Get Mystery Box with random crypto!

ሚያዝያ 21 | የእመቤታችን ፍቅር የበዛላቸው፥ ከፈላስፋነት እና ከእስላምነት የተመለሱ ሁለት ቅዱሳ | ደረጀ እና የድንግል ማርያም ልጆች ግሩፕ ቻናል።


ሚያዝያ 21 | የእመቤታችን ፍቅር የበዛላቸው፥ ከፈላስፋነት እና ከእስላምነት የተመለሱ ሁለት ቅዱሳን የዕረፍታቸው መታሰቢያ ነው።

  ◈ ቅዱስ ብሩታዎስ ሐዋርያ

ይህም ቅዱስ አባት፥ ከመድኃኔዓለም ዕርገት 14 ዓመት ሲሆን በፍልስፍናው ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር ይከራከር ነበር።

በኋላ ግን አመነ እና በቅዱስ ጳውሎስ እጅ ተጠመቀ፤ ቅስናን ተሾመ።

ዘወትርም እመቤታችንን ሄጄ ባየኋት እያለ ይመኝ ነበር። በአንደኛው ቀንም ከአቴና ተነሣ እና ወደ ኢየሩሳሌም ሔደ። እግዚአብሔርም መንገዱን አቀናለት።

ኢየሩሳሌም የደረሰውም በእመቤታችን የዕረፍት ቀን ጥር 21፥ 49 ዓ.ም ሆነለት። ከማረፏም በፊት አግኝቷት፣ በእጇ ተባረከ።

ከደስታውም ብዛት የመጀመሪያውን ጥዑም ውዳሴ ደረሰላት። ሐዋርያትም በጣዕሙ ተጽናኑ፨

        ◈ አቡነ እጨጌ ዕንባቆም

የመናዊው እጨጌ ዕንባቆም በዐረብ ምድር በየመን የተወለዱ ሲሆን አስቀድመው እስላም ነበሩ።

በኋላ ግን መጻሕፍትን መርምረው ዕውነትን ይፈልጉ ጀመር። ከነጋዴዎችም ጋር በዳህላክ በኩል ወደ ኢትዮጵያ ገቡ።

መርሐ ቤቴ አካባቢም የሃይማኖት ትምህርትን ጀመሩ። ከግእዝ ንባብ የጀመሩ ተአምረ ማርያም ሲደርሱ የእመቤታችን ፍቅር እጅግ ሳባቸው።

በጌታችን በክርስቶስ አምነው ተጠምቀው ከመነኮሱ በኋላ በደብረ ሊባኖስ በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ወንበር ተሾመው እስከማገለግል የደረሱ ታላቅ አባት ናቸው፨
~ ~ ~
የእመቤታችንን ፍቅሯን የቅዱሳኑን በረከት ያድለን።