Get Mystery Box with random crypto!

በአለማችን ወደ 75% የሚሆኑ እርጉዞች Anemia ወይንም የደም ማነስ ያጋጠማቸው ሲሆን ይህም የ | ዶክተር X

በአለማችን ወደ 75% የሚሆኑ እርጉዞች Anemia ወይንም የደም ማነስ ያጋጠማቸው ሲሆን ይህም የ Folic Acid እና Iron እጥረትን የሚያመላክት ነው፡፡ ይህንን ችግር በሚመለከት ያለውን ሁኔታ የሚ ዳስስ ጥናት በአገራችን በተለይም በባህርዳር በፈለገሕይወት አጠቃላይ ሆስፒታል መካሄዱን የኢትዮያጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ያሳተመው ጆርናል  (EJRH) ላይ ተገልጾአል፡፡
April 1 እስከ August 30, 2019 በተደረገው የዳሰሳ ጥናት የእርግዝና ክትትል የሚያደርጉ 390 ያህል እርጉዝ ሴቶች የፎሊክ አሲድን እንዲያገኙ እድል ማግኘት አለማግኘታቸውን ተጠይ ቀው ወደ 67.4% የሚሆኑት የማግኘት እድሉ እንደነበራቸው ገልጸዋል፡፡ በጥናቱ እንደተገኘው ውጤትም  iron-folic  acid ን በማግኘት ረገድ ያላቸው እውቀት፤ ያገኙት የምክር አገልግ ሎት፤ የሚያደርጉት የእርግዝና ክትትል ትክክለኛነት እና የአይረንና ፎሊክ አሲድን እንዲያገኙ የመደረጉ ሂደት ተመልክቶአል፡፡
የደም ማነስ ሲባል ቀይ የደም ሴል ከትክክለኛው መጠን ማነሱን የሚያመለክት ነው። ቀይ የደም ሴል ኦክስጂንን የሚሸከመውን በአይረን የበለጸገ ፕሮቲንን እና ሄሞግሎቢንን የሚይዝ ጠቃሜታው ከፍተኛ የሆነ ተፈጥሮ ነው። ሰዎች በቂ የሆነ የቀይ የደም ሴል ከሌላቸው ወይ ንም እጥረት ሲገጥማቸው የትንፋሽ እጥረት፤የልብ ምት መፍጠን፤የንቃት ጉድለት ማጋጠም ወይንም ድብርት፤ የአቅም ማነስ የሚገጥማቸው ሲሆን ይህም የህክምና እርዳታ ካልተደረገ ላቸው የልብ ምት ሊቋረጥና ለአደጋ ሊጋለጡ ይችላሉ፡፡ ይህ ችግር ሊከሰት የሚችለውም በሰውነት ውስጥ በቂ የሆነ አይረን ፤ቫይታሚን ቢ 12 እና ፎሊክ አሲድ ሳይኖር ሲቀር ነው፡፡
በእርግዝና ጊዜ የአይረንና ፎሊክ አሲድ እጥረት የሚኖር ከሆነ በእርጉዝዋ ሴት ላይ የደም ማነስን እና ተያያዥ ችግሮችን የሚያስከትል ሲሆን በተረገዘው ጽንስ ላይም የነርቭና የጭን ቅላት ችግር ሊያስከትል እንደሚችል ማዮ ክሊኒክ ለንባብ ካቀረበው እና ቃና ቴሌቪዥን ሕይወቴ በተሰኘው ፕሮግራሙ ከዘገበው በመጠኑ ቀንጨብ አድርገናል፡፡    
በኢትዮጵያ በየአመቱ እስከ ሀያ ሺህ የሚደርሱ አዲስ የሚጸነሱ ህጻናት ለነርቭ ዘንግ ክፍተት ተጋላጭ  ይሆናሉ፡፡ የጭንቅላት ውስጥ ውሀ መቋጠርና የነርቭ ዘንግ ክፍተት የተባለውን ችግር የሚያስከትለው የፎሊክ አሲድ እጥረት ነው፡፡
የነርቭ ዘንግ ማለት በጀርባ በኩል የጭንቅላትና የህብረሰረሰር ነርቭ ሆኖ የሚያድግ ሲሆን ይህም የሚሆነው በእርግዝና ከ21ኛው እስከ 28ኛው ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ ነው፡፡
ይህ የነርቭ ዘንግ ከ21ኛው እስከ 28ኛው ቀን ድረስ መዘጋት የሚኖርበት ሲሆን ካልተዘጋ ግን የነርቭ ዘንግ ክፍተት በሽታን ያመጣል፡፡ ይህ በሽታ በአብዣኛው የሚፈጠረው እርግዝናው ከጀመረ በመጀመሪያው አንድ ወር ጊዜ ውስጥ ሲሆን በሽታው ከአንጎል ጀምሮ እስከ ህብረሰረሰር ድረስ ያለውን የሰውት ክፍል ያጠቃል፡፡ ሕመሙም በአብዛኛው የሚፈጠረው የፎሊክ አሲድ ወይንም የቫይታሚን ዲ እጥረት በሚከሰትበት ጊዜ ነው፡፡
የነርቭ ዘንክ ክፍተት ባለመዘጋቱ ምን ሊፈጠር ይችላል..
የታችኛው የነርቭ ዘንግ በማይዘጋበት ጊዜ በጀርባ ላይ በሚፈጠር ክፍተት የተነሳ Spina Bifida ስፓይናል ባይፊዳ የተባለ ሕመም ይፈጠራል፡፡ ሕመሙም ሊፈጠር የሚችለው በመጀ መሪያዎቹ አራት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ሲሆን በሰውት ውስጥ ያለው ህብለሰረሰር በትክክል ማደግ ሳይችል ሲቀር አከርካሪ ላይና የነርቭ ስርአት ላይ ዘላቂ የሆነ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል፡፡ ይህ ደግሞ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ሽባነትን ያስከትላል፡፡ በሽታው ያለባቸው ህጻናትም ሆኑ አዋቂዎች የሰገራ እና የሽንት መቆጣጠር ችግር በአብዛኛው ይታይባቸዋል።  ወይንም የጀርባ ላይ ክፍተት በአብዛዛኛው እንደ እባጭ ሆኖ በውጭው በጀርባ ላይ የሚታይ ሲሆን ይህ እባጭ ውሀ የሚቋጥር ሲሆን አንዳንድ ጊዜ ይህ እባጭ በስስ ቆዳ የተሸፈነ ቢሆንም ብዙውን ጊዜ  ግን የተጋለጠ ነው፡፡ በዚህ በሽታ የተጠቁ ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ እግርና እጃቸው የተጎዳ ይሆ ናል፡፡ ይህ በሽታ (Spina Bifida) ኖሮባቸው የሚወለዱ ህጻናት በጊዜ የቀዶ ሕክምና አገል ግሎት ሊያገኙ ይገባል፡፡
ከነርቭ ዘንግ ክፍተት ጋር ተያይዞ የሚመጣው ሌላው በሽታ Hydrocephalus የተባለው ሲሆን ይህም የጭንቅላት ውሀ መቋጠር ነው፡፡የህ በሽታ በጭንቅላት ውስጥ ያለው ውሀ በመጨመሩ ወይንም በመብዛቱ ምክንያት የሚከሰት በሽታ ነው፡፡ ይህ ችግር ከልጁ ጋር አብሮ ሊወለድ ወይንም ከተወለደ በሁዋላም ሊፈጠር ይችላል፡፡ፈሳሹ የሚመረተው በአንጎል ውስጥ  ባለ ሄሪይድ ፕሌክሲስ በተባለ እጢ ሲሆን የፈሳሹ በጭንቅላት ውስጥ መመረትና ስርገት አለመመጣጠን እንዲሁም የቱቦዎች መጥበብ የጭንቅላት ውስጥ ውሀ መቋጠርን ያመጣል፡፡ ይህ ችግር መፈጠሩን ከሚያመላክቱ ነገሮች መካከል በተለይም በጨቅላ ህጻናት የጭንቅላት ዙሪያ መጠን እየጨመረ መሄዱ ነው፡፡ ይህ በሽታ በእርግዝና ወቅት ወይንም ልጆች ከተወለዱ በሁዋላ በሚከሰት ኢንፌክሽን ምክንያትም ሊፈጠር ይችላል፡፡ ይህም በጊዜ ሕክምና ካልተደ ረገለት እራስን መሳትና ሞትንም ሊያስከትል ይችላል፡፡
ከላይ የተመለከታችሁዋቸው የተለያዩ የጤና ችግሮች መንስኤ የሆኑት በዋነኛነት በእርግዝና ጊዜ የሚኖረው የአይረንና የፎሊክ አሲድ እጥረት ነው፡፡ መረጃችን ያደረግነው (The Ethiopian Journal of Reproductive Health; 2021; 13; 1-10) የሚከተሉትን ነጥቦችም ያስነብባል፡፡
Anemia…የደም ማነስ፡-
የደም ማነስ በአለም አቀፍ ደረጃ ወደ 2 ቢሊዮን ያህል ሰዎችን የሚያጠቃ ህመም ነው፡፡ ከዚህ ቁጥር ውስጥ ወደ 41.8% የሚሆኑት እርጉዝ ሴቶች እና 30.2% የሚሆኑት እርጉዝ ያልሆኑ ሴቶች በአለም አቀፍ ደረጃ በህመሙ የሚሰቃዩ ናቸው፡፡
የደም ማነስ ሕመም ከባድ ጫናውን የሚያሳርፈው በአፍሪካ ባሉ እርጉዝ ሴቶች ላይ ነው፡፡
ከደም ማነስ ጋር በተያያዘ ከፍተኛው ማለትም ከአለም አቀፉ ወደ 57.1% የሚሆነውን የደም ማነስ የሚጋሩት በአፍሪካ ያሉ እርጉዝ ሴቶች ናቸው፡፡
ወደ ኢትዮጵያ ስንመለስ የደም ማነስ ሕመም በእርጉዝ ሴቶች ላይ ወደ 22% ሲሆን ይህም መካከለኛ የሚባል የህብረተሰብ ጤና ችግር ነው፡፡
Iron…ብረት፡-
የብረት ማነስ የደም ማነስን ለማስከተል አንዱና ዋናው አስተዋጽኦ የሚያደርግ ነው፡፡ በአለም አቀፍ ደረጃ 50% ለሚሆነው የደም ማነስና 75% ለሚሆነው በእርግዝና ጊዜ ለሚከሰተው የደም ማነስ ምክንያት ነው፡፡
የደም ማነስ ሕመም በማህበራዊና በኢኮኖሚያዊ ልማቶችን ወደ ሁዋላ በማስቀረት ትልቅ አስተዋጽኦ ያለው የጤና ችግር ነው። በእርግዝና ጊዜ በመጠነኛም ይሁን በከፍተኛ ደረጃ የደም ማነስ ችግር ማጋጠሙ በጽንሱም ላይ አንዳንድ ጉዳቶች ሊያስከትል ይችላል፡፡ ከሚደርሱ ጉዳቶችም መካከል ካለእድሜ መወለድ፤ዝቅተኛ ክብደት ያለው ልጅ መወለድ፤የእናት እና የልጅ ሞት እና ለኢንፌክሽን ሊያጋልጥ ይችላል።
 በተጨማሪም የጽንሱን እድገት በማህጸን ውስጥ እና ከተወለደም በሁዋላ ለረጅም ጊዜ ሊያስተጉዋጉል ወይንም እንደተፈለገው እንዳይሆን ሊያ ደርግ ይችላል፡፡