Get Mystery Box with random crypto!

በምርጫው ብልጽግና ፓርቲ ካሸነፈ ተፎካካሪ ፓርቲዎችን እንደተሳትፏቸው በመንግስት መዋቅር ውስጥ ውክ | ድሬ Tube™

በምርጫው ብልጽግና ፓርቲ ካሸነፈ ተፎካካሪ ፓርቲዎችን እንደተሳትፏቸው በመንግስት መዋቅር ውስጥ ውክልና እንዲኖራቸው ያደርጋል-ጠ/ሚ ዐቢይ

ብልጽግና ፓርቲ በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ የሚያሸንፍ ከሆነ በምርጫ የተሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደ ተሳትፏቸው ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ የመንግስት መዋቅር ውስጥ ውክልና ወይም ተሳትፎ እንዲኖራቸው እንደሚያደርግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ፡፡

የምርጫ ውጤቱ በተቃራኒ ሆኖ ብልጽግና ፓርቲ የሚሸነፍ ከሆነም የኢትዮጵያን አሸናፊነት ለማረጋገጥ መንግስት ለአሸናፊው የፖለቲካ ፓርቲ ስልጣኑን በሰላማዊ መንገድ እንደሚያስረክብም ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒትሩ ይህን ያሉት የኢትዮጵያ ሲቪክ ማህበራት ድርጅቶች ምክር ቤት “ኢትዮጵያ አሸንፋለች እና እናመሰግናችኋለን” በሚል ባዘጋጀው የምስጋና ፕሮግራም ላይ ነው፡፡

በምርጫው እለት ዜጎች ኢትዮጵያ አሸናፊ እንድትሆን ወጥተው ድምፅ በመስጠታቸውም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ኢትዮጵያዊያን ከፖለቲካ ይልቅ አገር ትቀድማለች የሚል መርህ አንግበው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ በማካሄድ አገራቸውን አሸናፊ አድርገዋልም ነው ያሉት።

@diretube0