Get Mystery Box with random crypto!

የቀድሞው የትግራይ ገዢ ፓርቲና በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አሸባሪ ተብሎ የተፈረደው ህወሓት መቐለ ከ | ድሬ Tube™

የቀድሞው የትግራይ ገዢ ፓርቲና በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አሸባሪ ተብሎ የተፈረደው ህወሓት መቐለ ከተማ መቆጣጠሩን ማምሻውን አስታውቋል

የህወሓት ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ፥ "የትግራይ ዋና ከተማ መቐለ በቁጥጥራችን ሥር ነች" ሲሉ ለሬውተርስ ተናግረዋል።

በከተማው የሚገኘው ኤፍ.ኤም መቐለ ራዲዮ ጣቢያ ተቋርጦ የነበረ ሥርጭቱን መጀመሩ ታውቋል።

የራዲዮ ጣቢያው "ከዚህ ቀደም ይደመጡ ያልነበሩ እና የትግራይ ኃይሎችን የሚያወድሱ ሙዚቃዎች" በማሰማት ላይ እንደሚገኝ የጀርመን ሬድዮ ከመቐለ ዘግቧል።

"የትግራይ መከላከያ ኃይል" ተብሎ የሚጠራው ታጣቂ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ መቐለ ከተማ መግባቱን የከተማዋ ነዋሪዎች አረጋግጠዋል።

የመቐለ ከተማ አስተዳደር በሚገኝበት አካባቢ እንዲሁም አዋሽ ካምፕ ተብሎ የሚጠራው የቀድሞ የሰሜን ዕዝ የጦር ሰፈር አካባቢ ታጣቂዎቹ ታይተዋል።

ሁለት የከተማዋ ነዋሪዎች እንዳሉት በመቐለ የተለያዩ ቦታዎች ማምሻውን አልፎ አልፎ የተኩስ ይሰማ ነበር።

የተሽከርካሪዎች ጥሩምባና የርችት ተኩስ አሁንም እየተሰማ እንደሚገኝ የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ከመቐለ ዘግቧል።

@diretube0