Get Mystery Box with random crypto!

በግብፅ፣ በሱዳን እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ትብብር ማስፋት የታላቁ ህዳሴ ጉዳይን ለመፍታት | ዶይቸ ቬለን | DW AMHARIC NEWS🇪🇹

በግብፅ፣ በሱዳን እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ትብብር ማስፋት የታላቁ ህዳሴ ጉዳይን ለመፍታት ያስችላል ሲሉ የግብፁ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ተናገሩ።
አልሲሲ ይህንን የተናገሩት ትናንት በሰርቢያ የቤልግሬድ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ከተሰጣቸው በኋላ ባደረጉት ንግግር ነው።
በየሄዱበት ሀገር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጉዳይ በማንሳት የሚታወቁት አልሲሲ በሳምንትቱ መጀመሪያ ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት በምስራቅ አውሮፓዊቷ ሀገር ሰርቢያ ባደረጉት ጉብኝትም ጉዳዩን አንስተዋል።
ኤል ሲሲ በትናንቱ ንግግራቸው በግብፅ፣ በሱዳን እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ትብብር ማስፋት የታላቁ ህዳሴ ጉዳይን ለመፍታት ያስችላል ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በሶስቱ ሀገራት መካከል ሚዛናዊ እና ፍትሃዊ የህግ ስምምነት መኖሩ የኢትዮጵያን የልማት እና የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ከማሳደግ ጎን ለጎን የግብፅን እና የሱዳንን የውሃ መብት ለማስጠበቅ ያስችላል ብለዋል።
ግብፅ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጉዳይ ላይ የግብፅና የኢትዮጵያን ግንኙነት ለማሳደግ ያላትን እምነት መሰረት በማድረግ ለዓመታት የድርድር መንገድን ስትከተል መቆየቷን ገልፀው፤የውሃ አካላትን የጋራ አጠቃቀም የሚቆጣጠሩ ሁለንተናዊ መርሆች መከበር እንዳለባቸው ተናግረዋል። ይህም እንደ ፕሬዚዳንቱ የሀገሮችን ፍላጎት በሚዛናዊ በሆነ መንገድ ያሳካል።
ህጋዊ ስምምነት በሌለበት ሁኔታ ኢትዮጵያ የግድቡን የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ሙሌት በማጠናቀቅ በያዝነው አመት መጀመሪያ የግድቡን ተርባይን የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨት መጀመሯ እና ሦስተኛውን ሙሌትም በመጭው ነሀሴ እና መስከረም ወር ለመጀመር ዕቅድ መያዟ እንዳሳሰባቸው መግለፃቸውን አልሃራም የተባለው የግብፅ ጋዜጣ ዘግቧል።