የዩክሬኗን የወደብ ከተማ ኦዴሳን በሚሳኤል መታች። የዛሬው የሩሲያ የሚሳኤል ጥቃት የተሰማው ሞስኮ ከኪዬቭ ጋር በወደብ ከተማዋ በኩል እህል ወደ ውጭ እንዲላክ ከስምምነት ከደረሱ ከሰዓታት በኋላ ነው።

የዓለም ጤና ድርጅት በርካታ ሀገራትን እያዳረሰ የሚገኘውን የጦጣ ፈንጣጣ በሽታ «ዓለም አቀፍ ስጋት» ሆኗል ሲል አወጀ።
https://p.dw.com/p/4EYZE?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
@dwcommentbot