Get Mystery Box with random crypto!

#AddisAbaba 'ዛሬም በሁለት ተጨማሪ አካባቢዎች እሳት ለማስነሳት የተደረገው ሙከራ ከሽፏል' | ዶይቸ ቬለን | DW AMHARIC NEWS🇪🇹

#AddisAbaba

"ዛሬም በሁለት ተጨማሪ አካባቢዎች እሳት ለማስነሳት የተደረገው ሙከራ ከሽፏል" - የአ/አ ከተማ አስተዳደር

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዛሬ በሁለት ተጨማሪ አካባቢዎች እሳት ለማስነሳት የተደረገው ሙከራ ከሽፏል ሲል ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ገለፀ።

በከተማው ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች እየታዩ ያሉት የእሳት ቃጠሎዎች በከተማው ህዝብ እና አመራሮች፣ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ሰራተኞች፣ የፀጥታ አካላትና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የጋራ ርብርብ የከፋ ጉዳት ሳያደርሱ መቆጣጠር ተችሏል ብሏል አስተዳደሩ።

አስተዳደሩ ፥ "የጥፋት አላማቸው ያልተሳካላቸው አካላት ሆን ብለው ህብረተሰቡን ለማሸበር እያደረጉት ያለው ተግባር እንደማይሳካ እናሳውቃለን" ብሏል በመግለጫው።

ህብረተሰቡ ሳይደናገጥ ተገቢውን ጥንቃቄ እያደረገ፣ ሳይዘናጋ ነቅቶ አካባቢውን በመከታተል እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መረጃ በመለዋወጥ ያለምንም ስጋት መደበኛ እንቅስቃሴውን ማስቀጠል ይኖርበታልም ብሏል።

@dwamharic_news
@dwamharicnewsbot