Get Mystery Box with random crypto!

Dondor Times - ዶንዶር ታይምስ

የቴሌግራም ቻናል አርማ dondortimes — Dondor Times - ዶንዶር ታይምስ D
የቴሌግራም ቻናል አርማ dondortimes — Dondor Times - ዶንዶር ታይምስ
የሰርጥ አድራሻ: @dondortimes
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.45K
የሰርጥ መግለጫ

በአገራችንና ቀጠናችን ላይ ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የዚህ ቴሌግራም ገፅ ቤተሰብ ይሁኑ-ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
@Dondor_Times - provide you political, economical and social information,analysis on Ethiopia and the horn of Africa

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-31 07:45:48 አሁንም ምስጋና ለአ/አ ፖሊስ !!
ፖሊስ ሲያጠፋና ሲያጎድል የምንወቅሰውን ያህል፣ ሲሰራና ውጤት ሲያስመዘግብ ማመስገንና ማበረታታም አለብን።
ይህን የማለት መነሻዬ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመዲናችን ለሚ ኩራ ክ/ከ ወረዳ 13 እና የካ ክ/ከ ወረዳ 12 ( ካራ ስጋቤቶቹ አካባቢ) ለወራት ያህል ህዝብ የተማረረበት የዘረፋ ወንጀል፣ ዋነኛ ተጠርጣሪዎቹ በፖሊስ እጅ በመውደቃቸው ነው።
አንድ የቡና መጭመቂያ ውርክሾፕ፣ ጋራጅ፣ የሳይክል መሸጫ ሱቅች፣ ሶስት ሆቴል ቤቶች ፣ሁለት የግለሰብ ቤቶች...በቡድን በተደራጁ የጦር መሳሪያና ተሸከርካሪ በያዙ ሌቦች በቀናት ልይነት ተዘርፈው ነበር። ነዋሪዎችም " ፖሊስ እየረዳን አይደለም " እስከ ማለትም ደርሰው ነበር።
እንሆ ዝርዝር መረጃውን ራሱ ፖሊስ የሚያሳውቀው ፣ ሆኖ እዛው ሰፈር ውስጥ ባሉ የቆራሌ ቤትና አሸዋ ቤት " ሰራተኞች" አስተባባሪነት ከ40 የማያንሱ የዘረፋ ቡድኑ አባላት በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆናቸውን ሰምተናል ። ግሩም የምርመራ ውጤትም የሚባል ተግባር ተሰርቷል።
አሳዛኙ ነገር ደግሞ የፖሊስና የመከላከያ ልብሰ ጭምር እየለበሱ ' መንግስት አልቻለም' እንዲባል ጭምር ሲሰሩ የነበሩት እነዚህ ወንበዴዎች፣ የጁንታው ተባባሪዎችና ኤርትራውያን ሆነው መገኘታቸው ነው ። ይህም የወንጀሉን አቅጣጫና ቀጣዮን ስጋት ያሳያል።
እናም ሁሉም ዜጋ ተባብሮና ነቅቶ ራሱንና አካባቢውን ከወንጀል ሊጠብቅ ይገባል።
ፖሊስም በርታ፣ ከጎንህ ነን መባል አለበት!!
አበበ ጃለታ
# BMH
388 views04:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 07:15:17 #ወልቃይት

ፍልሚያውን ትህነግ/ህወሓት ዛሬ ጀምሮቷል። ህዝባችን ከጥምር ጦሩ ጋር በመሆን የተለመደውን አኩሪ ጀብደ በወራሪ ቡድን ላይ ይፈፅማል
372 views04:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 07:11:53
“በህዝባችን ላይ እየደረሰ የሚገኘውን የጠላት ትህነግና መሰሎቹ ወረራ ለመቀልበስ በየትኛውም ግንባር ለመሰለፍ ዝግጁ ነን” ፦ የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር

በወቅታዊ የጠላት ወረራ ሲመክር የቆየው የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር በህዝባችንና በሀገራችን የህልውና ዕጣ ፈንታ ላይ ያነጣጠረውን የጠላት ወረራ እንደተለመደው ከህዝባችንና ከፀጥታ አካላት ጎን በመሰለፍ ማንኛውንም መስዕዋትነት በመክፈል ጠላትን ለመፋለምና ዕኩይ ምኞቱን ለማክሸፍ ዝግጁ መሆናችንን እናሳውቃለን።

ህዝባችን የተለመደው አጋርነትህ እንዳይለየን እያልን ከዘመቻ ዝግጅታችን መሳ ለመሳ የሚከተሉት ትብብርና ድጋፎች የሚመለከተው አካል እንዲያደርግልን እናሳስባለን።

1ኛ. አላግባብ በእስር የሚገኙ የፋኖ ዓባሎቻችን በአስቸኳይ እንዲፈቱ፣

2ኛ. በከፋፋይ ሴረኞችና በተራ አሉባልታ እየተሳደዱና ያልተገባ ጫና እየደረሰባቸው የሚገኙ በየትኛውም አካባቢ የሚገኙ የፋኖ ዓባላት ነፃነት ተሰቷቸው ትግሉን እንዲቀላቀሉ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጥ፣

3ኛ. በዘመቻችን ቀና ትብብርና መደጋገፍ የሚመለከተው ሁሉ እንዲያደርግልን ስንል ከዘመቻ ዝግጅታችን መሳ ለመሳ ትብብርና ድጋፍ እንጠይቃለን።

ለቀናት እየተደረገ በሚገኘው ጦርነት የሚጠበቅባችሁን እየፈፀማችሁ ለምትገኙ የህዝባችን ታማኝ ጀግና ልጆች ሁሉ ያለንን ክብር እያረጋገጥን በትንሽ ቀናት ውስጥ ከጎናችሁ ተሰልፈን የጠላትን ግፍና ዕኩይ ምኞት አክሽፈን ጦርነቱን በድል እንደምንቋጨው ጥርጥር የለንም።
390 views04:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 12:24:05
ወ*ያ*ኔ ዛሬ ያወጣው መግለጫ ነው።

መግለጫው ለኢትዮጵያና ለኤርትራ ህዝብ የተላለፈ ጥሪ ሲሆን የመግለጫው አንኳር ይዘት ባጭሩ .......
"የኢትዮጵያና የኤርትራ ጦሮች በጋራ ትግራይን ለመውረር ዝግጅት መጨረሳቸውን ተረድቻለሁ ፤ በመሆኑም እኛ ከኢትዮጵያና ከኤርትራ ህዝብ ጋር ጠብ የለንም፤ጠባችን ከአቢይ እና ከአማራ ክልል ጋር ብቻ መሆኑን ተረድታችሁ ይሄንን እኩይ የጥፋት ድግስ እንድታወግዙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን" ይላል ።
244 views09:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 09:14:54 አሁን ባለው መረጃ ወልዲያ ከተማ የገባ የወራሪ ኃይል አለመኖሩን ነዋሪዎች ነግረውኛል።የጥምር ጦሩ አባላት በከተማዋ የተለያየ ቦታ ይታያሉ።ዶሮ ግብር ላይ ግን ከፍተኛ የጨበጣ ውጊያ እየተካሄደ እንደሚገኝ ታውቋል (wasu)
385 views06:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 09:07:45 #ጥብቅ_መረጃ!

read &forward!!

አማርኛ በደንብ የሚችሉ ፣ ወታደር መስለው በግሩፕ እየሆኑ የመከላከያን ልብስ በመልበስ መንገድ ላይ የሚያገኙትን ሰው ልክ እንደ መከላከያ መስለው መረጃ እየጠየቁ የፈለጉት አገር በቀላሉ እየገቡ ነው። ታዲያ እግር መንገዳቸውን አለቃችን ጠፍቶን፣ ምግብ ጨርሰን እርቦን፣ ያልተያዘ ከተማ እከሌ ከተማ ተይዟል እያሉ ህዝብ እያሸበሩና እንዲፈናቀል እያደረጉ ነው። ያየያዙት መታወቂያ ጭምር በደንብ የተዘጋጁበት እንደሆነ ያስታውቃል። አንድን ስራ ሊሰሩ ሶስት አራት አማራጭ ነው የሚጠቀሙት። ዛሬ ወልድያና ሳንቃ ላይ ይሄን አድርገዋል። ነገር ግን ወልዲያም ሳንቃም ህዝቡ በእነሱ ወሬ ከመሸበሩ ውጭ መሳሪያ የተሸከመ ጁንታ አልገባም። መከላከያ አላውሀ እየተዋጋ ነው። ይሄ ተግባር ነገ ሀራና መርሳ ሌላም ቦታ መቀጠሉ አይቀርም። ትናንት ክምር ድንጋይ ላይ ተይዘዋል ዛሬ ደሴ ላይ በባጃጅ ተይዘዋል።

የመከላከያን ልብስ የለበሱ ከአስር እስከ 100 የሚደርሱ ሰዎች ተሹሎክልከው በየከተማው ቀድመው በመግባት መሪያችን ጠፍቶ ተበትነን እየመጣን ነው ይላሉ። ያገኙትን ሰው ሁሉ እንዲያዝንላቸውና የትራንስፖርት እየከፈለ እንዲሸኛቸው ሁሉ የሚያደርስ አሳማኝ ድራማ ይሠራሉ። ዋናው ዓላማቸው ግን ሽብር መንዛትና ሕዝቡ ላይ ከባድ የተስፋ መቁረጥ ስሜት በመፍጠር ለወገን ጦር ምንም ዓይነት እገዛ እንዳያደርግ ማስቻል ነው። በስላላ ከሰነበቱ በኋላ በቁርጡ ቀን አሰላለፋቸውን ቀይረው የባንዳ ሥራቸውን ይሠራሉ። በሁሉም አቅጣጫ ይህን ለማድረግ ሲሞክሩ የነበሩ በርካታ ባንዳዎች ወልዲያን ጨምሮ በበርካታ ከተሞች ተይዘዋል።

ለዚህ መፍትሄው ቀላል ነው። የየከተማው የመንግሥት መዋቅር ከዕዙ ተነጥሎ ተበተነኩ ብሎ የሚመጣ የመከላከያን ልብስ የለበሰ ሰው ሲያገኝ ወደ መከላከያ ካምፕ መመለስ አለበት። ቁጥራቸው ምንም ይሁን ምን ከተማ ለከተማ የሚዞር የወታደር ልብሰ የለበሰ ሰው መሉ መረጃው ተረጋገጦ በወታደራዊ ፖሊስ ተይዞ ወደ ካምፕ እንዲመለስ መደረግ አለበት።
406 views06:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 23:34:44
መንግሥት በአስቸኳይ የእርምት እርምጃ መውሰድ አለበት!
(ውብሸት ሙላት )

ያኔ በታሕሳስ፥ መከላከያ ሠራዊቱ በቆቦና በአካባቢው እንዲቆም የተደረገው በፖለቲካ ውሳኔ ነው፤ ሠራዊቱ የመንግሥትን ትዕዛዝ መቀበል ስላለበት። ጠላት በይፋ ልመጣ ነው እያለ እየተናገረም፣ እየመጣም እንደሆነ ማንም እያወቀ ለኹለተኛና ሦስተኛ ዙር ጥቃትና ጭፍጨፋ ሕዝባችን እንደተጋለጠ እየታወቀ መንግሥት የቀድሞ የታሕሳስ ውሳኔውን አላሻሻለም። እናም ሕዝባችን ይኼው ለስንተኛ ዙር በጠላት እየተጨፈጨፈ ነው።
ጦርነቱ እንኳን ሊያልቅ ይቅርና በጊዜያዊነትም ሳይቆም የድህረ ጦርነት ግምገማ እና ወሬ ውስጥ ተገባ። ለቆቦ ሕዝብም ስለ ድህረ ጦርነት፣ ለዋግ ሕዝብም ስለ ድህረ ጦርነት፣ ለወልዲያ ሕዝብም ስለ ድህረ ጦርነት ተወራ። ይህ የሆነውና የተደረገው ጦርነቱ ሊያልቅ ይቅርና ሳይቆም ነው!
ከዚያም ሕዝባችን ራሱን እንዳያደራጅ መንግሥት አፋዛዥነትን ሥራዬ ብሎ ተያይዞት ከረመ።
መንግሥት በአስቸኳይ የእርምት እርምጃ መውሰድ አለበት!
437 views20:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 23:05:42
(Assaye deribie)
413 views20:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 22:59:13
ዛሬ የመከላከያ ልብስ የለበሱ አለቃችን ጠፋን የሚሉ 300 ወታደሮች ክምር ድንጋይ ተይዘዋል።
አሁን ምሽት ስለሆነ ሰው መረጃ አያገኝም ተብሎ ያልሆነ መረጃ እየተሰራጨ ነው!!
አሉቧልታ መረጃ የሚያሰራጩ የተመደቡ የእኛ የሚመስሉ ሰወች በየቦታው አሉ።ከመሸ አለቃችን ጠፋን የሚሉ የመከላከያ ዩኒፎርም የለበሱ 300 ወታደሮች ጨጨሆን ጋይንትን አልፈው ክምር ድንጋይ ተይዘዋል።ሲፈተሹ ትግሬ ሁነው ተገኙ።የተላኩት ባህር ዳር ገብተው ሴክተር የመንግስት መስሪያቤቶችን መቆጣጠር እንደሆነ ከያዟቸው የስልክ ልውውጦች የተገኘው መረጃ አመላክቷል። ሌላም የዚህ አይነት ሙከራ አድርገው የተመለሱ እንዳሉ መረጃው አለኝ።
በየ ኬላው ያለው የፀጥታ ሁኔታ እና ፍተሻ መጠንከር አለበት።
አዩ ዘሀበሻ
412 views19:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 22:50:16
አሁንም አልረፈደም
መንግስት ትንሽ እረፋት ያገኘ መስሎት ለሀገሩ የተዋደቀውን ከ15 ሺ በላይ ፋኖ አስሯል፣ እጃቸውን ያልሰጡትንም ለመያዝ በርካታ ጥረቶችን አድርጓል። እያደረገም ይገኛል።

መንግስት በይፋ ፋኖን ይቅርታ ጠይቆ ፋኖም ሀገሩን ከወራሪ ያድን!
398 views19:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ