Get Mystery Box with random crypto!

በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሩ ዞን 27 የጸጥታ ኃይሎች በታጣቂዎች ተገደሉ በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድ | ድሬ Tube™

በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሩ ዞን 27 የጸጥታ ኃይሎች በታጣቂዎች ተገደሉ

በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሩ ዞን ጃርደጋ ጃርቴ ወረዳ 27 የጸጥታ ኃይሎች ትናንት ሐሙስ በታጣቂዎች መገደላቸውን የወረዳው አስተዳዳሪ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። የጃርደጋ ጃርቴ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አብዮት በቀለ እንዳሉት ከተገደሉት የጸጥታ ኃይሎች በተጨማሪ 10 የፌደራል ፖሊስ አባላት ጉዳት ደርሶባቸዋል።

በጸጥታ ኃይሎቹ ላይ ጥቃቱ የተነሰዘረው ከጠዋቱ 1 ሰዓት ገደማ እንደሆነ የሚገልጹት አቶ አብዮት፤ ድርጊቱ የተፈጸመው በአካባቢው ይንቀሳቀሳሉ የተባሉ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎችን በማሰስ ላይ ባሉበት ወቅት እንደነበር ይናገራሉ። የጸጥታ ኃይሎቹ በሁለት ዙር ወደ አካባቢው መንቀሳቀሳቸውን የሚያስረዱት ዋና አስተዳዳሪው፤ ጥቃቱ የተሰዘረው በመጀመሪያው ዙር በተጓዙ 47 የፌደራል ፖሊስ እና ሁለት የሚሊሺያ አባላት ላይ ነው ብለዋል።

ከስምንት አመታት በላይ ያገለገሉ እና ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ሁለት ሚሊሺያዎች በበኩላቸው ትናንት ሐሙስ ሰኔ 3፤ አካዩ ቀበሌ በተባለ ቦታ በተፈጸመው ጥቃት 24 የጸረ ሽብር ፖሊስ እና ሁለት የሚሊሺያ አባላት፤ በድምሩ 27 የጸጥታ ኃይሎች መገደላቸውን ተናግረዋል።

@diretube0