Get Mystery Box with random crypto!

ማሳሰቢያ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአክሲዮን ለማደራጀት ፈቃድ የሰጠው አካል የለም! የኢትዮጵያ | Development Bank of Ethiopia (DBE) : Training to Lease Financing

ማሳሰቢያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአክሲዮን ለማደራጀት ፈቃድ የሰጠው አካል የለም!

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሰቃሾች ስልጠና በመስጠት ወደ ስራ በማስገባት ላይ ላይ መሆኑን ተከትሎ በአንዳንድ አካላት ተቋሙን የማይወክሉ የተሳሳቱ መረጃዎች እየወጡ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶችም ሆነ የአክሲዮን ማደራጀት ስራውን ባንካችን በራሱ አሰራር መሰረት የሚፈጽም እንጂ ሌላ ተቋም እንዲሰራለት ውክልና አልሰጠም።

በመሆኑም የአክስዮን አደረጃጀትን ጨምሮ ሌሎች ባንኩ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ከባንካችን ይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን እና ዌብሳይታችን ላይ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ለማስገንዘብ እንወዳለን፡፡

በመሆኑም ከዚህ በታች የተያያዘውን መረጃ እና ተያያዥ ጉዳዮችን የተመለከቱ ዜናዎች ከባንካችን ፈቃድ አግኝተው እየሰሩ አለመሆናቸውን እንድትረዱ እናሳስባለን።

ከሰሞኑ አንዳንድ አካላት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እየሰጠ ያለውን ስልጠና እንደ መልካም አጋጣሚያቸው ተጠቅመው በአክሲዮን የመደራጀት መልካም እድል እንደተፈጠረላቸው በማስመሰል መኪናን ጨምሮ በወር እስከ 60,000 ብር የሚደርስ ገቢ የሚያስገኝ ስራ እንዳላቸው፣የትርፋማ አክስዮን ድርሻ ባለቤት፣የኤሌክትሪክ መኪና እንደሚያገኙ፣የልማት ባንክ ብድር እንደሚያመቻቹ በመግለፅ ቴሌግራምን ጨምሮ በተለያዩ የማህበራዊ የትስስር ገፆች ላይ በማስተዋወቅ ላይ ይገኛሉ።

በመሆኑም የባንካችንን ስም በመጠቀም እናደራጃለን፣ ብድር እናሰጣለን በሚል የትኛውም አካል የሚያሰራጨው መረጃ ህገወጥ የወንጀል ድርጊት መሆኑን እንድታውቁና እንዳትጭበረበሩ እናሳስባለን።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአክሲዮን ተደራጅቶ ለመምጣት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችንና ሌሎች አስፈላጊ ሂደቶችን በይፋዊ የማህበራዊ የትስስር ገፆቻችን የምናሳውቅ ይሆናል፡፡

ተመሳሳይ ጥቆማዎችን ለባንካችን በማድረስ ሃሰተኞችን እንድታጋልጡ እየጠየቅን መሰል የማጭበርበር ድርጊቶችን በሚከተሉት ቁጥሮች እንድታሳውቁን በዚህ አጋጣሚ እንገልፃለን፡፡

1. 0904374444 ወይም
2.  0904357735 ወይም
3.  0904364436