Get Mystery Box with random crypto!

ከጀናዛ ማጠቢያ ክፍል ቁ • 28 በመኪና አደጋ ታሞ ሆስፒታል ከተኛ ሰ | Ethio Muslims ☪️

ከጀናዛ ማጠቢያ ክፍል ቁ • 28

በመኪና አደጋ ታሞ ሆስፒታል ከተኛ ሰንበትበት ብሏል። ዘመድም ሆነ ቅርብ አስታማሚ የለውም። የቆሸሸና የተበጫጨቀ ጀለቢያ ለብሷል። ጎዳና ላይ እንደሚኖር ሁኔታው ይመሰክራል። ዙርያውን በቆዳ ተደርጎ በቀይ ክር የተሰፋ ቁርአን በእጁ ይዟል ሽፋኑ በደም ተጨማልቋል። ጎዳናው ጫፍ ላይ ሆኖ ቁርአንን በመቅራት ላይ ሳለ ነበር መኪና ገጭቶት የተዘረረው። ቁርአኑን ከደረቱ ጋር ለጥፎ ሳይለቅ ሆስፒታል ገባ። ህመሙ ሲበረታበት በእጁ የያዘውን የአላህን ቃል ግንባሩ ላይ ሲያደርገው ያስታግስለታል። ሲኖርም ሲሞትም ቁርአኑ አልተለየውም።
ሩሁ ከጀሰዱ ተላቀቀች ወደ ጀናዛ ማጠቢያ ክፍሉ ይዘነው ገባን ከሰውነቱ ከሚፈሰው የደም ሽታ ጋር ተቀላቅሎ ከሚስክ በበለጠ የሚያውድ ሽታ ቤቱ ታጥኗል። ፈገግታን ተላብሶና አመልካች ጣቱን ለላኢላሀ ኢለላህ እንደቀሰረ ነው በዱንያ ላይ ሲኖር የቆሸሸ ቢመስልም ስናየው አምሮበታል። ጀናዛውን ማጠብ ጀመርኩ ሰውነቱ አንድም ቆሻሻ አይታይበትም አካሉን አገላብጬ ለማጠብ አልተቸገርኩም እንደውም እኔ ሳልሆን ጀናዛው እራሱን በራሱ ያጠበ ይመስላል። አጥበን እንደጨረስን በነጭ ጨርቅ ከፈንነው። ከሰውነቱ የሚመነጨው እንደሚስክ የሚጣፍጥጠው ሽታ ስላለ ከፈኑን ሽቶ ለመቀባት አልፈለግንም። ወደ ቀብሩ አስገባነው ቀብረነውም ተመለስን።
ማታ ላይ እሱ ካለበት ቀብር የሚወጣ ብርሀንን ተመለከትን አካባቢው ቦግ ባለ ብርሀን ተሞላ ነዋሪው ሁሉ በአግርሞት ተጠራርቶ መመልከት ጀመረ ይህ ብርሀንም በቀብሩ ላይ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ተስተዋለ።

ምንኛ ያማረ አሟሟት ነው!!!
በድህነት የጎዳና ህይወቱ ላይ እንኳ ቁርአን አልተለየውም ነበር እኛስ ?!

እባክዎ ለወዳጅ ዘመድዎ ሼርና ፎርዋርድ በማድረግ ያዳርሱ የሰዎች የተውበት ሰበብ በር ይሁኑ

በቻናላችን በሚሰጡ ትምህርቶች ተሳታፊ ለመሆን ይህን ይጫኑና ጆይን ይበሉ


https://t.me/shekalidarashid
https://t.me/shekalidarashid