Get Mystery Box with random crypto!

የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች

የቴሌግራም ቻናል አርማ deaconhenokhaile — የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች
የቴሌግራም ቻናል አርማ deaconhenokhaile — የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች
የሰርጥ አድራሻ: @deaconhenokhaile
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 64.23K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል በዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ፈቃድ ትምህርቶች የሚለቀቁበት ነው::
@deaconhenokhaile
"ነገር ግን በክርስቶስ ሁልጊዜ ድል በመንሣቱ ለሚያዞረን በእኛም በየስፍራው ሁሉ የእውቀቱን ሽታ ለሚገልጥ ለአምላክ ምስጋና ይሁን"
2ኛ ቆሮ. 2:14

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 36

2022-08-15 02:38:06

26.7K views. ., 23:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 09:14:03 +እንዘ ሰለስቱ አሃዱ +

ግጥምና ዜማ :-ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
በዘማሪ:-ሊቀዲያቆን ወንደሰን በላይ

+እንዘ ሠለስቱ+

ዓለምን በጥበብ ለፈጠረ ጌታ
ዘወትር እናቅርብ የክብር ሰላምታ
መላእክት በፍርሃት ለሚያመሰግኑት
ለሥላሴ እናቅርብ አኮቴት ስብሐት

ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
እንዘ ሠለስቱ አሐዱ

በሃሳቡ ብቻ ዓለምን ለሠራ
በአምላካዊ ቃሉ ብርሃንን ላበራ
ሰውን በምሳሌው በአርኣያው ፈጥሮ
ከአፈር አበጀው ከሁሉ አክብሮ

ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
እንዘ ሠለስቱ አሐዱ

የሰው ልጅ ሲበድል አምላክ ልሁን ብሎ
የሰይጣንን ምክር አምኖ ተቀብሎ
አዳም አዳም ብሎ ፍለጋ ለወጣ
ለይቅር ባይ ጌታ ምስጋናን እናምጣ

ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
እንዘ ሠለስቱ አሐዱ

ወደ ዓለም ልኮ አብ አንድ ልጁን
ወልድም በፈቃዱ መጣ ሰው ሊሆን
በመንፈስ ቅዱስ ግብር ተጸንሶ ተወልዶ
አክሊል አቀዳጀን በመስቀል ተዋርዶ

ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
እንዘ ሠለስቱ አሐዱ

እንዴት ላመስግንህ የቅዱሳን አምላክ
በልቤ ጉልበትም ለአንተ ልንበርከክ
ዓይኔን ከእጄ ጋር ወደ ላይ አንሥቼ
እዘምርልሃለሁ እንደ አባቶቼ

ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
እንዘ ሠለስቱ አሐዱ

ዝማሬ : ሊቀ ዲያቆናት ወንድወሰን በላይ
ግጥምና ዜማ: ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
9.0K viewsካልባረከኝ አለቅህም, 06:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 08:57:11 Watch "ጓደኝነት | ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ | ተግባራዊ ክርስትና ክፍል 3-Friendship | Deacon Henok Haile-Living Christianity-Part 3" on YouTube


7.4K viewsካልባረከኝ አለቅህም, 05:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 10:27:38 + ዝም ብለን የምንጠላው ሰው +

ከሩቅ የምናውቀው አንዳንድ ሰው የለም? ብዙም አናውቀውም:: ቀርበን አውርተነው አናውቅም:: ስናየው ግን እንዲሁ ደስ የማይለንና ያለ ምክንያት የምንጠላው ሰው የለም?

"እሱን ሰውዬ ጥሎብኝ አልወደውም"

"አይ እሱን ልጅ ቀልቤ ትከሻዬ አልወደደውም"

"እኔ እንጃ ለምን እንደሆነ ባላውቅም አልወዳትም:: ምክንያቴን አትጠይቀኝ ግን በቃ እንዲሁ አልወዳትም"

ምንም ምክንያት ሳይኖረን እንዲሁ የምንጠላው ሰው አለ::

እግዚአብሔር ግን
"አንድያ ልጁን እስኪሠጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአል" (ዮሐ 3:16)

ጠላቶቹ ሳለን በልጁ ሞት አዳነን እንደሚል እርሱ እኛን ለመጥላት ብዙ ምክንያት ነበረው:: እርሱ ግን እንዲሁ ወደደን:: ከእኛ ምንም ባያገኝም ስለ እኛ ያለው ፍቅር የእንዲሁ ፍቅር (unconditional love) ነበረ:: እርሱ እንዲሁ ወዶናል እኛ ግን እንዲሁ ሰው እንጠላለን::
ያለ ምክንያት መውደድ ቢያቅተን እንኳን ያለ ምክንያት መጥላታችን (unconditional hate) ቢቀር ምናለ?
የሚያሳዝነው ያለ ምክንያት የጠላናቸውን ሰዎች የበለጠ ለመጥላት በልባችን እስር ቤት ውስጥ በጥላቻ ሰንሰለት እናስራቸውና የበለጠ ለመጥላት ስለእነርሱ ክፉ ክፉ ማስረጃ ለመስማት እንተጋለን:: ጥሩ ነገራቸውን ለመስማት አንፈልግም:: ክፉ ስንሰማ ግን "እኮ እኔ እኮ ዝም ብሎ ትከሻዬ ይነግረኝ ነበር" ብለን በደስታ እንፈነድቃለን:: እንዲሁ የጠላነውን ሰው በምክንያት ለመጥላት በመቻላችን ደስ ይለናል::

እኛ ሰውን ለመጥላት ምክንያት የምንፈልገውን ያህል እንዲሁ የወደደን እግዚአብሔር ግን እኛን ለመማር ሰበብ ይፈልጋል:: ትንሽ በጎነት ቅንጣት ቅንነት ሲያገኝ እጅግ ይደሰታል:: ባለቅኔው "እግዚአብሔር መንግሥቱን በርካሽ ዋጋ ሸጠው:: በቀዝቃዛ ውኃ በዘለላ ዕንባ እና ማረኝ በሚል የወንበዴ ጩኸት!" እንዳሉት እሱ እኛን ይቅር ለማለት የሚታይ በጎነት ቢያጣ ልባችን ውስጥ ገብቶ ትንሽ መጸጸት ካለ ይፈልጋል:: እንዲሁ ወዶናልና እንዲሁ ሊተወን አይፈልግም::

"እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለሆነ
ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳን በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወትን ሠጠን"
ኤፌ 2:4

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ታኅሣሥ 30 2013 ዓ ም
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ! በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)

ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like, Subscribe እና Share ያድርጉ :-

የፌስቡክ ገጽ :- https://www.facebook.com/officialHenokhaile/
የቴሌግራም ቻናል : https://t.me/deaconhenokhaile
የዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/channel/UCOaVsWC05aUjeqIEW3fWj7g
12.9K viewsካልባረከኝ አለቅህም, 07:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 01:30:04

12.8K viewsחנוך כּוֹחַ, 22:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 01:26:57 Watch "ሙሴ እና ክርስቶስ - ኢየሱስ በብሉይ ኪዳን - ክፍል 5 - ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ I Moses & Jesus - Christ in the OT - Dn Henok" on YouTube


12.3K viewsካልባረከኝ አለቅህም, 22:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 06:59:39
14.7K views , 03:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 06:59:39 < +ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን >>
"እኛክርስቲያኖች ነን ቤተክርስቲያን ደግሞ የክርስቲያን ቤት ናት ታዲያ ቤተክርስቲያን በእኛ ስም ከተጠራች ከተሰየመች በአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ስም ብትሰየም ጥፋቱ ምንድነው አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ክርስቲያን አይደሉም ?)
_
የሽቶ ጠርሙስ የሰበረችውና ሽቶ በጌታ እግር ላይ ያፈሰሰችው ሴት ታሪክ ወንጌል በተነበበት ሁሉ ስሟ ይነሳ ከተባለ ስለ ክርስቶስ ሲሉ አንገታቸው ስለተሰበረው ደማቸው ስለፈሰሰው "ስለነ ቅድስት አርሴማ ስለቅዱስ ጊወርጊስ ስለ ሰማዕታቱ ወንጌል በተነበበት ሁሉ ቢነገር ጥፋቱ ምንድነው የሽቶ ጠርሙስ ከመስበር አንገት መስበር አይበልጥም ን ? ሽቶ ከማፍሰስ ደም ማፍሰስ አይበልጥምን !?)
(ከትምህርቱ ላይ የተወሰደ )

Telegram >>~https://t.me/deaconhenokhaile/1839
#መ/ር ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ )
14.8K views , 03:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 06:54:14 Watch "ክርስቶስ በሩት ታሪክ ውስጥ - ኢየሱስ በብሉይ ኪዳን - ክፍል 7 - ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ I Jesus in the Book of Ruth - Christ in OT" on YouTube


14.2K viewsካልባረከኝ አለቅህም, 03:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 20:54:46 Watch "ጥላና አካል - ኢየሱስ በብሉይ ኪዳን - ክፍል 1 - ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ The Shadow & The Body - Christ in the OT - Dn Henok" on YouTube


17.5K viewsካልባረከኝ አለቅህም, 17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ