Get Mystery Box with random crypto!

ከጀናዛ ማጠቢያ ክፍል ቁ • 29 እስልምናን የአስር ሰላት ወቅት | Ethio Muslims ☪️

ከጀናዛ ማጠቢያ ክፍል ቁ • 29

እስልምናን የአስር ሰላት ወቅት ነው የተቀበለው። ሻወር ከወሰደና ሸሀዳን ከያዘ በኋላ አስር መግሪብና ኢሻን ሰግዶ ስለ ኢስላም ለማወቅ ላፕቶፑን ከፍቶ እያነበበ ለሊቱን አሳለፈ። ቅርብ ጓደኛዬ ነበር የሱብሂን ሰላት ሰግጄ እንደጨረስኩ ልዘይረው ወደ ቤታቸው አመራሁ። ከቤታቸው አቅራቢያ የለቅሶ ድምፅ ይሰማል። ስሙን እየጠሩ ያለቅሳሉ።አንድ አደጋ መከሰቱን አስተዋልኩ ድንጋጤ ወረረኝ። ጓደኛዬ ምን ሆነ ብዬ ጠየቅኩ አንገታቸውን አቀርቅረው በለቅሶ መለሱልኝ። ወዳለበት ክፍል ገባሁ ሱብሂን እየሰገደ ሱጁድ ላይ ነበር የሞተው። ክፍት ወደነበረው ላፕቶፑ አይኖቼን ስወረውር ስለ ሑረል አይን ውበት የሚገልፅ ፅሁፍን ተመለከትኩ ለካ ስለ ጀነት ፀጋ በውስጧ ለእኛ አላህ ስላዘጋጀልን እንስት እያነበበ ሳለ የሱብሂ ወቅት ገብቶበት እየሰገደ ነበር ሱጁድ ላይ የሞተው።
ነገ አንቺም አንተም ትሞታለህ ቁም ነገሩ መሞትህ ሳይሆን በየትኛው ሁኔታ ላይ እንደምትሞት ነው።
አላህዬ ሆይ! መጨረሻችንን አሳምርልን

እባክዎ ለወዳጅ ዘመድዎ ሼርና ፎርዋርድ በማድረግ ያዳርሱ የሰዎች የተውበት ሰበብ በር ይሁኑ

በቻናላችን በሚሰጡ ትምህርቶች ተሳታፊ ለመሆን ይህን ይጫኑና ጆይን ይበሉ


https://t.me/shekalidarashid
https://t.me/shekalidarashid