2022-08-29 16:16:35
የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ባደረባቸው በስጋት ምክንያት ግቢያቸውን ለቀው የወጡ ተማሪዎችን በሚመለከት ውሳኔ አሳለፈ
ሰኞ ነሐሴ 23 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በነሐሴ 22 ቀን 2014 ባደረባቸው ስጋት ምክንያት ግቢውን ለቀው መውጣታቸውን ገልጿል።
በዚህም መሰረት ዩኒቨርሲቲው የሚከተሉትን ውሳኔዎች አስተላልፏል፡፡
1ኛ. የመደበኛ መርሀ ግብር ተማሪዎች በሙሉ ወደ ዩኒቨርሲቲው መመለሻ ጊዜ በቀጣይ ዓመት ጥሪ በሚደረግበት ጊዜ ይሆናል።
2ኛ. የክረምት መርሀ ግብር ተማሪዎች በሙሉ የተጀመረውን ትምህርትና ፈተና ለማጠናቀቅ ወደ ዩኒቨርሲቲው መመለሻ ጊዜ መስከረም 03 ቀን 2015 መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
4.9K viewsedited 13:16