Get Mystery Box with random crypto!

ዶክተር X

የቴሌግራም ቻናል አርማ doctor_tena — ዶክተር X
የቴሌግራም ቻናል አርማ doctor_tena — ዶክተር X
የሰርጥ አድራሻ: @doctor_tena
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.34K
የሰርጥ መግለጫ

ለ ማንኛውም የህክምና ጥያቄ መጠየቅ ከፈለጉ በዶክተሮች የምክር አገልግሎት እንሰጣለን
@Doctortenabot

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-02-04 10:06:35 Hello dear friends,
Our startup company "LIT Health" has been selected to the next step of Total Energies - startupper of the Year competition.

LIT health is platform which books apppointments for clients to see any type of healthcare provider they wish . The service will also have an option of comparing pricing so the customer gets the best deals.

We need your votes to proceed to the next step. please give us a like by following these steps.
1) First click the link down below
https://click.experience.totalenergies.com/?qs=7f843af50a2a6d3c17b13f6faf9be0a474b2fbfb80a9d3ebe591b4c5ed9ac0cd1518d8a39fda043d3b70e7c99c8325cce36ad3ce53a25327
2) Then login (sign up) to the system using email and Verify (Confirm)
3) After login to the system go out from chrome and click the link https://click.experience.totalenergies.com/?qs=7f843af50a2a6d3c17b13f6faf9be0a474b2fbfb80a9d3ebe591b4c5ed9ac0cd1518d8a39fda043d3b70e7c99c8325cce36ad3ce53a25327 and vote for us.
7.0K viewsedited  07:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-01 22:55:04
LIT Health total energies startupper of the year ባዘጋጀው ውድድር ላይ ወደ ቀጣይ ዙር እንዲያልፍ ከታች ባለው መስፈንጠሪያ አካውንት በመክፈት like ያድርጉ!

LIT ጤና ለደንበኞች የሚፈልጉትን ማንኛውንም ዓይነት የጤና እንክብካቤ አቅራቢ ለማየት ቀጠሮ የሚሰጥበት መድረክ። አገልግሎቱ ደንበኛው ምርጡን ቅናሾች እንዲያገኝ ዋጋን የማወዳደር አማራጭ ይኖረዋል።
1. በመጀመሪያ ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ https://click.experience.totalenergies.com/?qs=7f843af50a2a6d3c17b13f6faf9be0a474b2fbfb80a9d3ebe591b4c5ed9ac0cd1518d8a39fda043d3b70e7c99c8325cce36ad3ce53a25327
2. ከዚያ ኢሜልን በመጠቀም ወደ ስርዓቱ ይግቡ ( ይመዝገቡ ) እና ያረጋግጡ ( አረጋግጥ )
3. ወደ ስርዓቱ ከገቡ በኋላ ከ chrome ውጡ እና ከታች ያለውን ሊንክ
https://click.experience.totalenergies.com/?qs=7f843af50a2a6d3c17b13f6faf9be0a474b2fbfb80a9d3ebe591b4c5ed9ac0cd1518d8a39fda043d3b70e7c99c8325cce36ad3ce53a25327
እንደገና ጠቅ ያድርጉ እና ከዚያ ድምጽ ይስጡን ወይንም ቦክሱ ላይ 'Ewnet Azeref' ወይም 'LIT Health' ብሎ በመፃፍ ፊት ለፊት በሚመጣው የድርጂታችንን ምርቶች በማየት ያድርጉን

Vote for #Dr.Ewnet

ለትብብሮ እናመሰግናለን!
Dr. Ewnet
7.5K views19:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-01 22:54:44
Hello dear friends,
Our startup company "LIT Health" has been selected to the next step of Total Energies - startupper of the Year competition.

LIT health is platform which books apppointments for clients to see any type of healthcare provider they wish . The service will also have an option of comparing pricing so the customer gets the best deals.

We need your votes to proceed to the next step. please give us a like by following these steps.
1) First click the link down below
https://click.experience.totalenergies.com/?qs=7f843af50a2a6d3c17b13f6faf9be0a474b2fbfb80a9d3ebe591b4c5ed9ac0cd1518d8a39fda043d3b70e7c99c8325cce36ad3ce53a25327
2) Then login (sign up) to the system using email and Verify (Confirm)
3) After login to the system go out from chrome and click the link https://click.experience.totalenergies.com/?qs=7f843af50a2a6d3c17b13f6faf9be0a474b2fbfb80a9d3ebe591b4c5ed9ac0cd1518d8a39fda043d3b70e7c99c8325cce36ad3ce53a25327 and vote for us.
6.5K views19:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-19 15:50:39 ሴቶች በእርግዝ ወቅት በብረት እጥረት በመከሰት ምክንያት በሚደርሰው የደም ማነስ ከፍተኛ የጤና ችግር ሊደርስባቸው እንደሚችል እና ይህንን የብረት እጥረትም በሚመገቡዋቸው ምግቦች ብቻ ሊያሙዋሉአቸው እንደማይችሉ ጥናቶች ያስረዳሉ፡፡ የአለም የጤና ድርጅት ባወጣው መመሪያ መሰረት በእርግዝና ላይ ያሉ ሴቶች ሁሉ 60mg iron እና 400μg folic  acid  ከመጀመሪያው ወር እርግዝና ጊዜ ጀምሮ በየቀኑ ለ6ወር ያህል መውሰድ አለባቸው፡፡ ይህም የእርግዝና ክትትል ከጀመሩበት ወይንም ከመጀመሪያው ወር የእርግዝና ጊዜ ጀምሮ መውሰድ አለባቸው፡፡  በእርግዝና ላይ ላሉ ሴቶች የደም ማነስ ከ40% በላይ የሚሆን ከሆነም የሚደረገው ድጋፍ ሊቀጥል ይገባዋል፡፡  
በእርግዝና ወቅት የሚያስፈልገውን ብረት እና ፎሊክ አሲድ በእርግዝና ክትትል ወቅት እንዲያገኙ ማድረግ ከሕክምና አገልግሎት ሰጪዎች የሚጠበቅ ነገር መሆኑን በማህጸንና ጽንስ ሐኪሞች ማህበር ጆርናል የወጣው መረጃ ያመላክታል፡፡
1.5K views12:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-19 15:50:39 በአለማችን ወደ 75% የሚሆኑ እርጉዞች Anemia ወይንም የደም ማነስ ያጋጠማቸው ሲሆን ይህም የ Folic Acid እና Iron እጥረትን የሚያመላክት ነው፡፡ ይህንን ችግር በሚመለከት ያለውን ሁኔታ የሚ ዳስስ ጥናት በአገራችን በተለይም በባህርዳር በፈለገሕይወት አጠቃላይ ሆስፒታል መካሄዱን የኢትዮያጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ያሳተመው ጆርናል  (EJRH) ላይ ተገልጾአል፡፡
April 1 እስከ August 30, 2019 በተደረገው የዳሰሳ ጥናት የእርግዝና ክትትል የሚያደርጉ 390 ያህል እርጉዝ ሴቶች የፎሊክ አሲድን እንዲያገኙ እድል ማግኘት አለማግኘታቸውን ተጠይ ቀው ወደ 67.4% የሚሆኑት የማግኘት እድሉ እንደነበራቸው ገልጸዋል፡፡ በጥናቱ እንደተገኘው ውጤትም  iron-folic  acid ን በማግኘት ረገድ ያላቸው እውቀት፤ ያገኙት የምክር አገልግ ሎት፤ የሚያደርጉት የእርግዝና ክትትል ትክክለኛነት እና የአይረንና ፎሊክ አሲድን እንዲያገኙ የመደረጉ ሂደት ተመልክቶአል፡፡
የደም ማነስ ሲባል ቀይ የደም ሴል ከትክክለኛው መጠን ማነሱን የሚያመለክት ነው። ቀይ የደም ሴል ኦክስጂንን የሚሸከመውን በአይረን የበለጸገ ፕሮቲንን እና ሄሞግሎቢንን የሚይዝ ጠቃሜታው ከፍተኛ የሆነ ተፈጥሮ ነው። ሰዎች በቂ የሆነ የቀይ የደም ሴል ከሌላቸው ወይ ንም እጥረት ሲገጥማቸው የትንፋሽ እጥረት፤የልብ ምት መፍጠን፤የንቃት ጉድለት ማጋጠም ወይንም ድብርት፤ የአቅም ማነስ የሚገጥማቸው ሲሆን ይህም የህክምና እርዳታ ካልተደረገ ላቸው የልብ ምት ሊቋረጥና ለአደጋ ሊጋለጡ ይችላሉ፡፡ ይህ ችግር ሊከሰት የሚችለውም በሰውነት ውስጥ በቂ የሆነ አይረን ፤ቫይታሚን ቢ 12 እና ፎሊክ አሲድ ሳይኖር ሲቀር ነው፡፡
በእርግዝና ጊዜ የአይረንና ፎሊክ አሲድ እጥረት የሚኖር ከሆነ በእርጉዝዋ ሴት ላይ የደም ማነስን እና ተያያዥ ችግሮችን የሚያስከትል ሲሆን በተረገዘው ጽንስ ላይም የነርቭና የጭን ቅላት ችግር ሊያስከትል እንደሚችል ማዮ ክሊኒክ ለንባብ ካቀረበው እና ቃና ቴሌቪዥን ሕይወቴ በተሰኘው ፕሮግራሙ ከዘገበው በመጠኑ ቀንጨብ አድርገናል፡፡    
በኢትዮጵያ በየአመቱ እስከ ሀያ ሺህ የሚደርሱ አዲስ የሚጸነሱ ህጻናት ለነርቭ ዘንግ ክፍተት ተጋላጭ  ይሆናሉ፡፡ የጭንቅላት ውስጥ ውሀ መቋጠርና የነርቭ ዘንግ ክፍተት የተባለውን ችግር የሚያስከትለው የፎሊክ አሲድ እጥረት ነው፡፡
የነርቭ ዘንግ ማለት በጀርባ በኩል የጭንቅላትና የህብረሰረሰር ነርቭ ሆኖ የሚያድግ ሲሆን ይህም የሚሆነው በእርግዝና ከ21ኛው እስከ 28ኛው ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ ነው፡፡
ይህ የነርቭ ዘንግ ከ21ኛው እስከ 28ኛው ቀን ድረስ መዘጋት የሚኖርበት ሲሆን ካልተዘጋ ግን የነርቭ ዘንግ ክፍተት በሽታን ያመጣል፡፡ ይህ በሽታ በአብዣኛው የሚፈጠረው እርግዝናው ከጀመረ በመጀመሪያው አንድ ወር ጊዜ ውስጥ ሲሆን በሽታው ከአንጎል ጀምሮ እስከ ህብረሰረሰር ድረስ ያለውን የሰውት ክፍል ያጠቃል፡፡ ሕመሙም በአብዛኛው የሚፈጠረው የፎሊክ አሲድ ወይንም የቫይታሚን ዲ እጥረት በሚከሰትበት ጊዜ ነው፡፡
የነርቭ ዘንክ ክፍተት ባለመዘጋቱ ምን ሊፈጠር ይችላል..
የታችኛው የነርቭ ዘንግ በማይዘጋበት ጊዜ በጀርባ ላይ በሚፈጠር ክፍተት የተነሳ Spina Bifida ስፓይናል ባይፊዳ የተባለ ሕመም ይፈጠራል፡፡ ሕመሙም ሊፈጠር የሚችለው በመጀ መሪያዎቹ አራት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ሲሆን በሰውት ውስጥ ያለው ህብለሰረሰር በትክክል ማደግ ሳይችል ሲቀር አከርካሪ ላይና የነርቭ ስርአት ላይ ዘላቂ የሆነ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል፡፡ ይህ ደግሞ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ሽባነትን ያስከትላል፡፡ በሽታው ያለባቸው ህጻናትም ሆኑ አዋቂዎች የሰገራ እና የሽንት መቆጣጠር ችግር በአብዛኛው ይታይባቸዋል።  ወይንም የጀርባ ላይ ክፍተት በአብዛዛኛው እንደ እባጭ ሆኖ በውጭው በጀርባ ላይ የሚታይ ሲሆን ይህ እባጭ ውሀ የሚቋጥር ሲሆን አንዳንድ ጊዜ ይህ እባጭ በስስ ቆዳ የተሸፈነ ቢሆንም ብዙውን ጊዜ  ግን የተጋለጠ ነው፡፡ በዚህ በሽታ የተጠቁ ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ እግርና እጃቸው የተጎዳ ይሆ ናል፡፡ ይህ በሽታ (Spina Bifida) ኖሮባቸው የሚወለዱ ህጻናት በጊዜ የቀዶ ሕክምና አገል ግሎት ሊያገኙ ይገባል፡፡
ከነርቭ ዘንግ ክፍተት ጋር ተያይዞ የሚመጣው ሌላው በሽታ Hydrocephalus የተባለው ሲሆን ይህም የጭንቅላት ውሀ መቋጠር ነው፡፡የህ በሽታ በጭንቅላት ውስጥ ያለው ውሀ በመጨመሩ ወይንም በመብዛቱ ምክንያት የሚከሰት በሽታ ነው፡፡ ይህ ችግር ከልጁ ጋር አብሮ ሊወለድ ወይንም ከተወለደ በሁዋላም ሊፈጠር ይችላል፡፡ፈሳሹ የሚመረተው በአንጎል ውስጥ  ባለ ሄሪይድ ፕሌክሲስ በተባለ እጢ ሲሆን የፈሳሹ በጭንቅላት ውስጥ መመረትና ስርገት አለመመጣጠን እንዲሁም የቱቦዎች መጥበብ የጭንቅላት ውስጥ ውሀ መቋጠርን ያመጣል፡፡ ይህ ችግር መፈጠሩን ከሚያመላክቱ ነገሮች መካከል በተለይም በጨቅላ ህጻናት የጭንቅላት ዙሪያ መጠን እየጨመረ መሄዱ ነው፡፡ ይህ በሽታ በእርግዝና ወቅት ወይንም ልጆች ከተወለዱ በሁዋላ በሚከሰት ኢንፌክሽን ምክንያትም ሊፈጠር ይችላል፡፡ ይህም በጊዜ ሕክምና ካልተደ ረገለት እራስን መሳትና ሞትንም ሊያስከትል ይችላል፡፡
ከላይ የተመለከታችሁዋቸው የተለያዩ የጤና ችግሮች መንስኤ የሆኑት በዋነኛነት በእርግዝና ጊዜ የሚኖረው የአይረንና የፎሊክ አሲድ እጥረት ነው፡፡ መረጃችን ያደረግነው (The Ethiopian Journal of Reproductive Health; 2021; 13; 1-10) የሚከተሉትን ነጥቦችም ያስነብባል፡፡
Anemia…የደም ማነስ፡-
የደም ማነስ በአለም አቀፍ ደረጃ ወደ 2 ቢሊዮን ያህል ሰዎችን የሚያጠቃ ህመም ነው፡፡ ከዚህ ቁጥር ውስጥ ወደ 41.8% የሚሆኑት እርጉዝ ሴቶች እና 30.2% የሚሆኑት እርጉዝ ያልሆኑ ሴቶች በአለም አቀፍ ደረጃ በህመሙ የሚሰቃዩ ናቸው፡፡
የደም ማነስ ሕመም ከባድ ጫናውን የሚያሳርፈው በአፍሪካ ባሉ እርጉዝ ሴቶች ላይ ነው፡፡
ከደም ማነስ ጋር በተያያዘ ከፍተኛው ማለትም ከአለም አቀፉ ወደ 57.1% የሚሆነውን የደም ማነስ የሚጋሩት በአፍሪካ ያሉ እርጉዝ ሴቶች ናቸው፡፡
ወደ ኢትዮጵያ ስንመለስ የደም ማነስ ሕመም በእርጉዝ ሴቶች ላይ ወደ 22% ሲሆን ይህም መካከለኛ የሚባል የህብረተሰብ ጤና ችግር ነው፡፡
Iron…ብረት፡-
የብረት ማነስ የደም ማነስን ለማስከተል አንዱና ዋናው አስተዋጽኦ የሚያደርግ ነው፡፡ በአለም አቀፍ ደረጃ 50% ለሚሆነው የደም ማነስና 75% ለሚሆነው በእርግዝና ጊዜ ለሚከሰተው የደም ማነስ ምክንያት ነው፡፡
የደም ማነስ ሕመም በማህበራዊና በኢኮኖሚያዊ ልማቶችን ወደ ሁዋላ በማስቀረት ትልቅ አስተዋጽኦ ያለው የጤና ችግር ነው። በእርግዝና ጊዜ በመጠነኛም ይሁን በከፍተኛ ደረጃ የደም ማነስ ችግር ማጋጠሙ በጽንሱም ላይ አንዳንድ ጉዳቶች ሊያስከትል ይችላል፡፡ ከሚደርሱ ጉዳቶችም መካከል ካለእድሜ መወለድ፤ዝቅተኛ ክብደት ያለው ልጅ መወለድ፤የእናት እና የልጅ ሞት እና ለኢንፌክሽን ሊያጋልጥ ይችላል።
 በተጨማሪም የጽንሱን እድገት በማህጸን ውስጥ እና ከተወለደም በሁዋላ ለረጅም ጊዜ ሊያስተጉዋጉል ወይንም እንደተፈለገው እንዳይሆን ሊያ ደርግ ይችላል፡፡
1.4K views12:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-19 15:50:36 Folic Acid--Iron….በእርግዝና ወቅት

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
1.2K views12:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-16 18:41:16 3 ለጤናችን እጅግ በጣም ጠቃሚ ነገሮች

1/ዘዉትር የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ
2/ ጤናማ የአመጋገብ ስርዓት መከተል
3/ ዘዉትር በቂ እንቅልፍ መተኛት
1.5K views15:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-15 09:18:22
ኢትዮጵያ በአንደኝነት ያሸነፈቺው #ስንተኛዉን #የአፍሪካ #ዋንጫ ነው?
Anonymous Quiz
26%
አንደኛዉን የአፍሪካ ዋንጫ 1957 እ.ኤ.አ
17%
ሁለተኛዉን የአፍሪካ ዋንጫ 1959 እ.ኤ.አ
42%
ሶስተኛውን የአፍሪካ ዋንጫ 1962 እ.ኤ.አ
14%
አራተኛዉን የአፍሪካ ዋንጫ 1963 እ.ኤ.አ
2.8K voters1.3K views06:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-12 12:07:07
በሰዉነታችን ዉስጥ በጣም ትንሽ አጥንት ያለው :-
Anonymous Quiz
9%
በጣቶቻችን
70%
በጆሮዎቻቺን
14%
በአፍንጫችን
7%
በአንገታችን
4.4K voters25.5K views09:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-02 10:51:01 ጥያቄ፦ሰላም ዶክተር ስሜ sulu ይባላል መጠየቅ የምፈልገው ሙዝ ስበላ ያንደበድበኛል ፊቴ ያብጣል ያሳከኛል
መልስ

አለርጂ ምንድን ነው?

አለርጂ ራሱን የቻለ መንስኤ ያለው የጤና ችግር ነው፡፡ በህዋስም ሆነ በንጥረ ነገር መልክ ወደ ሰውነታችን በሚገቡ ነገሮች የሰውነታችን የመከላከያ ኃይል ከመደበኛው (ከሚጠበቀው) በላይ ምላሽ ሲሰጥ የሚፈጠር ክስተት ነው፡፡
በየትኛውም መንገድ ይሁን ወደ ሰውነታችን የሚገቡ ባዕድ ነገሮችን ለመከላከል ወይም ለማጥፋት የሚያስችሉ ንጥረ ነገሮች (anti body) ማንጨት የሰውነታችን በሽታን የመከላከል ስርዓት ቀዳሚ ተግባር ነው፡፡ ይህ ስርዓት ብዙውን ጊዜ የሚጠበቅበትን ተግባር የሚያከናውን ቢሆንም፣ አንዳንድ ጊዜ ውስጣዊና ውጫዊ ምክንያቶች በሚፈጥሩት ተፅኖ ሳቢ፣ ጎጂዎችንና ጠቃሚ ሴሎችን በጅምላ በማጥፋት ከመጠን በላይ የሆነ እርምጃ ይወስዳል፡፡ የሰውነት በሽታ የመከላከል ስርዓት አንዳንድ ጊዜ የራሳችንን አካል ክፍሎች ለምሳሌ ኩላሊትን፣ ልብን፣ መገጣሚያንና የአካል ንቅለ ተከላ ሲደረግ እንደ ባዕድ በመቁጠር ያጠቃል፡፡ በዚህ ጊዜ ከሚፈጠሩ ችግሮች አንዱና ዋነኛው አለርጂ ነው፡፡
ለአለርጂ አጋላጭ ምክንያቶች ምንድን ናቸው?
ማንኛውም ሰው በየትኛውም ጊዜና ሰዓት አለርጂ በሚፈጠሩ የጤና ችግሮች የመጋለጥ ዕድል አለው፡፡ ለዚህ ችግር የሚያጋልጡ በርካታ ምክንያቶች አሉ፡፡
* የተለያዩ የምግብ አይነቶች
አለርጂን በማምጣት የሚታወቁ የምግብ አይነቶች አሉ፡፡ እነዚህም ወተትና የወተት ተዋፅኦዎች፣ ዓሳና ዓሳ ነክ ምግቦች፣ እንቁላል፣ ተለያዩ የኦቾሎኒ አይነቶች፣ አኩሪ አተርና ምግብን ለማጣፈጥ ወይም ለረጅም ጊዜ ለማቆየት ተብለው የሚጨምሩ ንጥረ ነገሮች እንዲሁም በመድሃኒት ውስጥ የሚጨመሩ ኬሚካሎችና በፋብሪካ የታሸጉ ምግቦች ለአለርጂ የማጋለጥ እድላቸው ሰፊ ነው፡፡
ሁሉም ሰው ለአንድ አይነት መድሃኒት አላርጂ ነው ማለት ባይቻልም፣ ለተለያዩ የህመም አይነቶች የሚሰጡ መድሃኒቶች ለአለርጂ መከሰት ምክንያት ይሆናሉ፡፡
* በኬሚካል ማምረቻዎች የሚሰሩ
ለአረም ማጥፊያ ኬሚካሎች ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች እንዲሁም አቧራ፣ የዕፅዋት ብናኝ፣ ቀዝቃዛ የአየር ፀባይና ከቤት ውስጥ እንስሳት ጋር የዕለት ተዕለት ግንኙነት የሚያደርጉ ሰዎች ለአለርጂ ተጋላጭ የመሆን ዕድል አላቸው፡፡
ነገር ግን ሁሉም ሰው ለአንድ አይነት ጉዳይ በተመሳሳይ ጊዜና ቦታ አለርጂ ይሆናል ማለት አይደለም፡፡ ምክንያቱም ለአንዱ አለርጂ የሆነ ጉዳይ ለሌላው ላይሆን የሚችልበት ሁኔታ ሰፊ በመሆኑ ነው፡፡

አለርጂ በአብዛኛው የሚከሰተው በየትኛው የሰውነት ክፍል ነው ?
ቆዳ ጋር ባለ ንኪኪ ቆዳ ላይ ይከሰታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ
• በዓይን፣
• በአፍንጫ፣
• በአፍ፣
• በመተንፈሻ አካላትና በአንጀት አካባቢ ይከሰታል፡፡
አለርጂ ሲከሰት የሚታዩ ምልክቶች
አለርጂ ሲከት የተለያዩ ምልክቶችን የሚያሳይ ሲሆን፣ አለርጂው እንደሚከሰትበት ቦታ የሚታዩ ምልክቶችም የተለያዩ ናቸው፡፡

* ዓይን አካባቢ ሲከሰት ማሳከክ፣ መቅላት፣ ማበጥ፣ ህመም፣ ፣ ቶሎ ቶሎ እንባ መፍሰስና ብርሃን ማየት መፍራት ይከሰታል፡፡

* አፍንጫ እና የመተንፈሻ አካላት አካባቢ ሲከሰት፡- ቀጭን ውሃ መሳይ ንፍጥ፣ ማስነጠስ፣ የአፍንጫ መደፈን፣ ማሳከክ፣ ማሳል፣ የመተንፈሻ አካላት እብጠትና ውሃ መቋጠር፣ ፈሳሽ መብዛት፣ የአየር መታፈን፣ ፣ ስር ስር የሚል ድምፅ ሊከሰት ይችላል፡፡

*ከምንመገበውና ከምንጠጣው ምግብ ጋር አለርጂ ሲከሰት፡- አፍና ከንፈር ማበጥ፣ ምግብ ለመዋጥ መቸገር፣ ጉረሮ አካባቢ ህመምን ጨምሮ ማቅለሽለሽ፣ ማስታወክ፣ ተቅማጥና የሆድ አካባቢ ህመም ይከሰታል፡፡

*ከንክኪ ጋር በተያያዘ ቆዳ ላይ ሲከሰት፣ ማሳከክ፣ መቅላት፣ ሽፍታ እና ማበጥ ናቸው፡፡
አለርጂ ሲከሰት የሚያሳያቸው ምልክቶች ቀለል ያሉ ቢመስሉም ራስን ከመሳት እስከ ሞት ድረስ ሊያደርስ የሚችል በሽታ እንደሆነ መገንዘብ ጠቃሚ ነው፡፡ በአንድ ይሁን በሌላ ምክንያት የሚፈጠር አላርጅ፣ ተገቢውን ህክምና ከተደረገለት በኋላ የሚድን ቢሆንም ተመልሶ የመምጣት ዕድሉ ሰፊ ነው፡፡
ምንጭ#ዶክተር አለ
ማንኛውም የህክምና ጥያቄ መጠየቅ ከፈለጉ በዶክተሮች የምክር አገልግሎት እንሰጣለን
@doctorTalksT
3.3K views07:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ