Get Mystery Box with random crypto!

ማስታወሻ የ 4ኘው ዙር ስልጠና ተመዝጋቢዎች ሆነው በአንደኛው ምእራፍ/ዙር ያልተጠሩ ሰልጣኞች | Development Bank of Ethiopia (DBE) : Training to Lease Financing

ማስታወሻ

የ 4ኘው ዙር ስልጠና ተመዝጋቢዎች ሆነው በአንደኛው ምእራፍ/ዙር ያልተጠሩ ሰልጣኞች መኖራቸውን፣ ስለዚህ በቀጣይ በሌሎች 2 ምእራፎች የተቀሩት ተመዝጋቢዎች ጥሪ እንደሚደረግ መነገሩ ይታወቃል።

ሆኖም ግን አንዳንድ ተመዝጋቢዎች ስልኬ ስለማይሰራ ስለነበር፣ ከሀገር ውጪ ስለነበርኩ፣ እና በመሰል ምክንያቶች ለ1ኛው ዙር/ምእራፍ ተጠርተው ከነበር ለማረጋገጥ አሁንም ድረስ በቅርንጫፍ ቢሮዎች እየቀረቡ እየጠየቁ መሆኑንና እነርሱ የሚያውቋቸው ለመጀመሪያው ምእራፍ ስልጠና ጥሪ ከተደረገላቸው ሰዎች ስልክ በመውሰድ እየደወሉ ለማረጋገጥ እየሞከሩ እንደሆነ ተስተውሏል። ስለዚህ ለመጀመሪያው ምእራፍ/ዙር ስልጠና የተጠሩ ሰልጣኞች ስም እስካሁን ያልደረሳችሁና መሰል ጥያቄ ያላችሁ ከ https://www.dbe.com.et/ ድረ ገፅ ላይ እንድትመለከቱት እንጋብዛለን።

የ4ኛው ዙር ተመዝጋቢዎች ቀጣይ ምእራፍ ስልጠና መቼ ነው የሚለው የአብዛኛዎቹ ጥያቄ መሆኑ በተግባር ከሚቀርቡ ተመዝጋቢዎች ጥያቄ ማውቅ ተችሏል።

ይህ ጥሪ መቼ ተደርጎ ስልጠናው ይሰጣል የሚለውን ባንኩ ባሉት የሚዲያ አማራጮች የሚያስታውቅ የሚያስታውቅ ስለሆነ በትእግስት እንድትጠብቁ እንጠይቃለን።

እንዲሁም ይህንን ስልጠና የወሰዳችሁ የምስክር ወረቀት ስለመዘጋጀቱ ለማወቅና ለመውሰድ እየጠየቃችሁ መሆኑ ታይቷል። ስለዚህ የምስክር ወረቀታችሁ ተዘጋጅቶ እንዳለቀ ባንኩ የሚያሳውቅ ስለሆነ አሁንም በትዕግስት እንድትጠብቁ እንጠይቃለን።

አንዳንዶች ባለማወቅ በአካል እየመጡ በአክስዮን ሰልጣኞችን እንድናደራጅ ባንኩ ፍቃድ/እውቅና ይስጠን የሚል ጥያቄ እያቀረቡ መሆኑ ታይቷል።

በአክስዮን መደራጀትን በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፍላጎቱ ያላቸውና መስፈርቱን የሚያሟሉ ዕጩዎችን እንዲደራጁ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገለፀ እንጂ ለማንም አካል በአክስዮን የማደራጀት ስራ እንዲሰራ ወይም እንዲሰራለት እውቅና እሰጣለሁ ወይም እፈቅዳለው ብሎ ያስተላለፈው መልዕክት የለም።

ስለዚህ፣ ሰልጣኞችን በአክስዪን እናደራጅ የሚል ጥየቄ እያቀረቡ ያሉ ሰዎች ባንኩ ከሚመራበት ፓሊሲና እና ፕሬዚደንቱ በስልጠና ማእከላት ከተናገሩትና እና በሚዲያ ከሰጡት ማብራሪያዎች መረዳት ያለባቸው ማመልከት የሚሹ ሰልጣኞች/አመልካቾች በሚፈልጉት ፕሮጀክት ዙሪያ ተሰባስበው፣ የአክስዮን ህግን እና አሰራርን ጠብቀውና አሟልተው ሲገኙ ባንኩ ያደራጃቸውና ወደ ስራ እንዲገቡ ይደረጋል የሚለውን ነው። ባንኩ ለማንም አካል የማደራጀት እውቅና እሰጣለው አለማለቱን መገንዘብ ያስፈልጋል።