Get Mystery Box with random crypto!

ሳልሳዊ ቴዎድሮስ ከአባ አመሃ እየሱስ መልእክት የተወሰደ በተረፈ ስለ ንጉሡ | ደረጀ እና የድንግል ማርያም ልጆች ግሩፕ ቻናል።

ሳልሳዊ ቴዎድሮስ

ከአባ አመሃ እየሱስ መልእክት የተወሰደ

በተረፈ ስለ ንጉሡ ማንነት አሁን የምነግራችሁ በጣም ባጭሩ ነው። ዝርዝር ሁኔታ አልገባም።
ለወደፊቱ በድምፅ ሰፊ የሆነ ምስጢራዊ የትርጉም ትምህርት ስለ ንጉሡና ስለ ጳጳሱ ማንነት
ስለምለቅላችሁ በተስፋ ጠብቁኝ አትቸኩሉ። ሳለቅላችሁ ቀድመው ከመጡ ግን መጡ ነው።
የማቀርብላችሁ ራሴ በጥያቄና በመልስ ባዘጋጀሁት መሠረት ነው። ይኸውም በደንብ
እንዲገባችሁ ብየ በማሰብና በማመን ነው። በሉ ተቀበሉኝ፦
ጥያቄ፦ ንጉሥ ቴዎድሮስ የሚባል አለ የለም?
መልስ፦ በደንብ አለ እንጅ።
ጥያቄ፦ የት ነው የሚኖረው?
መልስ፦ ከጥንት ጀምሮ እንደነ ሄኖክ፣ኤልያስ፣ዕዝራ፣አቡነ አረጋዊ፣ቅዱስ
ያሬድ...........በክብር ተሰውሮ የሚኖር ነው እንጅ ጊዜው ደርሶ እስኪገለጥና
እስኪመጣ ድረስ ከአሁን በፊት ለማንም ለማን አልታየም አይታይም።
ጥያቄ፦ መቼ ነው የሚመጣ? መልስ፦ አይነገርም። ግን ግን በጣም በጣም ቅርብ ጊዜ ነው።
ከበራፋችሁ ደርሶ ሊገባ ቆሟልና ደስ ይበላችሁ። ጥያቄ፦ በየት ነው የሚመጣ?
መልስ፦ በምሥራቅ።
ጥያቄ ፦ በየትኛው የኢትዮጵያ ምሥራቃዊ ክፍል ነው? በበጌምድር ጎንደር ምሥራቅ? በሸዋ
ምሥራቅ? በጎጃም ምሥራቅ? በቤተ አምሐራ ( ወሎ) ምሥራቅ?
መልስ፦ አሁን አይነገርም፣ ሲመጣ ማየትና መቀበል ብቻ ነው።
ጥያቄ፦ ነገዱ ምንድን ነው?
መልስ፦ ቤተ አይሁድ እስራኤላዊ እና ኢትዮጵያዊ አማራ ነው።
ጥያቄ፦ ትውልድ ሀገሩ የት ነው?
መልስ፦ አሁን አይነገርም። የት እንደሆነ ያኔ ሲመጣ ታውቁታላችሁ።
ጥያቄ፦ ቴዎድሮስ ማለት ትርጉሙ ምን ማለት ነው?
መልስ፦ ቴዎድሮስ ቃሉ የግሪክ ነው እንጅ አማርኛም ግእዝም አይደለም። ትርጉሙም ስጦታ፣
የፈጣሪ ስጦታ ማለት ነው።
ጥያቄ፦ ግዛቱ እስከምን ነው?
መልስ፦ መላ ኢትዮጵያን፣ መላ አፍሪካን፣በፈጣሪ ፈቃድና ትእዛዝ እንደዛሬዋ አሜሪካ መላ
ዓለምን በኃያልነት ይገዛል ይመራል። እንደ ንጉሥ ሰሎሞን ዘመን መላው ዓለም ሁሉ ወዶና
ፈቅዶ ይገብርለታል፣ ይሰግድለታል..........ያኔ ግብጽና ሱዳን እንደዛሬው ኢትዮጵያን
መረበሽ ይቅርና መተንፈስም አይችሉም።
ጥያቄ፦ በሌላ መልኩ ደግሞ የሚመጣው ንጉሥ ንጉሥ ሕዝቅያስ ነው የሚሉ ስላሉ ይህስ
እንዴት ነው? ለምትሉኝ፦
መልስ፦ ሌላ ሁለተኛ ሆነ ሦስተኛ ንጉሥ ሕዝቅያስ የሚባል የለም፣ አይመጣምም። ንጉሥ
ሕዝቅያስ የሚባለው ራሱ ንጉሥ ቴዎድሮስ ነው እንጅ ሌላ አይደለም። ሰዎች ትምህርትና
እውቀት ሳይኖራቸው ዝምብለው ንጉሥ ሕዝቅያስ የሚባል ከቴዎድሮስ ቀድሞ ይመጣል፣
አገሩንና ሕዝቡን ያረጋጋል ምናምን ምናምን እያሉ ይቀባጥራሉ። ይህ ካለመማርና ካለማወቅ፣
እንዲሁም የፈጣሪን ምስጢራዊ የፀጋ ስጦታ ያለማግኘት ነው እንጅ የሚያናግራቸው ሕዝቅያስ
የሚባለው ራሱ ቴዎድሮስ ነው። ሕዝቅያስ የተባለበትም ራሱን የቻለ ትምህርታዊ ትርጉምና
ምስጢር ስላለው በድምፅ በምለቅበት ጊዜ ስለምተረጉምላችሁ በትእግስት ጠብቁኝ አትቸኩሉ።
ጥያቄ፦ ስንት ዓመት ይገዛል? መልስ፦ ከቁጥር አራት የጽሑፍ መልእክቴ ከሆነው መጨረሻ
ላይ ብሥራት ከሚለው ላይ አለላችሁ ያንን አንብቡ እላችኋለሁ።
በአንጻሩ ደግሞ የሚመጣው ጳጳስ መደበኛ ስሙ ፀሓይ ነው። ግን ግን በትንቢቱ ላይ ኤርምያስ
የሚባል ጳጳስ ይመጣል፥ አቡነ አረጋዊ የሚባል ስውሩ ጳጳስ ሆኖ ይመጣል እየተባለም ይነገራል።
አዎ ልክ ነው። ግን ግን ኤርምያስ የሚባለውም ሆነ አረጋዊ የሚባለው ራሱ ፀሐይ ነው እንጅ
ሌላ ኤርምያስና ሌላ አረጋዊ አይደሉም። ፀሐይን ኤርምያስና አረጋዊ የሚባልበትም ምክንያት
ራሱን የቻለ ትምህርታዊ ትርጉምና ምስጢር ስላለው ሁሉንም በድምፅ ስለቅ
እተረጉምላችኋለሁና በተስፋና በትእግስት ጠብቁኝ አትቸኩሉ። ከዚህ ውጭ ስውሩ አቡነ
አረጋዊ አሁን ጳጳስ ሆነው የሚገለጡና የሚመጡ ሳይሆን በሐሳዊ ዘመን ስውራን ሁሉ
ተገልጠው ሲያስተምሩና ሲዋጉ እሳቸውም ያኔ ተገልጠው የሚያስተምሩ፣ የሚዋጉና ሰማዕት
የሚሆኑ ናቸው። በጥቅሉ የጳጳሱ ማንነትም ምስጢሩ እንደ ንጉሥ ቴዎድሮስ ነው። ሳልነግራችሁ
የማልተወው ሌላ ተጨማሪ ጉዳይ ግን የሚመጡት ጳጳሳት ሁለት ናቸው። አንደኛው በትንቢት
የታወቀው አቡነ ፀሐይ ሲሆን ይህ ጳጳስ ዓለምን የሚመራ የዓለም ፓትርያርክ ነው። ፀሐይ
የተባለበትም ምስጢርና ትርጉም ስለዚህ ነው ባጭሩ። ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ ነው። ትውልድ ሀገሩ
ግን አሁን አይነገርም። ያኔ ሲመጣ ታውቁታላችሁ። ሁለመናው እንደ ንጉሡ ነው። ነገዱ ግን
በእስራኤል በኩል ነገደ ሌዊ ሲሆን በኢትዮጵያ በኩል ደግሞ ነገደ አምሓራ (አማራ) ነው።
ሁለተኛው ጳጳስ ደግሞ ትንቢት ያልተነገረለትና ሱባኤ ያልተቆጠረለት ሲሆን ሆኖም ግን ያኔ
የሚሾም ነው። ይኸውም የኢትዮጵያ ፓትርያሪክ የሚሆን ነው። ሥራውም ከዋናው የዓለሙ
ፓትርያሪክ ከፀሐይ በታች ሆኖ ኢትዮጵያን ይመራል። ይህኛውም ጳጳስ ነገዱ ኢትዮጵያዊ
አማራ ሲሆን ነገደ እስራኤል ይኑርበት አይኑርበት አላውቅም፣ አልተገለጠልኝም።
የምነግራችሁ የተማርኩትን፣ የተገለጠልኝንና የማውቀውን ብቻ ነው። ከዚህ ውጭ መናገር
የወንጌል ደላላዎች ሰይጣናዊ ስብከት ነው። ትውልድ ሀገሩን ግን አሁን አይነገርም። ሁሉንም
ነገር ያኔ ከፈጣሪ መቅሰፍት፣ ከኢትዮጵያ ቅጣት በሥጋ ሕይወት የተረፈ ሁሉ በደስታ ሆኖ ያያል
ያውቃል።