Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ አበባ ቅዳሜ እና እሁድ ያስተናገደችው የእሳት አደጋ ፦ #1 በጉለሌ እጸዋት ማእከል የደረ | ዶይቸ ቬለን | DW AMHARIC NEWS🇪🇹

አዲስ አበባ ቅዳሜ እና እሁድ ያስተናገደችው የእሳት አደጋ ፦

#1

በጉለሌ እጸዋት ማእከል የደረሰው የእሳት አደጋ 2 ሄክታር ቦታ የሸፈነ ነው። በአደጋው ከ200 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወድሟል፤ ምን ያህል ንብረት ከውድመት እንደተረፈ ለጊዜው አልታወቀም።

#2

በጉለሌ ክፍል ከተማ ወረዳ አምስት ጽዮን ሆቴል አካባቢ በአንድ ሼድ ላይ በደረሰው የእሳት አዳጋ ከ50 ሺህ ብር በላይ የሚጠጋ ንብረት ለውድመት ሲዳረግ ከ4 ሚሊየን ብር በላይ የሚጠጋ ንብረት ደግሞ ማዳን ተችሏል፡፡

#3

በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ አንድ ኮሎምብያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በመኖርያ ቤት ላይ በደረሰ አደጋ 20 ሺህ ብር በሚገመት ንብረት ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን ከ300 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ንብረት ማዳን ተችሏል፡፡

#4

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ገርጂ ማርያም አካባቢ በአንድ ህንጻ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ 100 ሺህ ብር በሚጠጋ ንብረት ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን ከ100 ሚሊየን ብር በላይ ከውድመት ማዳን እንደተቻለ ተችሏል።

#5

በጉለሌ ክፍለ ከተማ እንጦጦ ማርያም አካባቢ ላይ በሚገኝ የእንጨት ክምር ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ ሶስት መቶ ሺህ የሚጠጋ ንብረት ሲወድም ወደ አንድ ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ማዳን ተችሏል።

#6

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 "እፎይታ የገበያ ማዕከል" ላይ በሚገኙ ሱቆች ላይ በደረሰው የእሳት አደጋ የጉዳት መጠን በማጣራት ላይ ይገኛል።

* ዛሬ ሰኞ ቦሌ ዘሀብ ሆቴል ፊት ለፊት እና ኡራኤል አካባቢ በመኖሪያ ቤቶች ላይ የእሳት አደጋ አጋጥሞ ነበር (የጉዳት መጠን አልታወቀም)

(የእሳትና የአዳጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን)
Compiled By: ETHIO FM 107.8

@dwamharic_news
@dwamharicnewsbot