Get Mystery Box with random crypto!

የሰናፍጭ ቅንጣት 🤓🧐😎

የቴሌግራም ቻናል አርማ deressereta — የሰናፍጭ ቅንጣት 🤓🧐😎
የቴሌግራም ቻናል አርማ deressereta — የሰናፍጭ ቅንጣት 🤓🧐😎
የሰርጥ አድራሻ: @deressereta
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 189
የሰርጥ መግለጫ

የሞተ ነገር አለማንሳት፣ ያየነውን ግን በጥልቀት መመልከት፣በከፍታ መብረር ባህሪያችን ነው። ለተግዳሮት እጅ አንሰጥም።
እኛም እንደ ንስር በከፍታ፣ ከተለመደው ውጭ፣ በቀና አስተሳሰብ፣ በበጎነት ተግባር፣ እንድትበሩ እንተጋለን። ከበጎነት የተሻለ በጎ ነገር የለም።
ኋይላችን እንደ አንበሳ እይታችን እንደ ንስር ነው። ለአገራችን እና ለወገናችን የሰናፍጭ ቅንጣትም ያህል ቢሆን በጎ አስተዋጽኦ እናደርጋለን።

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-10 06:25:00
ማህበራዊ ሚዲያ ተቀላቀልኩ ጊዜው አጭር አይደለም። ነገር ግን አጠቃቀሙን ብዙም አይደለሁም።

ለዚህም መሰለኝ ብዙ ተከታይ የሌለኝ።

ተከታይ ያለመኖሩ ያለመብዛቱ like share comment የሚያደርግ ሰው ቁጥር እጅግም አያስጨንቀኝም።

ነገር ግን ሁሌም የሚያስጨንቀኝ ዛሬ ለራሴ ምን ጥሩ ነገር ልንገረው የሚለው ነገር ነው፤

ነገ ሰወች ወደ ሕይወቴ፣ አካውንቴ፣ መልዕክቴ ሲመጡ አያፍሩም፤ ሁሉ ሙሉ ሁሉ ዝግጁ ነውና።

ከፌስቡክ፣ ወደ ትዊተር፣ ቴሌግራም፣ ቲክቶክ፣ ከዛም ወደ ኢንስታግራም እየተቀላቀልኩ መጣሁ። አሁንም ሰወች ወደኔ አልመጡም፥ አንድ የገባኝ ነገር እኔ የጎደለብኝ ነገር ሳይኖር እነርሱ የፈጠርኩላቸውን እድል አለመጠቀማቸው ነው የሚታየኝ።

በእርግጥ ወደኔ ከሚመጡት የማገኘው ነገር ቢኖርም እኔ ግን የማውቀው ያጣሁት ነገር የለም። ያልመጡት ግን የተዘጋጀላቸውን አጥተዋልና። እኔ ግን ለቤቴ ለሕይወቴ ለአካውንቴ ለተከታዮቼ የሚሆነውን የሚመጥነውን ዛሬም አስባለሁ፣ አዘጋጃለሁ፣ እለጥፋለሁ።

ለሚመጡት እድል እየፈጠርኩ እንደሆነ ይሰማኛል።

ልዩነት እየፈጠርኩም እንደሆነ አምናለሁ።

አንድም ሰው እዚህ ገጽ ላይ ገብቶ አንዱንም አይረባም እንደማይል አምናለሁ። አንዱን ከአንዱ ያበላልጥ እንደሆነ እንጂ። የተከታዮቼን ማነስ አይቶ ይንቀኝ እንደሆነ እንጂ የተለጠፉትን አይቶ አንዳችም እንከን አያወጣልኝም።

ለምን?

ለዛሬ አልሰራም።

ለነገ እንጂ። ትውልድ የሚረከብ፣ ትውልድ የሚያሸጋግር ስራ ነውና የምሰራው።

ኑ ወደ ጓዳዬ ዝለቁ ከመአዴም ተቋደሱ። ደስም ይበላችሁ። ነፍሳችሁም ትርካ ስጋችሁም ይረፍ። አዕምሯችሁ እንዲህም አለንዴ ብሎ ይደነቅ፤ ያድንቅ።

@t.me/deressereta
51 viewsEagel view R.E, 03:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 12:52:40 ለዚህ ግሩፕ አባላት የእስልምና እምነት ተከታይ ጓደኞቼ በሙሉ እንኳን ለአረፋ በአል በሰላም አደረሳችሁ። መልካም በአል ከመላው ቤተሰቦቻችሁ ጋር
54 viewsEagel view R.E, 09:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 19:10:47 አሸናፊነት

"መጀመሪያ እንድትሸነፍ የሚያደርጉህን ምክንያትህን አሸንፍ"

ጀግናችን አበበ ቢቂላ በባዶ እግሩ ሮጦ ጀግንነትን ከመቀዳጀቱ በፊት 35ኪሎ ሜትር እንደሮጠ ሆዱን አመመው፤ ይኽም ሕመም ሩጫውን እንዲያቋርጥ ሊያደርገው ከጫፍ የደረሰውን ውሳኔ እንዲቀይር ያደረገው ከላይ የጠቀስኩት የአለቃው ምክር ነበረ።

የድል ምልክታችን አበበም ወደ ልቡ ተመልሶ ሕመሙን ችላ አለው። ሩጫውን ቀጠል፤ ዛሬ የምንኮራበትን ድል አስመዘገበ። አበበን ለድል ያበቃው በዓለም አደባባይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ እንዲውለበለብ ያስቻለው ሕመሙን ማሸነፉ ነው።

እኛም እንዳናሸንፍ የሚያደርጉን፣ የሚያዋርዱን፣ ከክብር ዝቅ የሚያደርጉን፣ መለያየት ላይ እንድናተኩር የሚያደርጉን፣ ዘረኞች እንድንሆን፣ ለኔ ብቻ እንድንል ያደረጉን ሕመሞች አሉብን።

ድል ለመቀዳጀት፣ በዓለም አደባባይ አንደኞች እንድንሆን፣ ከፈለግን መጀመሪያ እንድንሸነፍ የሚያደርጉንን ምክንያቶች እናሸንፍ።

መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል " ጥቃቅኑን ቀበሮዎች አጥምዳችሁ ያዙ" እንዚህ ቀበሮዎች ጥቃቅን መሆናቸው ሳይሆን የሚያጠፉት ሰፊ የወይን እርሻ ነው ግምት ሊሰጠው የሚገባው። በዘመናችንም ችላ የምንላቸው ጥቃቅን የመሰሉን ለዓመታት አዕምሯችን ላይ የተሰሩ ነገሮች ዛሬ ላይ ለእርስ በርስ ጦርነት፣ ለስደት፣ ለሞት፣ ለጥላቻ፣ ለዘር እልቂት እየዳረገን ይገኛል።

እንድንሸነፍ ከሚያደርጉን ነገሮች መካከል አንዱ ዘረኝነት ነው፤ ለማሸነፍ ከፈለግን መጀመሪያ ዘረኝነትን የተጠናወተው ማንነታችንን ማሸነፍ ይኖርብናል።

ሌላው ጥላቻ ነው "ወንድሙን የሚጠላ ነፍሰ ገዳይ ነው" እንዲል መጽሐፍ ጥላቻ የዕድገት/የአሸናፊነት ጸር ነው። ስለዚህ መጀመሪያ ጥላቻን እናሸንፍ። ከዚያ ወደቀደመ ክብራችን እንመለሳለን። አለበለዚያ የሶስት ሺ ዘመን ታሪካችንን እናበላሻለን።

ሁሌም አሸናፊ ትሆን ዘንድ የሚያሸንፍህን አሸንፍ።
መልካም ጊዜ
ደረሰ ረታ

https://t.me/deressereta
553 viewsEagel view R.E, 16:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 15:20:11 ከአንተ ጊዜያዊ ጥቅም ይልቅ የወንድምህን ዘላቂ ጥቅም አስቀድም
78 viewsደረሰ ረታ, 12:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 15:20:10 https://youtube.com/shorts/HvT5Au_7htA?feature=share
75 viewsደረሰ ረታ, 12:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 11:15:02 ማስጠንቀቂያ

ልጆቻችንን እንዴት ነው የምናሳድገው?
ምን እያልናቸው፣
ምን እውቀት እያስገበየናቸው፣
ምን እየፈቀድን፣
ምን እየከለከልን፣  ነው የምናሳድጋቸው?

በመሠረቱ ልጆች መጠየቅ ይወዳሉ፤ ጠይቀው አይጨርሱም። ጠይቀው አይረኩም፣ በጥያቄ ላይ ጥያቄ ያከታትላሉ።

እኛም ምላሽ ከመስጠት ይልቅ መከልከል ይቀናናል፤ ምላሻችንም ክልከላ/ማስጠንቀቂያ ይበዛዋል።

ተው፣
አትንካ፣
እረፍ፣
ትወድቃለህ፣

የምላሾቻችን ድምር ውጤት በልጆቻችን ሥነ ልቡና ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል። አስተዳደጋቸውን እና ነገአቸውን ያመላክታል።

እኛ ለምን ፈሪ ሆንን?
በራስ መተማመን ለምን ጎደለን?
በአደባባይ ለምን መናገር ተሳነን?
ለምን አንሞክርም?
ለምን አንፈጥርም?
የምናስበውኝ የምንመኘውን ለምን አናደርግም?

ሌላ አዲስ ነገር የለውም ትናንት ከወላጆቻችን፣ ከአሳዳጊዎቻችን፣ ከአከባቢው ፣ ከማህበረሰቡ የሰማናቸው ቃላቶች፣ ያየናቸው ተግሳጾች፣ የተመከርነው ምክሮች፣ የስህተታችን ግብረ መልሶች ውጤት ስሪቶች ነን።

እኛስ ልጆቻችን እንዴት አይነት ልጆች እንዲሆኑ ነው የምንፈልገው?

በእርግጠኝነት እኛን መስለው እኛን አክለው እንዲያድጉ አንፈልግም።
ነገር ግን እንዴት እንዲሆኑ ነው እያሳደግናቸው ያለነው?

ሰው የዘራውን ያንኑ ያጭዳልና ልጆቻችንን እንዲያፈሩ የምንፈልገውን ዓይነት ዘር እንዝራባቸው።

ማስጠንቀቂያ ከበዛበት ምክርና ተግሳጽ ይልቅ ምሳሌነት ያለው ተግባር እና የሚያንጹ የሚያስተምሩ ቃላቶችን እንናገር።

ለቃላቶቻችን እና ለድርጊቶቻችን ጥንቃቄ እናድርግ። መልዕክቴ ነው።

መልካም ቀን።
ደረሰ ረታ

https://t.me/deressereta
790 viewsEagel view R.E, 08:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 03:46:57 #ቀናነት #ቀና አስተሳሰብ #መልካም ሐሳብ #በጎ ድርጊት

እነዚህ ሁሉ የደስታ ምንጭ ናቸው። መለማመድ ብቻ የሚፈልጉ ማንንም ዋጋ የማያስከፍሉ።
ማሰብ ፥ ማድረግ ብቻ።
ነገር ግን እንደምናስበው ቀላል ያይደሉ፤ እጅግ በጣም በተጽዕኖ የተሞሉ ናቸው።

በፍጹም ቅንነት ከታሰቡ ግን ማንም ሰው ሊያደርጋቸው የሚችላቸው።

ከሁሉ አስቀድሞ በዙሪያ ካሉ ወደኋላ ከሚስቡ ነገሮች መላቀቅ ይጠይቃል፣ መላቀቅ ብቻም ሳይሆን ቅንነት፣ መልካምነት ካለበት ከባቢ መጣበቅ ይጠይቃል።

አንዳች ኃይል ሊያስቆምህ የማይችልበት ጉልበት ይኖርሃል። ያንኑ አስብ፣ አሰላስል፣ ተለማመድ፣ አድርግ።

በተግባርህ አንተ የሕሊና እርካታ ስታገኝ ሌሎች ሠላምን፣ ደስታን፣ መጽናናትን፣ ብርታትን ያገኛሉና።

ብትማር፣ ብትነግድ፣ ብትሰለጥን ከዚህ የተሻለ ትርፍ ከምን ታገኛለህ? የትም።

#በጎሁን
#ቅንሁን
#መልካሙንነገርሁሉአድርግ

ቸር ቀን ተመኘሁልህ

ደረሰ ረታ
214 views00:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 15:31:46
475 views12:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 09:43:39 +++ የጀማሪ ጠባይ +++

መንፈሳዊ ሕይወትን ገና ስትጀምረው ለፍጹምነት ጥቂት የቀረህ ያህል ይሰማሃል። አንተ ጋር ያለው ደስታ እና ሰላም ሌሎች ጋር የሌለ ይመስልሃል። በዚህች ሁከት በሞላባት ዓለም አንተ ብቻ ክርስቶስን እንዳገኘኸው ታስባለህ። የቀረው ሕዝበ አዳም እንዲሁ በከንቱ ሲርመሰመስ የሚውል ባካና ሆኖ ይታይሃል። ታዝንለታለህ፣ አይይይ ይህ ኃጢአተኛ ሕዝብ ምን ይሻለዋል? ትላለህ።

የእውነተኛ መንፈሳዊ እድገት መገለጫ ግን ይህ አይደለም። ሰው ወደ እግዚአብሔር እየቀረበ ሲመጣ ከሌላው ሰው ይልቅ የራሱ ጉድለት ይታየዋል። መንፈሳዊነት የሚገልጥልህ ሰዎችን ተመልክተህ የምትፈርድበትን ውጫዊ ዓይንህን ሳይሆን ራስህን አይተህ የምትወቅስበት የውስጥ ዓይንህን ነው። መንፈሳዊ ሕይወትህ ሲጎመራ "አይ ሰው" ሳይሆን "አይ እኔ!" ያሰኝሃል። አባ ማቴዎስም እንዲህ ይላል "ሰው የበለጠ ወደ እግዚአብሔር ሲቀርብ ይበልጥ ኃጢአተኛ መሆኑ እየታየው ይመጣል። ነቢዩ ኢሳይያስ እግዚአብሔርን ካየ በኋላ ከንፈሮቼ የረከሱብኝና የጠፋሁ ሰው ነኝ እንዳለ።"

ከብቃት ደርሰህ መላእክት ሲወጡና ሲወርዱ ቢታዩህ እንኳን ሁሉ እንዳንተ ስለሚመስልህ እንደ ዮሐንስ ሐጺር "ሚካኤል ይበልጣል ወይስ ገብርኤል?" እያልህ ከአጠገብህ የቆመውን ትጠይቃለህ እንጂ "አይይ አንተ እንኳን ገና አልበቃህም። ብዙ ይቀርሃል" ብለህ ወዳጅህን አታናንቅም። ይልቅ "ለእኔ ብቻ ገልጦ ለሌላው እንዲሰውር የሚያደርገው ምንም ቁም ነገር የለኝም" በማለት ከወንድምህ የተሻልህ እንዳልሆንክ በፍጹም ልብህ ታምናለህ።

ለመንፈሳዊ ሕይወት አዲስ ስትሆን ገና ጥቂት ጸልየህ፣ ጥቂት ጾመህ፣ ጥቂት መጽውተህ ሳለ ግን ሩጫህን ወደ መጨረሱ የተቃረብህ ይመስልሃል። ጉዞህን በግማሽ እርምጃ ከመጀመርህ ከፍጻሜው ላይ የደረስህ ያህል ይሰማሃል። "እኔን ምሰሉ" ማለት ያምርሃል። ነገር ግን መንፈሳዊ ሕይወት የቱንም ያህል ብትሮጥበት ሁል ጊዜ እንደ ጀማሪ የሚያደርግ ረጅም ጎዳና ነው። ሰማንያ ዓመት በገዳም ሲጋደል የነበረው አባ ሲሶይ ነፍሱ ከሥጋው ልትለይ በቀረበች ጊዜ ብዙ መነኮሳት በአልጋው ዙሪያ ከበውት ሳለ ቅዱሱ "አምላኬ ሆይ፣ እባክህ ለንስሐ የሚሆን ጥቂት ጊዜን ስጠኝ?" እያለ በልቅሶ ሲማጸን ሰሙት። በዚህ የተገረሙት መነኮሳቱ አባ ሲሶይን "አባታችን አንተ እድሜ ልክህን በንስሐ የኖርህ መምህረ ንስሐ ሆነህ ሳለ እንዴት አሁን ጥቂት የንስሐ ጊዜን ትለምናለህ?" ቢሉት፣ ቅዱሱም "ልጆቼ ይህን መንፈሳዊ ጥበብ (ንስሐን) ገና አሁን መጀመሬ ነው" አላቸው።

ጌታ ሆይ መንፈሳዊ ሕይወት እኖር ዘንድ አስጀምረኝ፤ ገና ጀማሪ ሳለሁ ደርሻለሁ ከማለትም ሰውረኝ። እንድቆም አትፍቀድልኝ፤ ወደ አንተ ሳበኝ፣ አሳድገኝ።
''ስትጸልይ በማክበር ውስጥ መሆንን ተለማመድ፣ የልብና የሥጋ ማክበር ይኑርህ፣ የስሜቶች ሰላምም እንዲሁ። ቀስ በቀስ መዝሙራትን፣ ወንጌላትንና የዘወትር ጸሎቶችን አጥና። በሁሉም ጊዜ ውስጥ ጸሎት መጸለይን ተለማመድ፣ ስትሠራ፣ ስትራመድና ከሌሎች ሰዎች ጋር ስትቀመጥ እንኳ፣ ዘወትር ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ እኔ ኃጢአተኛውን ማረኝ እያልህ መጸለይን ተለማመድ።

በማንኛውም ጊዜ ለሌሎች ሰዎች መጸለይን ተለማመድ፣ ለሁሉም ሰዎችም ፍቅር አሳይ፣ ለጠላቶችህና አንተን ለሚሰድቡህ ሰዎች እንድትጸልይ የሚያዝህን የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ተለማመድና ተግባራዊ አድርግ።"


~2014 ዓ•ም ~
@mahtotetonetor2
54 views06:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 02:41:51
ሠማይን ያለ ባላ ምድርን ያለ ካስማ ያጸናህ መድኃኒዓለም ሆይ አመሰግንህ ዘንድ ምክንያቴ ብዙ ነው።

ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣኸኝ ሰው አድርገኽ ስለፈጠርከኝ አመሰግንሃለሁ።

በሕጻንነቴ እንደ ወላጅ ተንከባክበኽ ያሳደከኝ፣ በወጣትነቴ ተቅበዝብዤ እንዳልጠፋ በቤትህ የጠበከኝ አሁንም በዚህ ዓለም ውጣ ውረድ ውስጥ በምህረትኽ እና በቸርነትህ በመግባቴ እና በመውጣቴ ውስጥ የማትለየኝ ቸር አባት ሆይ ተመስገን።

ስምህን ስጠራህ የማላፍርብህ አባቴ፣ ስመካብህ በፍጹም የማልጠራጠርብኽ ጠባቂዬ፣ ጌጤ ውበቴ ጉልበቴ ደም ግባቴ አንተ ነኽ ተመስገንልኝ።

እንደኔ ባለጸጋ ማን አለ?

እንደ እኔ ጤነኛ ማን አለ?

እንደ እኔ ዘመደ ብዙ ማን አለ?

እንደ እኔ መውጣት መግባቱ የተከናወነለት ማን አለ?

ይኽ ሁሉ በአንተ ነው፤ ይኽ ሁሉ ምክንያቱ አንተ ነኽ፣ ሁለነገሬ አንተ ነኽ። ተመስገን።

በጨለማ ውስጥ አመሰግንሃለ፣ በብርሃን ውስጥ አመሰግናለሁ፣ በቀን በሌሊት አመሰግናለሁ፣ በደስታ እና በሐዘን ውስጥ አመሰግናለሁ፣ በሞት እና በሕይወት መካከል አመሰግናለሁ።
608 views23:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ