Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ ዜና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የ4ኛ ዙር አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ስ | Development Bank of Ethiopia (DBE) : Training to Lease Financing

አዲስ ዜና

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የ4ኛ ዙር አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ስልጠናን ሁሉንም የስልጠና ቀናት ሳያቆራርጡ ያጠናቀቁ ሰልጣኞች የቢዝነስ የአዋጭነት ምክረ ሀሳባቸውን እንዲያስገቡ ጥሪ አቀረበ፡፡

ባንኩ ከወራት በፊት በ4ኛ ዙር የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ስልጠና 112 ሺህ ለሚሆኑ ስራ ፈጣሪዎች ስልጠና መስጠቱ ይታወሳል፡፡

ከሰልጣኞች መካከል አምስቱንም ቀናት ስልጠናውን የተከታተሉና ሰልጠነው ያጠናቀቁ ለምስክር ወረቀት ዝግጁ የሆኑ ሰልጣኖች ብቻ ወደ ባንኩ ዲስትሪክቶችና ቅርንጫፎች በመቅረብ ሪፖርት እንዲያደርጉና የቢዝነስ አዋጭነት ሀሳባቸውን እንዲያስገቡ ነው ባንኩ ያሳሰበው፡፡

ሙሉ በሙሉ ስልጠናውን ተከታትለው ለአጠናቀቁ ሰልጣኞች የምስክር ወረቀት የማዘጋጀቱ ስራ እየተሰራ ሲሆን፣ የሰልጣኞችን የስራ ጊዜ በአግባቡ ለመጠቀም ሲባል ቀሪ የሌለባቸው ሰልጣኞች የቅድመ ዝግጅት ስራቸውን እንዲጀምሩ ነው ባንኩ ሁኔታዎችን ያመቻችው፡፡

ሰልጣኞች ወደ አምራች ኢንዱትሪ ዘርፍ ለመግባት ያላቸውን የስራ ተነሳሽነት ባንኩ መደገፍና ማበረታታት ስላለበት የስልጠና የምስክር ወረቀቱ እስኪሰራጭ ድረስ በልዩ ሁኔታ ማስታናገድ እንደሚገባ ስለታመነበት ነው፡፡

በዚህም መሰረት ሙሉ በሙሉ ሁሉንም የስልጠና ቀናት ሳያቆራርጡ የሰለጠኑ ሰልጣኞች እድሉን በመጠቀም ወደ ተመዘገቡባቸው የባንኩ ዲስትሪክቶችና ቅርንጫፎች በመቅረብ በተመቻቸው እድል እንዲጠቀሙ ባንኩ ጥሪ አቅርቧል፡፡