Get Mystery Box with random crypto!

ሴቶች በእርግዝ ወቅት በብረት እጥረት በመከሰት ምክንያት በሚደርሰው የደም ማነስ ከፍተኛ የጤና ችግ | ዶክተር X

ሴቶች በእርግዝ ወቅት በብረት እጥረት በመከሰት ምክንያት በሚደርሰው የደም ማነስ ከፍተኛ የጤና ችግር ሊደርስባቸው እንደሚችል እና ይህንን የብረት እጥረትም በሚመገቡዋቸው ምግቦች ብቻ ሊያሙዋሉአቸው እንደማይችሉ ጥናቶች ያስረዳሉ፡፡ የአለም የጤና ድርጅት ባወጣው መመሪያ መሰረት በእርግዝና ላይ ያሉ ሴቶች ሁሉ 60mg iron እና 400μg folic  acid  ከመጀመሪያው ወር እርግዝና ጊዜ ጀምሮ በየቀኑ ለ6ወር ያህል መውሰድ አለባቸው፡፡ ይህም የእርግዝና ክትትል ከጀመሩበት ወይንም ከመጀመሪያው ወር የእርግዝና ጊዜ ጀምሮ መውሰድ አለባቸው፡፡  በእርግዝና ላይ ላሉ ሴቶች የደም ማነስ ከ40% በላይ የሚሆን ከሆነም የሚደረገው ድጋፍ ሊቀጥል ይገባዋል፡፡  
በእርግዝና ወቅት የሚያስፈልገውን ብረት እና ፎሊክ አሲድ በእርግዝና ክትትል ወቅት እንዲያገኙ ማድረግ ከሕክምና አገልግሎት ሰጪዎች የሚጠበቅ ነገር መሆኑን በማህጸንና ጽንስ ሐኪሞች ማህበር ጆርናል የወጣው መረጃ ያመላክታል፡፡